አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ዕዝራ የመጽሐፉ ይዘት ዕዝራ የመጽሐፉ ይዘት 1 ንጉሥ ቂሮስ ቤተ መቅደሱ ዳግመኛ እንዲገነባ አዋጅ አስነገረ (1-4) በግዞት የተወሰዱት እስራኤላውያን ወደ አገራቸው ለመመለስ ተዘጋጁ (5-11) 2 ወደ አገራቸው የተመለሱት ግዞተኞች ዝርዝር (1-67) የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች (43-54) የሰለሞን አገልጋዮች ወንዶች ልጆች (55-57) ለቤተ መቅደሱ የቀረቡ የፈቃደኝነት መባዎች (68-70) 3 መሠዊያው ዳግመኛ ተገነባ፤ መሥዋዕቶች ቀረቡ (1-6) ቤተ መቅደሱን የመገንባቱ ሥራ ተጀመረ (7-9) የቤተ መቅደሱ መሠረት ተጣለ (10-13) 4 ቤተ መቅደሱን የመገንባቱ ሥራ ተቃውሞ ገጠመው (1-6) ተቃዋሚዎች ለንጉሥ አርጤክስስ ቅሬታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ጻፉ (7-16) አርጤክስስ የሰጠው ምላሽ (17-22) የቤተ መቅደሱ ግንባታ ተቋረጠ (23-24) 5 አይሁዳውያን ዳግመኛ ቤተ መቅደሱን መገንባት ጀመሩ (1-5) ታተናይ ለንጉሥ ዳርዮስ የላከው ደብዳቤ (6-17) 6 ዳርዮስ ያካሄደው ምርመራና ያወጣው አዋጅ (1-12) ቤተ መቅደሱ ተሠርቶ ተጠናቀቀ፤ ከዚያም ተመረቀ (13-18) የፋሲካ በዓል ተከበረ (19-22) 7 ዕዝራ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ (1-10) አርጤክስስ ለዕዝራ የጻፈው ደብዳቤ (11-26) ዕዝራ ይሖዋን አወደሰ (27,28) 8 ከዕዝራ ጋር የተመለሱት ሰዎች ዝርዝር (1-14) ለጉዞው የተደረገ ዝግጅት (15-30) ከባቢሎን ተነስተው ኢየሩሳሌም ደረሱ (31-36) 9 እስራኤላውያን ከሌሎች ብሔራት ጋር መጋባታቸው (1-4) ዕዝራ ያቀረበው የንስሐ ጸሎት (5-15) 10 ባዕዳን ሚስቶችን ለማሰናበት ቃል ኪዳን ገቡ (1-14) ባዕዳን ሚስቶቻቸውን አሰናበቱ (15-44)