የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ተሰሎንቄ 5
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

1 ተሰሎንቄ የመጽሐፉ ይዘት

      • የይሖዋ ቀን የሚመጣበት መንገድ (1-5)

        • “ሰላምና ደህንነት ሆነ!” (3)

      • ነቅተን እንኑር፤ የማመዛዘን ችሎታችንን እንጠብቅ (6-11)

      • ማሳሰቢያ (12-24)

      • የስንብት ቃላት (25-28)

1 ተሰሎንቄ 5:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሶፎ 1:14
  • +ማቴ 24:36፤ 2ጴጥ 3:10

1 ተሰሎንቄ 5:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 37:10፤ ኤር 8:11

1 ተሰሎንቄ 5:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 12:36፤ ሮም 13:12፤ ኤፌ 5:8
  • +ዮሐ 8:12፤ ቆላ 1:13፤ 1ጴጥ 2:9

1 ተሰሎንቄ 5:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 24:42
  • +1ጴጥ 5:8
  • +ሮም 13:11

1 ተሰሎንቄ 5:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 13:13

1 ተሰሎንቄ 5:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤፌ 6:14-17

1 ተሰሎንቄ 5:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ተሰ 2:13

1 ተሰሎንቄ 5:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በሞት ብናንቀላፋ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ተሰ 4:16, 17
  • +ሮም 5:8

1 ተሰሎንቄ 5:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ተጽናኑ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 1:11, 12፤ 15:2

1 ተሰሎንቄ 5:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ፊልጵ 2:29, 30፤ 1ጢሞ 5:17፤ ዕብ 13:7
  • +ማር 9:50፤ 2ቆሮ 13:11

1 ተሰሎንቄ 5:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ምከሯቸው።”

  • *

    ወይም “ተስፋ የቆረጡትን።” ቃል በቃል “ትንሽ ነፍስ ያላቸውን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 19:17፤ 2ጢሞ 4:2
  • +1ቆሮ 13:4፤ ገላ 5:22፤ ኤፌ 4:1, 2፤ ቆላ 3:13

1 ተሰሎንቄ 5:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 5:39
  • +ሮም 12:17, 19

1 ተሰሎንቄ 5:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ቆሮ 6:4, 10፤ ፊልጵ 4:4

1 ተሰሎንቄ 5:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 18:1፤ ሮም 12:12

1 ተሰሎንቄ 5:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤፌ 5:20፤ ቆላ 3:17

1 ተሰሎንቄ 5:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤፌ 4:30

1 ተሰሎንቄ 5:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 14:1

1 ተሰሎንቄ 5:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዮሐ 4:1

1 ተሰሎንቄ 5:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዮብ 2:3

1 ተሰሎንቄ 5:23

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሕይወታችሁና።” የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 1:8

1 ተሰሎንቄ 5:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 15:30

1 ተሰሎንቄ 5:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ቆላ 4:16

ተዛማጅ ሐሳብ

1 ተሰ. 5:2ሶፎ 1:14
1 ተሰ. 5:2ማቴ 24:36፤ 2ጴጥ 3:10
1 ተሰ. 5:3መዝ 37:10፤ ኤር 8:11
1 ተሰ. 5:5ዮሐ 12:36፤ ሮም 13:12፤ ኤፌ 5:8
1 ተሰ. 5:5ዮሐ 8:12፤ ቆላ 1:13፤ 1ጴጥ 2:9
1 ተሰ. 5:6ማቴ 24:42
1 ተሰ. 5:61ጴጥ 5:8
1 ተሰ. 5:6ሮም 13:11
1 ተሰ. 5:7ሮም 13:13
1 ተሰ. 5:8ኤፌ 6:14-17
1 ተሰ. 5:92ተሰ 2:13
1 ተሰ. 5:101ተሰ 4:16, 17
1 ተሰ. 5:10ሮም 5:8
1 ተሰ. 5:11ሮም 1:11, 12፤ 15:2
1 ተሰ. 5:13ፊልጵ 2:29, 30፤ 1ጢሞ 5:17፤ ዕብ 13:7
1 ተሰ. 5:13ማር 9:50፤ 2ቆሮ 13:11
1 ተሰ. 5:14ዘሌ 19:17፤ 2ጢሞ 4:2
1 ተሰ. 5:141ቆሮ 13:4፤ ገላ 5:22፤ ኤፌ 4:1, 2፤ ቆላ 3:13
1 ተሰ. 5:15ማቴ 5:39
1 ተሰ. 5:15ሮም 12:17, 19
1 ተሰ. 5:162ቆሮ 6:4, 10፤ ፊልጵ 4:4
1 ተሰ. 5:17ሉቃስ 18:1፤ ሮም 12:12
1 ተሰ. 5:18ኤፌ 5:20፤ ቆላ 3:17
1 ተሰ. 5:19ኤፌ 4:30
1 ተሰ. 5:201ቆሮ 14:1
1 ተሰ. 5:211ዮሐ 4:1
1 ተሰ. 5:22ኢዮብ 2:3
1 ተሰ. 5:231ቆሮ 1:8
1 ተሰ. 5:25ሮም 15:30
1 ተሰ. 5:27ቆላ 4:16
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
1 ተሰሎንቄ 5:1-28

ለተሰሎንቄ ሰዎች የተጻፈ የመጀመሪያው ደብዳቤ

5 እንግዲህ ወንድሞች፣ ጊዜያትንና ወቅቶችን በተመለከተ ምንም ነገር እንዲጻፍላችሁ አያስፈልግም። 2 የይሖዋ* ቀን+ የሚመጣው ሌባ በሌሊት በሚመጣበት መንገድ+ መሆኑን እናንተ ራሳችሁ በሚገባ ታውቃላችሁና። 3 “ሰላምና ደህንነት ሆነ!” ሲሉ ምጥ እርጉዝ ሴትን እንደሚይዛት ያልታሰበ ጥፋት ድንገት ይመጣባቸዋል፤+ ደግሞም በምንም ዓይነት አያመልጡም። 4 እናንተ ግን ወንድሞች፣ በጨለማ ውስጥ ስላልሆናችሁ ሌሊቱ ድንገት እንደሚነጋበት ሌባ፣ ያ ቀን ድንገት አይደርስባችሁም፤ 5 እናንተ ሁላችሁ የብርሃን ልጆችና የቀን ልጆች ናችሁና።+ እኛ የሌሊት ወይም የጨለማ ልጆች አይደለንም።+

6 ስለዚህ ነቅተን እንኑር+ እንዲሁም የማስተዋል ስሜታችንን እንጠብቅ+ እንጂ እንደ ሌሎቹ አናንቀላፋ።+ 7 የሚያንቀላፉ ሰዎች፣ የሚያንቀላፉት በሌሊት ነው፤ የሚሰክሩም ቢሆኑ የሚሰክሩት በሌሊት ነው።+ 8 የቀን ልጆች የሆንነው እኛ ግን የማስተዋል ስሜታችንን እንጠብቅ፤ ደግሞም የእምነትንና የፍቅርን ጥሩር እንልበስ፤ የመዳንንም ተስፋ እንደ ራስ ቁር እንድፋ፤+ 9 ምክንያቱም አምላክ የመረጠን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መዳን እንድናገኝ+ ነው እንጂ ለቁጣ አይደለም። 10 እሱ በሕይወት ብንኖርም ሆነ ብናንቀላፋ* አብረነው እንድንኖር+ ለእኛ ሞቶልናል።+ 11 ስለዚህ አሁን እያደረጋችሁት እንዳለው እርስ በርስ ተበረታቱ* እንዲሁም እርስ በርስ ተናነጹ።+

12 እንግዲህ ወንድሞች፣ በመካከላችሁ በትጋት እየሠሩና በጌታ ሥራ አመራር እየሰጧችሁ ያሉትን እንዲሁም ምክር እየለገሷችሁ ያሉትን እንድታከብሯቸው እንለምናችኋለን፤ 13 በተጨማሪም በሚያከናውኑት ሥራ የተነሳ በፍቅር ለየት ያለ አሳቢነት እንድታሳዩአቸው እንለምናችኋለን።+ እርስ በርሳችሁ ሰላማዊ ግንኙነት ይኑራችሁ።+ 14 በሌላ በኩል ደግሞ ወንድሞች፣ ይህን እናሳስባችኋለን፦ በሥርዓት የማይሄዱትን አስጠንቅቋቸው፤*+ የተጨነቁትን* አጽናኗቸው፤ ደካሞችን ደግፏቸው፤ ሁሉንም በትዕግሥት ያዙ።+ 15 ማንም ሰው በማንም ላይ በክፉ ፋንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፤+ ከዚህ ይልቅ እርስ በርሳችሁም ሆነ ለሌሎች ሰዎች ሁሉ ምንጊዜም መልካም የሆነውን ነገር ለማድረግ ተጣጣሩ።+

16 ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ።+ 17 ዘወትር ጸልዩ።+ 18 ለሁሉም ነገር አመስግኑ።+ አምላክ በክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ ያለው ፈቃድ ይህ ነው። 19 የመንፈስን እሳት አታጥፉ።+ 20 ትንቢቶችን አትናቁ።+ 21 ሁሉንም ነገር መርምሩ፤+ መልካም የሆነውን አጥብቃችሁ ያዙ። 22 ከማንኛውም ዓይነት ክፋት ራቁ።+

23 የሰላም አምላክ ራሱ ሙሉ በሙሉ ይቀድሳችሁ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገኝበት ጊዜ መንፈሳችሁ፣ ነፍሳችሁና* አካላችሁ በማንኛውም ረገድ ጤናማ ይሁን፤ ደግሞም ነቀፋ አይገኝበት።+ 24 የጠራችሁ ታማኝ ነው፤ ይህን በእርግጥ ያደርገዋል።

25 ወንድሞች፣ ስለ እኛ መጸለያችሁን አታቋርጡ።+

26 ወንድሞችን ሁሉ በተቀደሰ አሳሳም ሰላም በሏቸው።

27 ይህ ደብዳቤ ለወንድሞች ሁሉ እንዲነበብ በጌታ አደራ እላችኋለሁ።+

28 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ