የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የሐዋርያት ሥራ 14
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ሥራ የመጽሐፉ ይዘት

      • በኢቆንዮን የተገኘ እድገትና ያጋጠማቸው ተቃውሞ (1-7)

      • “አማልክት በሰው አምሳል ሆነው ወደ እኛ ወርደዋል!” (8-18)

      • ጳውሎስ በድንጋይ ቢወገርም በሕይወት ተረፈ (19, 20)

      • ጉባኤዎችን አጠናከሩ (21-23)

      • ወደ ሶርያ አንጾኪያ ተመለሱ (24-28)

የሐዋርያት ሥራ 14:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ከአሕዛብ ወገን የሆኑትን ሰዎች ነፍሳት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 13:45

የሐዋርያት ሥራ 14:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 19:11፤ ዕብ 2:3, 4

የሐዋርያት ሥራ 14:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 14:19

የሐዋርያት ሥራ 14:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 10:23

የሐዋርያት ሥራ 14:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 9:28

የሐዋርያት ሥራ 14:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 35:6

የሐዋርያት ሥራ 14:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 28:3-6

የሐዋርያት ሥራ 14:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 10:25, 26
  • +ዘፀ 20:11፤ መዝ 146:6

የሐዋርያት ሥራ 14:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 17:30

የሐዋርያት ሥራ 14:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 17:26, 27፤ ሮም 1:20
  • +መዝ 147:8፤ ኤር 5:24፤ ማቴ 5:45
  • +መዝ 145:16

የሐዋርያት ሥራ 14:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 17:13
  • +2ቆሮ 11:25

የሐዋርያት ሥራ 14:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 16:1

የሐዋርያት ሥራ 14:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የደቀ መዛሙርቱን ነፍስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 10:38፤ ዮሐ 15:19፤ ሮም 8:17፤ 1ተሰ 3:4
  • +ሥራ 11:22, 23

የሐዋርያት ሥራ 14:23

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ቲቶ 1:5
  • +ሥራ 13:2, 3

የሐዋርያት ሥራ 14:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 13:13

የሐዋርያት ሥራ 14:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 13:1, 2

የሐዋርያት ሥራ 14:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 11:18

ተዛማጅ ሐሳብ

ሥራ 14:2ሥራ 13:45
ሥራ 14:3ሥራ 19:11፤ ዕብ 2:3, 4
ሥራ 14:5ሥራ 14:19
ሥራ 14:6ማቴ 10:23
ሥራ 14:9ማቴ 9:28
ሥራ 14:10ኢሳ 35:6
ሥራ 14:11ሥራ 28:3-6
ሥራ 14:15ሥራ 10:25, 26
ሥራ 14:15ዘፀ 20:11፤ መዝ 146:6
ሥራ 14:16ሥራ 17:30
ሥራ 14:17ሥራ 17:26, 27፤ ሮም 1:20
ሥራ 14:17መዝ 147:8፤ ኤር 5:24፤ ማቴ 5:45
ሥራ 14:17መዝ 145:16
ሥራ 14:19ሥራ 17:13
ሥራ 14:192ቆሮ 11:25
ሥራ 14:20ሥራ 16:1
ሥራ 14:22ማቴ 10:38፤ ዮሐ 15:19፤ ሮም 8:17፤ 1ተሰ 3:4
ሥራ 14:22ሥራ 11:22, 23
ሥራ 14:23ቲቶ 1:5
ሥራ 14:23ሥራ 13:2, 3
ሥራ 14:24ሥራ 13:13
ሥራ 14:26ሥራ 13:1, 2
ሥራ 14:27ሥራ 11:18
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
የሐዋርያት ሥራ 14:1-28

የሐዋርያት ሥራ

14 በኢቆንዮን ጳውሎስና በርናባስ አብረው ወደ አይሁዳውያን ምኩራብ ገቡ፤ በዚያም ጥሩ ንግግር ስለሰጡ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አይሁዳውያንና ግሪካውያን አማኞች ሆኑ። 2 ሆኖም ያላመኑት አይሁዳውያን ከአሕዛብ ወገን የሆኑትን ሰዎች* በማነሳሳት በወንድሞች ላይ ጥላቻ እንዲያድርባቸው አደረጉ።+ 3 በመሆኑም ከይሖዋ* ባገኙት ሥልጣን በድፍረት እየተናገሩ በኢቆንዮን ረዘም ላለ ጊዜ ቆዩ፤ እሱም ተአምራዊ ምልክቶችና ድንቅ ነገሮች በእነሱ አማካኝነት እንዲከናወኑ በማድረግ ስለ ጸጋው የሚነገረው መልእክት ትክክል መሆኑን ያረጋግጥላቸው ነበር።+ 4 ይሁንና የከተማዋ ሕዝብ ተከፋፈለ፤ አንዳንዶቹ ከአይሁዳውያን ጎን ሲቆሙ ሌሎቹ ደግሞ ከሐዋርያት ጎን ቆሙ። 5 አሕዛብና አይሁዳውያን ከገዢዎቻቸው ጋር ሆነው ሊያንገላቷቸውና በድንጋይ ሊወግሯቸው በሞከሩ ጊዜ+ 6 ጳውሎስና በርናባስ ይህን ስላወቁ ልስጥራና ደርቤ ወደሚባሉት የሊቃኦንያ ከተሞች እንዲሁም በዙሪያቸው ወዳሉት መንደሮች ሸሹ።+ 7 በዚያም ምሥራቹን ማወጃቸውን ቀጠሉ።

8 በልስጥራም አንድ ሰው ተቀምጦ ነበር። እሱም ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ ሽባ የነበረ ሲሆን ፈጽሞ በእግሩ ሄዶ አያውቅም። 9 ይህ ሰው ጳውሎስ ሲናገር ያዳምጥ ነበር። ጳውሎስም ትኩር ብሎ አየውና ለመዳን የሚያበቃ እምነት እንዳለው ተመልክቶ+ 10 ከፍ ባለ ድምፅ “ተነስና በእግርህ ቁም” አለው። ሰውየውም ዘሎ ተነሳና መራመድ ጀመረ።+ 11 ሕዝቡም ጳውሎስ ያደረገውን ባዩ ጊዜ በሊቃኦንያ ቋንቋ “አማልክት በሰው አምሳል ሆነው ወደ እኛ ወርደዋል!” በማለት ጮኹ።+ 12 በርናባስን ዙስ፣ ጳውሎስን ደግሞ ዋና ተናጋሪ ስለነበር ሄርሜስ ብለው ይጠሯቸው ጀመር። 13 በከተማዋ መግቢያ ላይ ይገኝ የነበረው የዙስ ቤተ መቅደስ ካህን፣ ኮርማዎችና የአበባ ጉንጉን ወደ ከተማዋ መግቢያ በማምጣት ከሕዝቡ ጋር ሆኖ መሥዋዕት ሊሠዋላቸው ፈለገ።

14 ይሁን እንጂ ሐዋርያቱ በርናባስና ጳውሎስ ይህን ሲሰሙ ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ሮጠውም ሕዝቡ መሃል በመግባት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እንዲህ አሉ፦ 15 “እናንተ ሰዎች፣ እንዲህ የምታደርጉት ለምንድን ነው? እኛም እንደ እናንተው ድክመት ያለብን ሰዎች ነን።+ ምሥራቹን እያወጅንላችሁ ያለነውም እነዚህን ከንቱ ነገሮች ትታችሁ ሰማይን፣ ምድርን፣ ባሕርንና በውስጣቸው ያሉትን ነገሮች ሁሉ የፈጠረውን ሕያው አምላክ እንድታመልኩ ነው።+ 16 ባለፉት ትውልዶች፣ ሕዝቦች ሁሉ በራሳቸው መንገድ እንዲሄዱ ፈቀደላቸው፤+ 17 ይሁንና ለራሱ ምሥክር ከማቅረብ ወደኋላ አላለም፤+ ከሰማይ ዝናብ በማዝነብና ፍሬያማ ወቅቶችን በመስጠት+ እንዲሁም የተትረፈረፈ ምግብ በማቅረብና ልባችሁን በደስታ በመሙላት መልካም ነገር አድርጓል።”+ 18 ይህን ሁሉ ተናግረው እንኳ ሕዝቡ እንዳይሠዋላቸው ያስጣሉት በብዙ ችግር ነበር።

19 ሆኖም አይሁዳውያን ከአንጾኪያና ከኢቆንዮን መጥተው ሕዝቡን አግባቡ፤+ ጳውሎስንም በድንጋይ ከወገሩት በኋላ የሞተ መስሏቸው ጎትተው ከከተማዋ አወጡት።+ 20 ደቀ መዛሙርቱ መጥተው በከበቡት ጊዜ ግን ተነስቶ ወደ ከተማዋ ገባ። በማግስቱም ከበርናባስ ጋር ወደ ደርቤ ሄደ።+ 21 በዚያች ከተማ ምሥራቹን ሰብከው በርካታ ደቀ መዛሙርት ካፈሩ በኋላ ወደ ልስጥራ፣ ወደ ኢቆንዮንና ወደ አንጾኪያ ተመለሱ። 22 በዚያም “በብዙ መከራ አልፈን ወደ አምላክ መንግሥት መግባት አለብን”+ እያሉ በእምነት ጸንተው እንዲኖሩ በማበረታታት ደቀ መዛሙርቱን* አጠናከሩ።+ 23 ከዚህም በተጨማሪ በየጉባኤው ሽማግሌዎችን ሾሙላቸው፤+ ከጾሙና ከጸለዩም በኋላ+ ላመኑበት ለይሖዋ* አደራ ሰጧቸው።

24 ከዚያም በጵስድያ በኩል አልፈው ወደ ጵንፍልያ+ መጡ፤ 25 በጴርጌ ቃሉን ካወጁ በኋላ ወደ አታሊያ ወረዱ። 26 ከዚያም ተነስተው በመርከብ ወደ አንጾኪያ ሄዱ፤ ጳውሎስና በርናባስ አሁን ያጠናቀቁትን ሥራ እንዲያከናውኑ ለአምላክ ጸጋ በአደራ የተሰጡት በአንጾኪያ ነበር።+

27 እዚያም ደርሰው ጉባኤውን ከሰበሰቡ በኋላ አምላክ በእነሱ አማካኝነት ያከናወናቸውን በርካታ ነገሮች እንዲሁም ለአሕዛብ የእምነትን በር እንደከፈተላቸው ተረኩላቸው።+ 28 በዚያም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ረዘም ያለ ጊዜ አሳለፉ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ