የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማቴዎስ 28
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ማቴዎስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ኢየሱስ ከሞት ተነሳ (1-10)

      • ወታደሮቹ እንዲዋሹ ጉቦ ተሰጣቸው (11-15)

      • ደቀ መዛሙርት እንዲያደርጉ ተልእኮ ተሰጣቸው (16-20)

ማቴዎስ 28:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ይህ ቀን በአሁኑ ጊዜ እሁድ ተብሎ የሚጠራው ቀን ነው። ለአይሁዳውያን የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ነበር።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 16:1፤ ሉቃስ 24:1, 10፤ ዮሐ 20:1

ማቴዎስ 28:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 16:4, 5፤ ሉቃስ 24:2, 4

ማቴዎስ 28:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 1:10

ማቴዎስ 28:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 16:6

ማቴዎስ 28:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 16:21፤ 17:22, 23፤ 1ቆሮ 15:3, 4

ማቴዎስ 28:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 26:32፤ 28:16፤ ማር 14:28
  • +ማር 16:7

ማቴዎስ 28:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 16:8፤ ሉቃስ 24:9

ማቴዎስ 28:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “እጅ ነሱት።”

ማቴዎስ 28:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 27:65

ማቴዎስ 28:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ብር ከተባለው ማዕድን የተሠራ ሳንቲም።

ማቴዎስ 28:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 27:64

ማቴዎስ 28:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እናሳምነዋለን።”

ማቴዎስ 28:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 26:32፤ 1ቆሮ 15:6

ማቴዎስ 28:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “እጅ ነሱት።”

ማቴዎስ 28:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤፌ 1:20, 21

ማቴዎስ 28:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 1:8፤ ራእይ 14:6
  • +ሥራ 2:38

ማቴዎስ 28:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ዘመኑ።” የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 20:20፤ 1ዮሐ 3:23
  • +ማቴ 13:39

ተዛማጅ ሐሳብ

ማቴ. 28:1ማር 16:1፤ ሉቃስ 24:1, 10፤ ዮሐ 20:1
ማቴ. 28:2ማር 16:4, 5፤ ሉቃስ 24:2, 4
ማቴ. 28:3ሥራ 1:10
ማቴ. 28:5ማር 16:6
ማቴ. 28:6ማቴ 16:21፤ 17:22, 23፤ 1ቆሮ 15:3, 4
ማቴ. 28:7ማቴ 26:32፤ 28:16፤ ማር 14:28
ማቴ. 28:7ማር 16:7
ማቴ. 28:8ማር 16:8፤ ሉቃስ 24:9
ማቴ. 28:11ማቴ 27:65
ማቴ. 28:13ማቴ 27:64
ማቴ. 28:16ማቴ 26:32፤ 1ቆሮ 15:6
ማቴ. 28:18ኤፌ 1:20, 21
ማቴ. 28:19ሥራ 1:8፤ ራእይ 14:6
ማቴ. 28:19ሥራ 2:38
ማቴ. 28:20ሥራ 20:20፤ 1ዮሐ 3:23
ማቴ. 28:20ማቴ 13:39
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ማቴዎስ 28:1-20

የማቴዎስ ወንጌል

28 ከሰንበት ቀን በኋላ በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን* ጎህ ሲቀድ መግደላዊቷ ማርያምና ሌላዋ ማርያም መቃብሩን ለማየት መጡ።+

2 እነሆም የይሖዋ* መልአክ ከሰማይ ስለወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ተከሰተ፤ መልአኩም መጥቶ ድንጋዩን አንከባለለውና በላዩ ተቀመጠ።+ 3 መልኩ እንደ መብረቅ ያበራ ነበር፤ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበር።+ 4 ጠባቂዎቹ እሱን ከመፍራታቸው የተነሳ ተንቀጠቀጡ፤ እንደ በድንም ሆኑ።

5 ሆኖም መልአኩ ሴቶቹን እንዲህ አላቸው፦ “አትፍሩ፤ በእንጨት ላይ የተሰቀለውን ኢየሱስን እየፈለጋችሁ እንደሆነ አውቃለሁ።+ 6 አስቀድሞ እንደተናገረው ከሞት ስለተነሳ እዚህ የለም።+ ኑና አስከሬኑ አርፎበት የነበረውን ስፍራ እዩ። 7 ስለሆነም ፈጥናችሁ ሂዱና ለደቀ መዛሙርቱ ከሞት እንደተነሳ ንገሯቸው፤ ‘እነሆ፣ ቀድሟችሁ ወደ ገሊላ ይሄዳል።+ እዚያም ታዩታላችሁ’ በሏቸው። እነሆ ነግሬአችኋለሁ።”+

8 ስለዚህ ሴቶቹ በፍርሃትና በታላቅ ደስታ ተውጠው ከመታሰቢያ መቃብሩ በፍጥነት በመውጣት ወሬውን ለደቀ መዛሙርቱ ለመንገር እየሮጡ ሄዱ።+ 9 ወዲያውም ኢየሱስ አገኛቸውና “ሰላም ለእናንተ ይሁን!” አላቸው። እነሱም ወደ እሱ ቀረቡና እግሩን ይዘው ሰገዱለት።* 10 ከዚያም ኢየሱስ “አትፍሩ! ሂዱና ወደ ገሊላ እንዲሄዱ ለወንድሞቼ ንገሯቸው፤ እዚያም ያዩኛል” አላቸው።

11 ሴቶቹ በመንገድ ላይ ሳሉ ከጠባቂዎቹ አንዳንዶቹ+ ወደ ከተማ ሄደው የሆነውን ነገር ሁሉ ለካህናት አለቆቹ ነገሯቸው። 12 የካህናት አለቆቹም ከሽማግሌዎቹ ጋር ተሰብስበው ከተማከሩ በኋላ ለወታደሮቹ በርከት ያሉ የብር ሳንቲሞች* በመስጠት 13 እንዲህ አሏቸው፦ “‘ሌሊት ተኝተን ሳለ ደቀ መዛሙርቱ መጥተው አስከሬኑን ሰረቁት’ በሉ።+ 14 አትጨነቁ፤ ወሬው ወደ አገረ ገዢው ጆሮ ከደረሰ ሁኔታውን እናስረዳዋለን።”* 15 እነሱም የብር ሳንቲሞቹን ተቀብለው እንደታዘዙት አደረጉ፤ ይህም ታሪክ እስከ ዛሬ ድረስ በአይሁዳውያን ዘንድ በስፋት ይወራል።

16 ይሁንና የኢየሱስ 11 ደቀ መዛሙርት ከእሱ ጋር ለመገናኘት በገሊላ ወደሚገኘው፣ እሱ ወደነገራቸው ተራራ ሄዱ።+ 17 ባዩትም ጊዜ ሰገዱለት፤* አንዳንዶች ግን ተጠራጠሩ። 18 ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ አላቸው፦ “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል።+ 19 ስለዚህ ሂዱና ከሁሉም ብሔራት ሰዎችን ደቀ መዛሙርት አድርጉ፤+ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፣+ 20 ያዘዝኳችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው።+ እነሆም እኔ እስከ ሥርዓቱ* መደምደሚያ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ