የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘሌዋውያን 6
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘሌዋውያን የመጽሐፉ ይዘት

      • ሌሎች የበደል መባዎች (1-7)

      • መባዎችን አስመልክቶ የተሰጠ መመሪያ (8-30)

        • የሚቃጠል መባ (8-13)

        • የእህል መባ (14-23)

        • የኃጢአት መባ (24-30)

ዘሌዋውያን 6:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 22:7፤ ዘሌ 19:11
  • +ዘኁ 5:6

ዘሌዋውያን 6:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 22:10, 11፤ ዘሌ 19:12፤ ኤፌ 4:25፤ ቆላ 3:9

ዘሌዋውያን 6:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 5:15, 16፤ ዘኁ 5:6, 7

ዘሌዋውያን 6:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 5:15፤ 7:1፤ ኢሳ 53:10

ዘሌዋውያን 6:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 5:18

ዘሌዋውያን 6:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 29:38-42፤ ዘኁ 28:3፤ ዕብ 10:11

ዘሌዋውያን 6:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በስብ የራሰ አመድ።” መሥዋዕት ሆነው በሚቀርቡት እንስሳት ስብ የራሰውን አመድ ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 28:39፤ ዘሌ 16:32፤ ሕዝ 44:17
  • +ዘፀ 28:42፤ 39:27, 28
  • +ዘፀ 27:3፤ ዘሌ 1:16

ዘሌዋውያን 6:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 16:23፤ ሕዝ 44:19
  • +ዘሌ 4:3, 12

ዘሌዋውያን 6:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 1:7፤ ነህ 13:30, 31
  • +ዘሌ 3:5, 16

ዘሌዋውያን 6:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 2:1፤ ዘኁ 15:3, 4

ዘሌዋውያን 6:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሚያረጋጋ፤ የሚያበርድ።” ቃል በቃል “እረፍት የሚሰጥ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 2:2, 9፤ 5:11, 12

ዘሌዋውያን 6:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 2:3፤ 5:13፤ ሕዝ 44:29፤ 1ቆሮ 9:13
  • +ዘሌ 10:12

ዘሌዋውያን 6:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 2:11
  • +ዘኁ 18:9
  • +ዘሌ 2:3, 10

ዘሌዋውያን 6:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መባዎቹን የሚነካቸውም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 18:10
  • +ዘሌ 24:8, 9

ዘሌዋውያን 6:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    አንድ አሥረኛ ኢፍ 2.2 ሊትር ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 30:30፤ ዕብ 5:1
  • +ዘፀ 16:36
  • +ዘፀ 29:1, 2, 40, 41፤ ዘሌ 2:1፤ 9:17፤ ዘኁ 28:4, 5

ዘሌዋውያን 6:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሚያረጋጋ፤ የሚያበርድ።” ቃል በቃል “እረፍት የሚሰጥ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 2:5፤ 7:9፤ 1ዜና 23:29

ዘሌዋውያን 6:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 10:6

ዘሌዋውያን 6:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 4:3
  • +ዘሌ 1:3, 11

ዘሌዋውያን 6:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 10:17፤ ዘኁ 18:9፤ ሕዝ 44:29
  • +ዘፀ 27:9፤ ዘሌ 6:14, 16፤ ሕዝ 42:13

ዘሌዋውያን 6:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 6:14, 18፤ 21:21, 22፤ ዘኁ 18:10
  • +ዘሌ 6:25

ዘሌዋውያን 6:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 4:5፤ 10:18፤ 16:27፤ ዕብ 13:11

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘሌ. 6:2ዘፀ 22:7፤ ዘሌ 19:11
ዘሌ. 6:2ዘኁ 5:6
ዘሌ. 6:3ዘፀ 22:10, 11፤ ዘሌ 19:12፤ ኤፌ 4:25፤ ቆላ 3:9
ዘሌ. 6:5ዘሌ 5:15, 16፤ ዘኁ 5:6, 7
ዘሌ. 6:6ዘሌ 5:15፤ 7:1፤ ኢሳ 53:10
ዘሌ. 6:7ዘሌ 5:18
ዘሌ. 6:9ዘፀ 29:38-42፤ ዘኁ 28:3፤ ዕብ 10:11
ዘሌ. 6:10ዘፀ 28:39፤ ዘሌ 16:32፤ ሕዝ 44:17
ዘሌ. 6:10ዘፀ 28:42፤ 39:27, 28
ዘሌ. 6:10ዘፀ 27:3፤ ዘሌ 1:16
ዘሌ. 6:11ዘሌ 16:23፤ ሕዝ 44:19
ዘሌ. 6:11ዘሌ 4:3, 12
ዘሌ. 6:12ዘሌ 1:7፤ ነህ 13:30, 31
ዘሌ. 6:12ዘሌ 3:5, 16
ዘሌ. 6:14ዘሌ 2:1፤ ዘኁ 15:3, 4
ዘሌ. 6:15ዘሌ 2:2, 9፤ 5:11, 12
ዘሌ. 6:16ዘሌ 2:3፤ 5:13፤ ሕዝ 44:29፤ 1ቆሮ 9:13
ዘሌ. 6:16ዘሌ 10:12
ዘሌ. 6:17ዘሌ 2:11
ዘሌ. 6:17ዘኁ 18:9
ዘሌ. 6:17ዘሌ 2:3, 10
ዘሌ. 6:18ዘኁ 18:10
ዘሌ. 6:18ዘሌ 24:8, 9
ዘሌ. 6:20ዘፀ 30:30፤ ዕብ 5:1
ዘሌ. 6:20ዘፀ 16:36
ዘሌ. 6:20ዘፀ 29:1, 2, 40, 41፤ ዘሌ 2:1፤ 9:17፤ ዘኁ 28:4, 5
ዘሌ. 6:21ዘሌ 2:5፤ 7:9፤ 1ዜና 23:29
ዘሌ. 6:22ዘዳ 10:6
ዘሌ. 6:25ዘሌ 4:3
ዘሌ. 6:25ዘሌ 1:3, 11
ዘሌ. 6:26ዘሌ 10:17፤ ዘኁ 18:9፤ ሕዝ 44:29
ዘሌ. 6:26ዘፀ 27:9፤ ዘሌ 6:14, 16፤ ሕዝ 42:13
ዘሌ. 6:29ዘሌ 6:14, 18፤ 21:21, 22፤ ዘኁ 18:10
ዘሌ. 6:29ዘሌ 6:25
ዘሌ. 6:30ዘሌ 4:5፤ 10:18፤ 16:27፤ ዕብ 13:11
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘሌዋውያን 6:1-30

ዘሌዋውያን

6 ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2 “አንድ ሰው* በአደራ እንዲይዝ ወይም እንዲያስቀምጥ ከተሰጠው ነገር ጋር በተያያዘ+ ባልንጀራውን በማታለል ኃጢአት ቢሠራና በይሖዋ ላይ ታማኝነት የማጉደል ተግባር ቢፈጽም+ አሊያም ባልንጀራውን ቢሰርቅ ወይም ቢያጭበረብር 3 አሊያም ደግሞ የጠፋ ነገር አግኝቶ አላየሁም ብሎ ቢዋሽና ሰውየው ከእነዚህ ኃጢአቶች መካከል አንዱንም እንዳልሠራ አድርጎ በሐሰት ቢምል+ እንዲህ ማድረግ አለበት፦ 4 ኃጢአት ቢሠራና በደለኛ ሆኖ ቢገኝ የሰረቀውን፣ ቀምቶ ወይም አጭበርብሮ የወሰደውን አሊያም በአደራ ተሰጥቶት የነበረውን ወይም ደግሞ ጠፍቶ ያገኘውን ነገር ይመልስ፤ 5 አሊያም በሐሰት የማለበትን ማንኛውንም ነገር ይመልስ፤ ሙሉ ካሳ ይክፈል፤+ የዋጋውንም አንድ አምስተኛ ይጨምርበት። በደለኛ መሆኑ በተረጋገጠበትም ዕለት ለባለቤቱ ይሰጠዋል። 6 በተተመነውም ዋጋ መሠረት እንከን የሌለበትን አውራ በግ ከመንጋው መካከል በመውሰድ የበደል መባው አድርጎ ለይሖዋ ለማቅረብ ወደ ካህኑ ያመጣዋል።+ 7 ካህኑም በይሖዋ ፊት ያስተሰርይለታል፤ እሱም በደለኛ እንዲሆን ያደረገው ማንኛውም ነገር ይቅር ይባልለታል።”+

8 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ 9 “አሮንንና ወንዶች ልጆቹን እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ ‘የሚቃጠል መባ ሕግ ይህ ነው፦+ የሚቃጠለው መባ ሌሊቱን ሙሉ እስኪነጋ ድረስ በመሠዊያው ላይ ባለው ማንደጃ ላይ ይቀመጣል፤ እሳቱም በመሠዊያው ላይ ሲነድ ያድራል። 10 ካህኑ ከበፍታ የተሠራውን የክህነት ልብሱን+ ይለብሳል፤ እርቃኑንም ለመሸፈን ከበፍታ የተሠራውን ቁምጣ+ ያደርጋል። ከዚያም በመሠዊያው ላይ ከነበረው በእሳት ከነደደው የሚቃጠል መባ የወጣውን አመድ*+ ያነሳል፤ በመሠዊያውም ጎን ያደርገዋል። 11 ከዚያም ልብሱን አውልቆ+ ሌላ ልብስ ይለብሳል፤ አመዱንም ከሰፈሩ ውጭ ወደሚገኝ ንጹሕ የሆነ ቦታ ይወስደዋል።+ 12 እሳቱ በመሠዊያው ላይ ዘወትር ይነድዳል። መጥፋትም የለበትም። ካህኑም በየማለዳው እንጨት ይማግድበት፤+ በላዩም ላይ የሚቃጠለውን መባ ይረብርብበት፤ የኅብረት መሥዋዕቶቹንም ስብ በላዩ ላይ ያጨስበታል።+ 13 በመሠዊያውም ላይ ያለማቋረጥ እሳት ይነድዳል። መጥፋትም የለበትም።

14 “‘የእህል መባ ሕግ ደግሞ ይህ ነው፦+ እናንተ የአሮን ወንዶች ልጆች በመሠዊያው ፊት ለፊት በይሖዋ ፊት ታቀርቡታላችሁ። 15 ከመካከላቸው አንዱ ለእህል መባ ከቀረበው የላመ ዱቄት ላይ ከነዘይቱ አንድ እፍኝ ያነሳል፤ እንዲሁም በእህል መባው ላይ ያለውን ነጭ ዕጣን በሙሉ ይወስዳል። አምላክ መላውን መባ እንዲያስበውም ለይሖዋ ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጨሰዋል።+ 16 ከዚያ የተረፈውን አሮንና ወንዶች ልጆቹ ይበሉታል፤+ እንደ ቂጣ ተጋግሮ በቅዱስ ስፍራ ይበላል። በመገናኛ ድንኳኑ ግቢ ውስጥ ይበሉታል።+ 17 ያለእርሾ መጋገር አለበት።+ ለእኔ በእሳት ከሚቀርቡልኝ መባዎች ውስጥ ይህን ድርሻቸው አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ።+ እንደ ኃጢአት መባና እንደ በደል መባ ሁሉ ይህም እጅግ ቅዱስ ነገር ነው።+ 18 የአሮን ዘር የሆኑ ወንዶች ሁሉ ይበሉታል።+ ይህ ለይሖዋ በእሳት ከሚቀርቡ መባዎች ውስጥ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ለእነሱ የሚሰጥ ዘላለማዊ ድርሻ ነው።+ የሚነካቸውም* ነገር ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።’”

19 ይሖዋም በድጋሚ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 20 “አሮን በሚቀባበት+ ቀን እሱና ወንዶች ልጆቹ ለይሖዋ የሚያቀርቡት መባ ይህ ነው፦ የኢፍ አንድ አሥረኛ*+ የላመ ዱቄት በቋሚነት የሚቀርብ የእህል መባ አድርገው ያቅርቡ፤+ ግማሹን ጠዋት፣ ግማሹን ደግሞ ምሽት ላይ ያቅርቡ። 21 በዘይት ከተለወሰ በኋላም በምጣድ ላይ ይጋገራል።+ ከዚያም በደንብ በዘይት ለውሰህ ታመጣዋለህ፤ የተጋገረውንም የእህል መባ ቆራርሰህ ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ይሆን ዘንድ ለይሖዋ ታቀርበዋለህ። 22 ከወንዶች ልጆቹ መካከል እሱን የሚተካው የተቀባው ካህንም ያቀርበዋል።+ ሙሉ በሙሉ የሚቀርብ መባም ሆኖ ለይሖዋ እንዲጨስ ይደረጋል፤ ይህም ዘላቂ ሥርዓት ነው። 23 አንድ ካህን የሚያቀርበው እያንዳንዱ የእህል መባ ሙሉ በሙሉ መቃጠል ይኖርበታል። መበላት የለበትም።”

24 ይሖዋ በድጋሚ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 25 “አሮንንና ወንዶች ልጆቹን እንዲህ በላቸው፦ ‘የኃጢአት መባ ሕግ ይህ ነው፦+ ለኃጢአት መባ የሚሆነውም እንስሳ፣ ለሚቃጠል መባ የሚሆነው እንስሳ በሚታረድበት ቦታ+ በይሖዋ ፊት ይታረዳል። ይህ እጅግ ቅዱስ የሆነ ነገር ነው። 26 ይህን ለኃጢአት መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርበው ካህን ይበላዋል።+ በመገናኛ ድንኳኑ ግቢ ውስጥ ቅዱስ በሆነ ስፍራ ይበላል።+

27 “‘ሥጋውን የሚነካ ማንኛውም ነገር ቅዱስ ይሆናል፤ ማንም ሰው የእንስሳውን ደም በልብሱ ላይ ቢረጭ ደም የተረጨበትን ልብስ በቅዱስ ስፍራ እጠበው። 28 ሥጋው የተቀቀለበት የሸክላ ዕቃም መሰባበር አለበት። የተቀቀለው ከመዳብ በተሠራ ዕቃ ከሆነ ግን ዕቃው ፍትግ ተደርጎ በውኃ መታጠብ አለበት።

29 “‘ካህን የሆነ ወንድ ሁሉ ይበላዋል።+ እጅግ ቅዱስ የሆነ ነገር ነው።+ 30 ይሁን እንጂ በቅዱሱ ስፍራ ለማስተሰረያ እንዲሆን ደሙ ወደ መገናኛ ድንኳኑ የገባ የኃጢአት መባ መበላት የለበትም።+ በእሳት መቃጠል አለበት።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ