መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በባለ አውታር መሣሪያዎች የሚታጀብ። ማስኪል።* የዳዊት መዝሙር።
2 ትኩረት ስጠኝ፤ መልስልኝም።+
እነሱ በእኔ ላይ መከራ ይከምራሉና፤
በቁጣም ተሞልተው በጥላቻ ዓይን ያዩኛል።+
5 ፍርሃት አደረብኝ፤ ደግሞም ተንቀጠቀጥኩ፤
ብርክም ያዘኝ።
6 እኔም እንዲህ እላለሁ፦ “ምነው እንደ ርግብ ክንፍ በኖረኝ!
በርሬ ሄጄ ያለስጋት በኖርኩ ነበር።
7 እነሆ፣ ወደ ሩቅ ቦታ በበረርኩ፣+
በምድረ በዳም በቆየሁ ነበር።+ (ሴላ)
8 ከአውሎ ነፋስና ከውሽንፍር ሸሽቼ
መጠለያ ወደማገኝበት ቦታ ፈጥኜ በሄድኩ ነበር።”
9 ይሖዋ ሆይ፣ ግራ አጋባቸው፤ ዕቅዳቸውንም አጨናግፍ፤+
በከተማዋ ውስጥ ዓመፅና ብጥብጥ አይቻለሁና።
10 ቅጥሮቿ ላይ ወጥተው ቀንና ሌሊት ይዞራሉ፤
በውስጧም ተንኮልና መከራ አለ።+
11 ጥፋት በመካከሏ አለ፤
ጭቆናና ማታለል ከአደባባይዋ ፈጽሞ አይጠፉም።+
12 የሚዘልፈኝ ጠላት አይደለምና፤+
ቢሆንማ ኖሮ በቻልኩት ነበር።
በእኔ ላይ የተነሳው ባላጋራ አይደለም፤
ቢሆንማ ኖሮ ከእሱ በተሸሸግኩ ነበር።
14 በመካከላችን የጠበቀ ወዳጅነት ነበር፤
ከብዙ ሕዝብ ጋር ወደ አምላክ ቤት አብረን እንሄድ ነበር።
15 ጥፋት በድንገት ይምጣባቸው!+
በሕይወት ሳሉ ወደ መቃብር* ይውረዱ፤
ክፋት በመካከላቸውና በውስጣቸው ያድራልና።
16 እኔ በበኩሌ አምላክን እጣራለሁ፤
ይሖዋም ያድነኛል።+
አምላክን የማይፈሩት እነዚህ ሰዎች+
ለመለወጥ ፈቃደኞች አይደሉም።
21 የሚናገራቸው ቃላት ከቅቤ ይልቅ የለሰለሱ ናቸው፤+
በልቡ ውስጥ ግን ጠብ አለ።
ቃሎቹ ከዘይት ይልቅ የለሰለሱ ቢሆኑም
እንደተመዘዘ ሰይፍ ናቸው።+
23 አምላክ ሆይ፣ አንተ ግን ወደ ጥልቅ ጉድጓድ ታወርዳቸዋለህ።+
የደም ዕዳ ያለባቸውና አታላይ የሆኑ ሰዎች የዕድሜያቸውን ግማሽ እንኳ አይኖሩም።+
እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ።