የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ተሰሎንቄ 3
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

1 ተሰሎንቄ የመጽሐፉ ይዘት

      • ጳውሎስ በአቴንስ ሆኖ ያሉበትን ሁኔታ ለመስማት እጅግ ጓጓ (1-5)

      • ጢሞቴዎስ የሚያጽናና ዜና ይዞ መጣ (6-10)

      • ለተሰሎንቄ ክርስቲያኖች የቀረበ ጸሎት (11-13)

1 ተሰሎንቄ 3:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ስላልቻልኩ።” እዚህ ላይ ጳውሎስ በብዙ ቁጥር የተጠቀመው ራሱን ለማመልከት ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 17:15

1 ተሰሎንቄ 3:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ከአምላክ ጋር አብሮ የሚሠራ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 16:1, 2፤ ሮም 16:21፤ 1ቆሮ 16:10

1 ተሰሎንቄ 3:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እንዳይዋልል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 14:22፤ 1ቆሮ 4:9፤ 1ጴጥ 2:21

1 ተሰሎንቄ 3:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ተሰ 2:14

1 ተሰሎንቄ 3:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ተሰ 3:2
  • +ማቴ 4:3፤ 2ቆሮ 11:3

1 ተሰሎንቄ 3:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 18:5

1 ተሰሎንቄ 3:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ተሰ 1:4

1 ተሰሎንቄ 3:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በሕይወት እንኖራለን።”

1 ተሰሎንቄ 3:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ተሰ 1:3

1 ተሰሎንቄ 3:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ተሰ 4:9፤ 2ተሰ 1:3

1 ተሰሎንቄ 3:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ተሰ 2:19፤ 5:23፤ 2ተሰ 2:1, 2
  • +1ቆሮ 1:8

ተዛማጅ ሐሳብ

1 ተሰ. 3:1ሥራ 17:15
1 ተሰ. 3:2ሥራ 16:1, 2፤ ሮም 16:21፤ 1ቆሮ 16:10
1 ተሰ. 3:3ሥራ 14:22፤ 1ቆሮ 4:9፤ 1ጴጥ 2:21
1 ተሰ. 3:41ተሰ 2:14
1 ተሰ. 3:51ተሰ 3:2
1 ተሰ. 3:5ማቴ 4:3፤ 2ቆሮ 11:3
1 ተሰ. 3:6ሥራ 18:5
1 ተሰ. 3:72ተሰ 1:4
1 ተሰ. 3:102ተሰ 1:3
1 ተሰ. 3:121ተሰ 4:9፤ 2ተሰ 1:3
1 ተሰ. 3:131ተሰ 2:19፤ 5:23፤ 2ተሰ 2:1, 2
1 ተሰ. 3:131ቆሮ 1:8
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
1 ተሰሎንቄ 3:1-13

ለተሰሎንቄ ሰዎች የተጻፈ የመጀመሪያው ደብዳቤ

3 ስለዚህ ከዚህ በላይ መታገሥ ስላልቻልን* በአቴንስ+ ብቻችንን መቅረት እንደሚሻል ተሰማን፤ 2 በመሆኑም እምነታችሁ ይጠነክር ዘንድ እንዲያጸናችሁ እንዲሁም እንዲያበረታታችሁ ጢሞቴዎስን+ ላክንላችሁ፤ እሱ ወንድማችንና ስለ ክርስቶስ የሚገልጸውን ምሥራች የሚያውጅ የአምላክ አገልጋይ* ነው፤ 3 የላክነውም ማንም በእነዚህ መከራዎች እንዳይናወጥ* ነው። እንዲህ ካሉ መከራዎች ማምለጥ እንደማንችል እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁና።+ 4 አብረናችሁ በነበርንበት ጊዜ መከራ መቀበላችን እንደማይቀር አስቀድመን እንነግራችሁ ነበር፤ ደግሞም እንደምታውቁት ይኸው ነገር ደርሷል።+ 5 ስለዚህ ከዚህ በላይ መታገሥ ባልቻልኩ ጊዜ ስለ ታማኝነታችሁ ለመስማት እሱን ላክሁት፤+ ይህን ያደረግኩት ምናልባት ፈታኙ+ በሆነ መንገድ ፈትኗችሁ ድካማችን ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር ስለሰጋሁ ነው።

6 ይሁንና ጢሞቴዎስ ከእናንተ ዘንድ አሁን ወደ እኛ መጥቶ+ ስለ ታማኝነታችሁና ስለ ፍቅራችሁ ምሥራች አብስሮናል፤ ደግሞም እኛን ሁልጊዜ በመልካም እንደምታስታውሱንና እኛ እናንተን ለማየት እንደምንናፍቅ ሁሉ እናንተም እኛን ለማየት እንደምትናፍቁ ነግሮናል። 7 ወንድሞች፣ በችግራችንና በመከራችን ሁሉ በእናንተና ባሳያችሁት ታማኝነት የተነሳ የተጽናናነው ለዚህ ነው።+ 8 ምክንያቱም ከጌታ ጋር ባላችሁ ዝምድና ጸንታችሁ የምትቆሙ ከሆነ ሕይወታችን ይታደሳል።* 9 በእናንተ የተነሳ በአምላካችን ፊት ለተሰማን ታላቅ ደስታ በአጸፋው ስለ እናንተ ምስጋናችንን ለአምላክ ለመግለጽ ምን ማድረግ እንችላለን? 10 ፊታችሁን ማየትና ከእምነታችሁ የጎደለውን ነገር ማሟላት እንችል ዘንድ አቅማችን በሚፈቅደው መጠን ሌት ተቀን ምልጃ እናቀርባለን።+

11 አሁንም አምላካችንና አባታችን እንዲሁም ጌታችን ኢየሱስ ወደ እናንተ እንድንመጣ መንገዳችንን ያቅኑልን። 12 በተጨማሪም እኛ ለእናንተ ፍቅር እንዳለን ሁሉ እርስ በርስም ሆነ ለሰዎች ሁሉ የምታሳዩትን ፍቅር ጌታ ያብዛላችሁ ብሎም ያትረፍርፍላችሁ፤+ 13 ይህም ጌታችን ኢየሱስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር በሚገኝበት ጊዜ+ በአምላካችንና በአባታችን ፊት ልባችሁን እንዲያጸናና ያላንዳች እንከን ቅዱስ እንዲያደርግ ነው።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ