የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዮሐንስ 14
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዮሐንስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ወደ አብ መቅረብ የሚቻልበት ብቸኛው መንገድ ኢየሱስ ነው (1-14)

        • “እኔ መንገድ፣ እውነትና ሕይወት ነኝ” (6)

      • ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስን እንደሚልክ ቃል ገባ (15-31)

        • “ከእኔ አብ ይበልጣል” (28)

ዮሐንስ 14:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 14:27
  • +ማር 11:22፤ 1ጴጥ 1:21

ዮሐንስ 14:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 12:32፤ 1ጴጥ 1:3, 4

ዮሐንስ 14:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ወደ ቤቴ እወስዳችኋለሁ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 17:24፤ ሮም 8:17፤ ፊልጵ 1:23፤ 1ተሰ 4:16, 17

ዮሐንስ 14:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 11:16

ዮሐንስ 14:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 10:9፤ ኤፌ 2:18፤ ዕብ 10:19, 20
  • +ዮሐ 1:17፤ ኤፌ 4:21
  • +ዮሐ 1:4፤ 6:63፤ 17:3፤ ሮም 6:23
  • +ሥራ 4:12

ዮሐንስ 14:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 11:27፤ ዮሐ 1:18

ዮሐንስ 14:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 12:45፤ ቆላ 1:15፤ ዕብ 1:3

ዮሐንስ 14:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 10:38፤ 17:21
  • +ዮሐ 7:16፤ 8:28፤ 12:49

ዮሐንስ 14:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 5:36

ዮሐንስ 14:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 2:32, 33
  • +ማቴ 21:21፤ ሥራ 1:8፤ 2:41

ዮሐንስ 14:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 15:16፤ 16:23

ዮሐንስ 14:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 13:34፤ 15:10፤ ያዕ 1:22

ዮሐንስ 14:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አጽናኝ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 24:49፤ ዮሐ 15:26፤ 16:7፤ ሥራ 1:5፤ 2:1, 4፤ ሮም 8:26

ዮሐንስ 14:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 10:19, 20፤ ዮሐ 16:13፤ 1ቆሮ 2:12፤ 1ዮሐ 2:27
  • +1ቆሮ 2:14

ዮሐንስ 14:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ወላጅ አልባ እንደሆኑ ልጆች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 28:20

ዮሐንስ 14:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 10:40, 41

ዮሐንስ 14:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 10:38፤ 17:21

ዮሐንስ 14:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 6:13, 16፤ ሥራ 1:13

ዮሐንስ 14:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 15:10
  • +1ዮሐ 2:24፤ ራእይ 3:20

ዮሐንስ 14:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 5:19፤ 7:16፤ 12:49

ዮሐንስ 14:26

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አጽናኝ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 24:49፤ ዮሐ 15:26፤ 16:13፤ 1ዮሐ 2:27

ዮሐንስ 14:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 16:33፤ ኤፌ 2:14፤ ፊልጵ 4:6, 7፤ ቆላ 3:15፤ 2ተሰ 3:16

ዮሐንስ 14:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 20:17፤ 1ቆሮ 11:3፤ 15:28፤ ፊልጵ 2:5, 6

ዮሐንስ 14:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 13:19፤ 16:4

ዮሐንስ 14:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 12:31፤ 16:11
  • +ዮሐ 16:33

ዮሐንስ 14:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 10:18፤ 12:49፤ 15:10፤ ፊልጵ 2:8

ተዛማጅ ሐሳብ

ዮሐ. 14:1ዮሐ 14:27
ዮሐ. 14:1ማር 11:22፤ 1ጴጥ 1:21
ዮሐ. 14:2ሉቃስ 12:32፤ 1ጴጥ 1:3, 4
ዮሐ. 14:3ዮሐ 17:24፤ ሮም 8:17፤ ፊልጵ 1:23፤ 1ተሰ 4:16, 17
ዮሐ. 14:5ዮሐ 11:16
ዮሐ. 14:6ዮሐ 10:9፤ ኤፌ 2:18፤ ዕብ 10:19, 20
ዮሐ. 14:6ዮሐ 1:17፤ ኤፌ 4:21
ዮሐ. 14:6ዮሐ 1:4፤ 6:63፤ 17:3፤ ሮም 6:23
ዮሐ. 14:6ሥራ 4:12
ዮሐ. 14:7ማቴ 11:27፤ ዮሐ 1:18
ዮሐ. 14:9ዮሐ 12:45፤ ቆላ 1:15፤ ዕብ 1:3
ዮሐ. 14:10ዮሐ 10:38፤ 17:21
ዮሐ. 14:10ዮሐ 7:16፤ 8:28፤ 12:49
ዮሐ. 14:11ዮሐ 5:36
ዮሐ. 14:12ሥራ 2:32, 33
ዮሐ. 14:12ማቴ 21:21፤ ሥራ 1:8፤ 2:41
ዮሐ. 14:13ዮሐ 15:16፤ 16:23
ዮሐ. 14:15ዮሐ 13:34፤ 15:10፤ ያዕ 1:22
ዮሐ. 14:16ሉቃስ 24:49፤ ዮሐ 15:26፤ 16:7፤ ሥራ 1:5፤ 2:1, 4፤ ሮም 8:26
ዮሐ. 14:17ማቴ 10:19, 20፤ ዮሐ 16:13፤ 1ቆሮ 2:12፤ 1ዮሐ 2:27
ዮሐ. 14:171ቆሮ 2:14
ዮሐ. 14:18ማቴ 28:20
ዮሐ. 14:19ሥራ 10:40, 41
ዮሐ. 14:20ዮሐ 10:38፤ 17:21
ዮሐ. 14:22ሉቃስ 6:13, 16፤ ሥራ 1:13
ዮሐ. 14:23ዮሐ 15:10
ዮሐ. 14:231ዮሐ 2:24፤ ራእይ 3:20
ዮሐ. 14:24ዮሐ 5:19፤ 7:16፤ 12:49
ዮሐ. 14:26ሉቃስ 24:49፤ ዮሐ 15:26፤ 16:13፤ 1ዮሐ 2:27
ዮሐ. 14:27ዮሐ 16:33፤ ኤፌ 2:14፤ ፊልጵ 4:6, 7፤ ቆላ 3:15፤ 2ተሰ 3:16
ዮሐ. 14:28ዮሐ 20:17፤ 1ቆሮ 11:3፤ 15:28፤ ፊልጵ 2:5, 6
ዮሐ. 14:29ዮሐ 13:19፤ 16:4
ዮሐ. 14:30ዮሐ 12:31፤ 16:11
ዮሐ. 14:30ዮሐ 16:33
ዮሐ. 14:31ዮሐ 10:18፤ 12:49፤ 15:10፤ ፊልጵ 2:8
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዮሐንስ 14:1-31

የዮሐንስ ወንጌል

14 “ልባችሁ አይረበሽ።+ በአምላክ እመኑ፤+ በእኔም ደግሞ እመኑ። 2 በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ ቦታ አለ። ይህ ባይሆን ኖሮ በግልጽ እነግራችሁ ነበር፤ ለእናንተ ቦታ ለማዘጋጀት እሄዳለሁና።+ 3 ደግሞም ሄጄ ቦታ ባዘጋጀሁላችሁ ጊዜ እኔ ባለሁበት እናንተም እንድትሆኑ እንደገና መጥቼ እኔ ወዳለሁበት እወስዳችኋለሁ።*+ 4 እኔ ወደምሄድበትም ቦታ የሚወስደውን መንገድ ታውቃላችሁ።”

5 ቶማስም+ “ጌታ ሆይ፣ ወዴት እንደምትሄድ አናውቅም። ታዲያ መንገዱን እንዴት ማወቅ እንችላለን?” አለው።

6 ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “እኔ መንገድ፣+ እውነትና+ ሕይወት+ ነኝ። በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።+ 7 እኔን ብታውቁኝ ኖሮ አባቴንም ታውቁት ነበር፤ ከዚህ ጊዜ አንስቶ ታውቁታላችሁ፤ ደግሞም አይታችሁታል።”+

8 ፊልጶስም “ጌታ ሆይ፣ አብን አሳየንና ይበቃናል” አለው።

9 ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “ፊልጶስ፣ ከእናንተ ጋር ይህን ያህል ረጅም ጊዜ ኖሬም እንኳ አላወቅከኝም? እኔን ያየ ሁሉ አብንም አይቷል።+ ታዲያ እንዴት ‘አብን አሳየን’ ትላለህ? 10 እኔ ከአብ ጋር አንድነት እንዳለኝና አብ ከእኔ ጋር አንድነት እንዳለው አታምንም?+ የምነግራችሁን ነገር የምናገረው ከራሴ አመንጭቼ አይደለም፤+ ሆኖም ሥራውን እየሠራ ያለው ከእኔ ጋር አንድነት ያለው አብ ነው። 11 እኔ ከአብ ጋር አንድነት እንዳለኝ አብም ከእኔ ጋር አንድነት እንዳለው እመኑኝ፤ ካልሆነ ደግሞ ከተሠሩት ሥራዎች የተነሳ እመኑ።+ 12 እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ በእኔ የሚያምን ሁሉ እኔ የምሠራቸውን ሥራዎች ይሠራል፤ እንዲያውም እኔ ወደ አብ ስለምሄድ+ እሱ ከእነዚህ የበለጡ ሥራዎች ይሠራል።+ 13 በተጨማሪም አብ በወልድ አማካኝነት እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ።+ 14 ማንኛውንም ነገር በስሜ ከለመናችሁ እኔ አደርገዋለሁ።

15 “የምትወዱኝ ከሆነ ትእዛዛቴን ትጠብቃላችሁ።+ 16 እኔም አብን እጠይቃለሁ፤ እሱም ለዘላለም ከእናንተ ጋር የሚሆን ሌላ ረዳት* ይሰጣችኋል፤+ 17 እሱም የእውነት መንፈስ ነው፤+ ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ሊቀበለው አይችልም።+ እናንተ ግን አብሯችሁ ስለሚኖርና በውስጣችሁ ስላለ ታውቁታላችሁ። 18 ሐዘን ላይ* ትቻችሁ አልሄድም። ወደ እናንተ እመጣለሁ።+ 19 ከጥቂት ጊዜ በኋላ ዓለም ከቶ አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤+ ምክንያቱም እኔ እኖራለሁ፤ እናንተም ትኖራላችሁ። 20 እኔ ከአባቴ ጋር አንድነት እንዳለኝ፣ እናንተ ከእኔ ጋር አንድነት እንዳላችሁና እኔም ከእናንተ ጋር አንድነት እንዳለኝ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ።+ 21 እኔን የሚወደኝ ትእዛዛቴን የሚቀበልና የሚጠብቅ ነው። እኔን የሚወደኝን ሁሉ ደግሞ አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ፤ ራሴንም እገልጥለታለሁ።”

22 የአስቆሮቱ ሳይሆን ሌላው ይሁዳ+ “ጌታ ሆይ፣ ለዓለም ሳይሆን ለእኛ ራስህን ለመግለጥ ያሰብከው ለምንድን ነው?” አለው።

23 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ማንም ሰው እኔን የሚወደኝ ከሆነ ቃሌን ይጠብቃል፤+ አባቴም ይወደዋል፣ እኛም ወደ እሱ መጥተን መኖሪያችንን ከእሱ ጋር እናደርጋለን።+ 24 እኔን የማይወደኝ ሁሉ ቃሌን አይጠብቅም። ይህ እየሰማችሁት ያለው ቃል ደግሞ የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም።+

25 “አሁን ከእናንተ ጋር እያለሁ እነዚህን ነገሮች ነግሬአችኋለሁ። 26 ሆኖም አብ በስሜ የሚልከው ረዳት* ይኸውም መንፈስ ቅዱስ ሁሉንም ነገር ያስተምራችኋል እንዲሁም የነገርኳችሁን ነገር ሁሉ እንድታስታውሱ ያደርጋችኋል።+ 27 ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ።+ እኔ ሰላም የምሰጣችሁ ዓለም በሚሰጥበት መንገድ አይደለም። ልባችሁ አይረበሽ፤ በፍርሃትም አይዋጥ። 28 ‘እሄዳለሁ ወደ እናንተም ተመልሼ እመጣለሁ’ እንዳልኳችሁ ሰምታችኋል። ብትወዱኝስ ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር፤ ከእኔ አብ ይበልጣልና።+ 29 በመሆኑም በሚፈጸምበት ጊዜ እንድታምኑ ከመፈጸሙ በፊት አሁን ነግሬአችኋለሁ።+ 30 የዚህ ዓለም ገዢ+ እየመጣ ስለሆነ ከዚህ በኋላ ከእናንተ ጋር ብዙ አልነጋገርም፤ እሱም በእኔ ላይ ምንም ኃይል የለውም።+ 31 ይሁን እንጂ እኔ አብን እንደምወድ ዓለም እንዲያውቅ አብ ባዘዘኝ መሠረት+ እየሠራሁ ነው። ተነሱ ከዚህ እንሂድ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ