የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘኁልቁ 35
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘኁልቁ የመጽሐፉ ይዘት

      • ለሌዋውያን የተሰጡ ከተሞች (1-8)

      • የመማጸኛ ከተሞች (9-34)

ዘኁልቁ 35:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 22:1፤ 36:13

ዘኁልቁ 35:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 49:7፤ ዘዳ 18:1፤ ኢያሱ 14:4
  • +ዘሌ 25:32-34፤ ኢያሱ 21:3፤ 2ዜና 11:14

ዘኁልቁ 35:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    አንድ ክንድ 44.5 ሴንቲ ሜትር ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

ዘኁልቁ 35:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 4:42
  • +ኢያሱ 20:2, 3, 7, 8፤ 21:13, 21, 27, 32, 36, 38

ዘኁልቁ 35:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 21:3

ዘኁልቁ 35:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 49:7
  • +ዘኁ 26:54፤ 33:54

ዘኁልቁ 35:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 3:8፤ 23:23፤ ዘኁ 34:2

ዘኁልቁ 35:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስ መትቶ የገደለ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 21:12, 13፤ ዘዳ 4:42፤ 19:4, 5

ዘኁልቁ 35:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 19:11, 12፤ ኢያሱ 20:5, 9
  • +ዘኁ 35:19፤ ዘዳ 19:6

ዘኁልቁ 35:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 4:41-43
  • +ዘዳ 19:8, 9፤ ኢያሱ 20:7

ዘኁልቁ 35:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስ መትቶ የገደለ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 12:49፤ ዘሌ 19:34፤ ዘኁ 15:16
  • +ኢያሱ 20:2, 3

ዘኁልቁ 35:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 9:5፤ ዘፀ 21:12፤ ዘሌ 24:17፤ ዘዳ 19:11, 12

ዘኁልቁ 35:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “አድብቶ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 21:14፤ ዘዳ 19:11, 12

ዘኁልቁ 35:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “አድብቶ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 21:12, 13፤ ዘዳ 19:4, 5፤ ኢያሱ 20:2, 3

ዘኁልቁ 35:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 35:12፤ ኢያሱ 20:4, 5

ዘኁልቁ 35:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 29:4, 7

ዘኁልቁ 35:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 20:6

ዘኁልቁ 35:30

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስ።”

  • *

    ቃል በቃል “በምሥክሮች አፍ።”

  • *

    ቃል በቃል “ነፍስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 17:6፤ 19:15፤ ዕብ 10:28
  • +ዘፍ 9:6፤ ዘፀ 20:13

ዘኁልቁ 35:31

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 9:5፤ ዘፀ 21:14፤ ዘዳ 19:13

ዘኁልቁ 35:32

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ነፍስ።”

ዘኁልቁ 35:33

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 4:8, 10፤ መዝ 106:38፤ ሉቃስ 11:50
  • +ዘፍ 9:6

ዘኁልቁ 35:34

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 25:8፤ ዘሌ 26:12

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘኁ. 35:1ዘኁ 22:1፤ 36:13
ዘኁ. 35:2ዘፍ 49:7፤ ዘዳ 18:1፤ ኢያሱ 14:4
ዘኁ. 35:2ዘሌ 25:32-34፤ ኢያሱ 21:3፤ 2ዜና 11:14
ዘኁ. 35:6ዘዳ 4:42
ዘኁ. 35:6ኢያሱ 20:2, 3, 7, 8፤ 21:13, 21, 27, 32, 36, 38
ዘኁ. 35:7ኢያሱ 21:3
ዘኁ. 35:8ዘፍ 49:7
ዘኁ. 35:8ዘኁ 26:54፤ 33:54
ዘኁ. 35:10ዘፀ 3:8፤ 23:23፤ ዘኁ 34:2
ዘኁ. 35:11ዘፀ 21:12, 13፤ ዘዳ 4:42፤ 19:4, 5
ዘኁ. 35:12ዘዳ 19:11, 12፤ ኢያሱ 20:5, 9
ዘኁ. 35:12ዘኁ 35:19፤ ዘዳ 19:6
ዘኁ. 35:14ዘዳ 4:41-43
ዘኁ. 35:14ዘዳ 19:8, 9፤ ኢያሱ 20:7
ዘኁ. 35:15ዘፀ 12:49፤ ዘሌ 19:34፤ ዘኁ 15:16
ዘኁ. 35:15ኢያሱ 20:2, 3
ዘኁ. 35:16ዘፍ 9:5፤ ዘፀ 21:12፤ ዘሌ 24:17፤ ዘዳ 19:11, 12
ዘኁ. 35:20ዘፀ 21:14፤ ዘዳ 19:11, 12
ዘኁ. 35:22ዘፀ 21:12, 13፤ ዘዳ 19:4, 5፤ ኢያሱ 20:2, 3
ዘኁ. 35:24ዘኁ 35:12፤ ኢያሱ 20:4, 5
ዘኁ. 35:25ዘፀ 29:4, 7
ዘኁ. 35:28ኢያሱ 20:6
ዘኁ. 35:30ዘዳ 17:6፤ 19:15፤ ዕብ 10:28
ዘኁ. 35:30ዘፍ 9:6፤ ዘፀ 20:13
ዘኁ. 35:31ዘፍ 9:5፤ ዘፀ 21:14፤ ዘዳ 19:13
ዘኁ. 35:33ዘፍ 4:8, 10፤ መዝ 106:38፤ ሉቃስ 11:50
ዘኁ. 35:33ዘፍ 9:6
ዘኁ. 35:34ዘፀ 25:8፤ ዘሌ 26:12
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘኁልቁ 35:1-34

ዘኁልቁ

35 ይሖዋ ሙሴን በኢያሪኮ በሚገኘው በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው የሞዓብ በረሃማ ሜዳ+ ላይ እንዲህ አለው፦ 2 “እስራኤላውያንን ከሚወርሱት ርስት ላይ ለሌዋውያኑ መኖሪያ የሚሆኑ ከተሞችን እንዲሰጧቸው እዘዛቸው፤+ በከተሞቹም ዙሪያ ያለውን የግጦሽ መሬት ለሌዋውያኑ መስጠት አለባቸው።+ 3 ከተሞቹ ለእነሱ መኖሪያ፣ የግጦሽ ቦታዎቹ ደግሞ ለከብቶቻቸውና ለዕቃዎቻቸው እንዲሁም ለሌሎች እንስሶቻቸው ይሆናሉ። 4 ለሌዋውያኑ የምትሰጧቸው የከተሞቹ የግጦሽ ቦታዎች ከከተማው ቅጥር በሁሉም አቅጣጫ 1,000 ክንድ* ይሆናል። 5 ከተማውን መካከል ላይ በማድረግ ከከተማው ውጭ በምሥራቅ በኩል 2,000 ክንድ፣ በደቡብ በኩል 2,000 ክንድ፣ በምዕራብ በኩል 2,000 ክንድ እንዲሁም በሰሜን በኩል 2,000 ክንድ ለኩ። እነዚህም የከተሞቻቸው የግጦሽ መሬት ይሆናሉ።

6 “ለሌዋውያኑ የምትሰጧቸው ከተሞች ነፍስ ያጠፋ ሰው ሸሽቶ የሚሸሸግባቸውን+ 6 የመማጸኛ ከተሞችና+ ሌሎች 42 ከተሞችን ነው። 7 በጠቅላላ 48 ከተሞችን ከነግጦሽ መሬታቸው ለሌዋውያኑ ትሰጧቸዋላችሁ።+ 8 ከተሞቹን የምትሰጧቸው ከእስራኤላውያን ርስት ላይ ወስዳችሁ ነው።+ ተለቅ ካለው ቡድን ላይ ብዙ ትወስዳላችሁ፤ አነስ ካለው ቡድን ላይ ደግሞ ጥቂት ትወስዳላችሁ።+ እያንዳንዱ ቡድን በወረሰው ርስት መጠን ካሉት ከተሞች ላይ የተወሰኑትን ለሌዋውያኑ መስጠት ይኖርበታል።”

9 ይሖዋ በመቀጠል ሙሴን እንዲህ አለው፦ 10 “እስራኤላውያንን ተናገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘እንግዲህ ወደ ከነአን ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን ልትሻገሩ ነው።+ 11 ሳያስበው ሰው የገደለ* ሰው ሸሽቶ የሚጠጋባቸው አመቺ የሆኑ የመማጸኛ ከተሞችን ለራሳችሁ ምረጡ።+ 12 እነዚህ ከተሞች ነፍስ ያጠፋው ሰው በማኅበረሰቡ ፊት ለፍርድ ከመቅረቡ በፊት+ እንዳይሞት ከደም ተበቃዩ+ የሚሸሸግባቸው ከተሞች ይሆኑላችኋል። 13 እናንተ የምትሰጧቸው ስድስቱ የመማጸኛ ከተሞች ለዚህ ዓላማ ያገለግላሉ። 14 የመማጸኛ ከተሞች ሆነው እንዲያገለግሉ ከዮርዳኖስ ወዲህ ሦስት ከተሞችን፣+ በከነአን ምድር ደግሞ ሦስት ከተሞችን+ ትሰጣላችሁ። 15 እነዚህ ስድስት ከተሞች ለእስራኤላውያንም ሆነ ለባዕድ አገር ሰው+ አሊያም በመካከላቸው ለሚኖር ሰፋሪ ሳያስበው ሰው የገደለ* ማንኛውም ሰው ሸሽቶ የሚጠጋባቸው ከተሞች ሆነው ያገለግላሉ።+

16 “‘ሆኖም ሰውየው ግለሰቡን በብረት መሣሪያ ቢመታውና ቢገድለው ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ ነው። ነፍሰ ገዳዩ ያለምንም ጥርጥር መገደል አለበት።+ 17 ሰውየው ግለሰቡን ሊገድለው በሚችል ድንጋይ ቢመታውና ቢገድለው ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ ነው። ነፍሰ ገዳዩ ያለምንም ጥርጥር መገደል አለበት። 18 ሰውየው ግለሰቡን ሊገድለው በሚችል ከእንጨት የተሠራ መሣሪያ ቢመታውና ቢገድለው ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ ነው። ነፍሰ ገዳዩ ያለምንም ጥርጥር መገደል አለበት።

19 “‘ነፍሰ ገዳዩን መግደል ያለበት ደም ተበቃዩ ይሆናል። ባገኘው ጊዜ እሱ ራሱ ይግደለው። 20 አንድ ሰው ሌላውን በጥላቻ ተገፋፍቶ ቢገፈትረው ወይም ተንኮል አስቦ* የሆነ ነገር ቢወረውርበትና ግለሰቡ ቢሞት+ 21 አሊያም በጥላቻ ተነሳስቶ በእጁ ቢመታውና ቢሞት መቺው ያለምንም ጥርጥር ይገደላል። እሱ ነፍሰ ገዳይ ነው። ደም ተበቃዩም ነፍሰ ገዳዩን ባገኘው ጊዜ ይገድለዋል።

22 “‘ይሁን እንጂ ሰውየው ግለሰቡን የገፈተረው በጥላቻ ተነሳስቶ ሳይሆን ሳያስበው ከሆነ ወይም ዕቃ የወረወረበት ተንኮል አስቦ* ካልሆነ+ 23 አሊያም ግለሰቡ ሳያየው ድንጋይ ቢጥልበትና ቢሞት ሆኖም ሰውየው ከግለሰቡ ጋር ጠላትነት ባይኖረውና ይህን ያደረገው እሱን ለመጉዳት አስቦ ባይሆን 24 ማኅበረሰቡ እነዚህን ደንቦች መሠረት በማድረግ በገዳዩና በደም ተበቃዩ መካከል ፍርድ ይስጥ።+ 25 ማኅበረሰቡም ነፍሰ ገዳዩን ከደም ተበቃዩ እጅ ታድጎ ሸሽቶበት ወደነበረው የመማጸኛ ከተማ ይመልሰው፤ እሱም በቅዱስ ዘይት የተቀባው+ ሊቀ ካህናት እስኪሞት ድረስ በዚያ ይቆይ።

26 “‘ይሁንና ገዳዩ ሸሽቶ ከገባበት የመማጸኛ ከተማ ወሰን ቢወጣና 27 ደም ተበቃዩም ገዳዩን ከመማጸኛ ከተማው ወሰን ውጭ አግኝቶ ቢገድለው በደም ዕዳ አይጠየቅም። 28 ምክንያቱም ሊቀ ካህናቱ እስኪሞት ድረስ በመማጸኛ ከተማው ውስጥ መቆየት ይገባዋል። ሊቀ ካህናቱ ከሞተ በኋላ ግን ገዳዩ ወደ ርስቱ መመለስ ይችላል።+ 29 እነዚህም በምትኖሩበት በየትኛውም ቦታ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ፍርድ ለመስጠት እንደሚያገለግል ደንብ ይሁኗችሁ።

30 “‘ሰው* የገደለ ማንኛውም ሰው ምሥክሮች ከመሠከሩበት*+ እንደ ነፍሰ ገዳይ ተቆጥሮ ይገደል፤+ ይሁን እንጂ ማንም ሰው* አንድ ግለሰብ በሚሰጠው ምሥክርነት ብቻ በሞት መቀጣት የለበትም። 31 ሞት ለሚገባው ነፍሰ ገዳይ ሕይወት* ቤዛ አትቀበሉ፤ ምክንያቱም ያለምንም ጥርጥር መገደል አለበት።+ 32 እንዲሁም ሸሽቶ ወደ መማጸኛ ከተማው ለገባ ሰው* ሊቀ ካህናቱ ከመሞቱ በፊት ወደ ምድሩ ተመልሶ እንዲኖር ለማድረግ ቤዛ አትቀበሉ።

33 “‘ደም ምድሪቱን ስለሚበክል ያላችሁባትን ምድር አትበክሉ፤+ ደም ባፈሰሰው ሰው ደም ካልሆነ በስተቀር በምድሪቱ ላይ ለፈሰሰው ደም ስርየት ሊኖር አይችልም።+ 34 የምትኖሩባትን፣ እኔም የምኖርባትን ምድር አታርክሱ፤ እኔ ይሖዋ በእስራኤል ሕዝብ መካከል እኖራለሁና።’”+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ