አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ኢሳይያስ የመጽሐፉ ይዘት ኢሳይያስ የመጽሐፉ ይዘት 1 አንድ አባትና ዓመፀኛ ልጆቹ (1-9) ይሖዋ ለታይታ ተብሎ የሚቀርብን አምልኮ ይጠላል (10-17) “የተፈጠረውን ችግር ተወያይተን እንፍታ” (18-20) ጽዮን ዳግመኛ የታመነች ከተማ ትሆናለች (21-31) 2 የይሖዋ ተራራ ከፍ ከፍ ይላል (1-5) ሰይፋቸውን ማረሻ ያደርጋሉ (4) በይሖዋ ቀን ትዕቢተኞች ይዋረዳሉ (6-22) 3 የይሁዳ መሪዎች ሕዝቡን ያስታሉ (1-15) እየተጣቀሱ የሚሄዱት የጽዮን ሴቶች ተፈረደባቸው (16-26) 4 ሰባት ሴቶች ለአንድ ወንድ (1) ይሖዋ እንዲያቆጠቁጥ ያደረገው ተክል ክብር የተላበሰ ይሆናል (2-6) 5 ስለ ይሖዋ የወይን እርሻ የተዘመረ መዝሙር (1-7) በይሖዋ የወይን እርሻ ላይ የተነገረ ወዮታ (8-24) በሕዝቡ ላይ የነደደው የአምላክ ቁጣ (25-30) 6 ይሖዋ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ሆኖ በራእይ ታየ (1-4) “ይሖዋ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ነው” (3) የኢሳይያስ ከንፈሮች ነጹ (5-7) ኢሳይያስ ተልእኮ ተሰጠው (8-10) “እነሆኝ! እኔን ላከኝ!” (8) “ይሖዋ ሆይ፣ እስከ መቼ ነው?” (11-13) 7 ለንጉሥ አካዝ የተላከ መልእክት (1-9) ሸአርያሹብ (3) አማኑኤልን በተመለከተ የተሰጠ ምልክት (10-17) ከዳተኛ መሆን የሚያስከትለው መዘዝ (18-25) 8 የአሦር ወረራ (1-8) ማኸር-ሻላል-ሃሽ-ባዝ (1-4) አትፍሩ፤ “አምላክ ከእኛ ጋር ነው” (9-17) ኢሳይያስና ልጆቹ ምልክት ሆነው ያገለግላሉ (18) አጋንንትን ከመጠየቅ ይልቅ ሕጉን ተመልከቱ (19-22) 9 በገሊላ ምድር ላይ ታላቅ ብርሃን ወጣ (1-7) “የሰላም መስፍን” ተወለደ (6,7) በእስራኤል ላይ የተዘረጋው የአምላክ እጅ (8-21) 10 በእስራኤል ላይ የተዘረጋው የአምላክ እጅ (1-4) አሦር፣ የአምላክ የቁጣ በትር (5-11) በአሦር ላይ የሚደርስ ቅጣት (12-19) ከያዕቆብ ቤት የሚተርፉት ይመለሳሉ (20-27) አምላክ በአሦር ላይ ይፈርዳል (28-34) 11 የእሴይ ቀንበጥ የጽድቅ አገዛዝ (1-10) ተኩላ ከበግ ጠቦት ጋር ይቀመጣል (6) ምድር በይሖዋ እውቀት ትሞላለች (9) የሕዝቡ ቀሪዎች ይመለሳሉ (11-16) 12 የምስጋና መዝሙር (1-6) ‘ያህ ይሖዋ ብርታቴ ነው’ (2) 13 በባቢሎን ላይ የተላለፈ ፍርድ (1-22) “የይሖዋ ቀን ቀርቧል” (6) ሜዶናውያን ባቢሎንን ይገለብጣሉ (17) ባቢሎን ከዚያ በኋላ የሚቀመጥባት አይኖርም (20) 14 እስራኤላውያን በገዛ ምድራቸው ላይ ይሰፍራሉ (1, 2) በባቢሎን ንጉሥ ላይ ትሳለቃለህ (3-23) የሚያበራው ኮከብ ከሰማይ ወደቀ (12) የይሖዋ እጅ አሦራዊውን ያደቃል (24-27) በፍልስጤም ላይ የተላለፈ ፍርድ (28-32) 15 በሞዓብ ላይ የተላለፈ ፍርድ (1-9) 16 ለሞዓብ የተነገረው የፍርድ መልእክት ቀጣይ ክፍል (1-14) 17 በደማስቆ ላይ የተላለፈ ፍርድ (1-11) ይሖዋ ብሔራትን ይገሥጻቸዋል (12-14) 18 ለኢትዮጵያ የተነገረ የማስጠንቀቂያ መልእክት (1-7) 19 በግብፅ ላይ የተላለፈ ፍርድ (1-15) ይሖዋ በግብፃውያን ዘንድ የታወቀ ይሆናል (16-25) በግብፅ ምድር ለይሖዋ መሠዊያ ይሠራል (19) 20 ለግብፅና ለኢትዮጵያ የተሰጠ የማስጠንቀቂያ ምልክት (1-6) 21 በምድረ በዳው ባሕር ላይ የተላለፈ ፍርድ (1-10) “በመጠበቂያው ግንብ ላይ ቆሜአለሁ” (8) “ባቢሎን ወደቀች!” (9) በዱማና በበረሃማው ሜዳ ላይ የተላለፈ ፍርድ (11-17) “ጠባቂ ሆይ፣ ስለ ሌሊቱ ምን ትላለህ?” (11) 22 ስለ ራእይ ሸለቆ የተነገረ የፍርድ መልእክት (1-14) መጋቢው ሸብና በኤልያቄም ተተካ (15-25) ምሳሌያዊው ማንጠልጠያ (23-25) 23 ስለ ጢሮስ የተነገረ የፍርድ መልእክት (1-18) 24 ይሖዋ አገሪቱን ወና ያደርጋታል (1-23) ይሖዋ በጽዮን ነግሦአል (23) 25 የአምላክ ሕዝብ የሚያገኘው የተትረፈረፈ በረከት (1-12) ይሖዋ ጥሩ የወይን ጠጅ የሚቀርብበት ታላቅ ግብዣ ያዘጋጃል (6) “ሞትን ለዘላለም ይውጣል” (8) 26 በይሖዋ ስለ መታመንና ስለ መዳን የተዘመረ መዝሙር (1-21) “ያህ ይሖዋ የዘላለም ዓለት ነው” (4) የምድር ነዋሪዎች ስለ ጽድቅ ይማራሉ (9) “ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ” (19) ወደ ውስጠኛው ክፍልህ ገብተህ ተሸሸግ (20) 27 ይሖዋ ሌዋታንን ይገድለዋል (1) በወይን እርሻ ለተመሰለችው እስራኤል የተዘመረ መዝሙር (2-13) 28 የኤፍሬም ሰካራሞች ወዮላቸው! (1-6) የይሁዳ ካህናትና ነቢያት ይንገዳገዳሉ (7-13) “ከሞት ጋር ቃል ኪዳን ገብተናል” (14-22) በጽዮን የተቀመጠ ክቡር የማዕዘን ድንጋይ (16) ይሖዋ ያከናወነው እንግዳ የሆነ ተግባር (21) የይሖዋን ተግሣጽ የሚያሳይ ምሳሌ (23-29) 29 ለአርዔል ወዮላት! (1-16) ‘በከንፈሩ ያከብረኛል’ (13) መስማት የተሳናቸው ይሰማሉ፤ ዓይነ ስውራኑም ያያሉ (17-24) 30 ግብፅ የምትሰጠው እርዳታ ዋጋ የለውም (1-7) ሕዝቡ ትንቢታዊ መልእክቱን ንቀዋል (8-14) “ተማምናችሁ በመኖር ብርቱ መሆናችሁን ታሳያላችሁ” (15-17) ይሖዋ ለሕዝቡ ሞገስ ያሳያል (18-26) ታላቅ አስተማሪ የሆነው ይሖዋ (20) “መንገዱ ይህ ነው” (21) ይሖዋ በአሦር ላይ ፍርዱን ያስፈጽማል (27-33) 31 አስተማማኝ እርዳታ የሚገኘው ከሰው ሳይሆን ከአምላክ ነው (1-9) የግብፅ ፈረሶች ሥጋ ናቸው (3) 32 ንጉሥና ገዢዎች ለፍትሕ ይገዛሉ (1-8) ደንታ ቢስ ሴቶች ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው (9-14) መንፈስ ሲፈስ የሚገኝ በረከት (15-20) 33 ጻድቃን የሚያገኙት ፍትሕና የሚጠብቃቸው ተስፋ (1-24) ይሖዋ ዳኛ፣ ሕግ ሰጪና ንጉሥ ነው (22) “ታምሜአለሁ” የሚል አይኖርም (24) 34 ይሖዋ በብሔራት ላይ የሚወስደው የበቀል እርምጃ (1-4) ኤዶም ትወድማለች (5-17) 35 ምድር ገነት ትሆናለች (1-7) ዓይነ ስውራን ያያሉ፤ መስማት የተሳናቸውም ይሰማሉ (5) የተዋጁት የሚጓዙበት “የቅድስና ጎዳና” (8-10) 36 ሰናክሬም ይሁዳን ወረረ (1-3) ራብሻቁ በይሖዋ ላይ ተሳለቀ (4-22) 37 ሕዝቅያስ በኢሳይያስ በኩል የአምላክን እርዳታ ጠየቀ (1-7) ሰናክሬም በኢየሩሳሌም ላይ ዛተ (8-13) የሕዝቅያስ ጸሎት (14-20) ኢሳይያስ አምላክ የሰጠውን መልስ ተናገረ (21-35) አንድ መልአክ 185,000 አሦራውያንን ገደለ (36-38) 38 ሕዝቅያስ ከሕመሙ አገገመ (1-22) የምስጋና መዝሙር (10-20) 39 ከባቢሎን የመጡ መልእክተኞች (1-8) 40 ለአምላክ ሕዝብ የተሰጠ ማጽናኛ (1-11) በምድረ በዳ የተሰማ ድምፅ (3-5) የአምላክ ታላቅነት (12-31) “ብሔራት በገንቦ ውስጥ እንዳለች ጠብታ ናቸው” (15) ‘አምላክ ክብ ከሆነችው ምድር በላይ ይኖራል’ (22) ከዋክብትን ሁሉ በየስማቸው ይጠራቸዋል (26) አምላክ ፈጽሞ አይደክምም (28) ይሖዋን ተስፋ ማድረግ ኃይል ያድሳል (29-31) 41 ከፀሐይ መውጫ የመጣ ድል አድራጊ (1-7) እስራኤል የአምላክ አገልጋይ እንዲሆን ተመረጠ (8-20) ‘ወዳጄ አብርሃም’ (8) ለአማልክት የቀረበ ፈተና (21-29) 42 የአምላክ አገልጋይ የተሰጠው ተልእኮ (1-9) ‘ስሜ ይሖዋ ነው’ (8) ለይሖዋ የቀረበ አዲስ የውዳሴ መዝሙር (10-17) እስራኤል ዕውርና ደንቆሮ ነው (18-25) 43 ይሖዋ ሕዝቡን መልሶ ሰበሰበ (1-7) አማልክት የገጠማቸው ግድድር (8-13) “እናንተ ምሥክሮቼ ናችሁ” (10, 12) ከባቢሎን ነፃ መውጣት (14-21) “ጉዳያችንን አቅርበን እንሟገት” (22-28) 44 አምላክ የመረጠው ሕዝብ የሚያገኘው በረከት (1-5) ከይሖዋ በቀር ሌላ አምላክ የለም (6-8) ሰው ሠራሽ ጣዖታት ከንቱ ናቸው (9-20) እስራኤልን የሚቤዠው ይሖዋ (21-23) በቂሮስ አማካኝነት ቀድሞ ወደነበሩበት ሁኔታ ይመለሳሉ (24-28) 45 ቂሮስ ባቢሎንን ድል እንዲያደርግ ተቀብቷል (1-8) ሸክላ ከሠሪው ጋር ሙግት አይገጥምም (9-13) ሌሎች ብሔራት ለእስራኤል እውቅና ይሰጣሉ (14-17) የአምላክ የፍጥረት ሥራም ሆነ የሚናገረው ትንቢት አስተማማኝ ነው (18-25) ምድር የተፈጠረችው መኖሪያ እንድትሆን ነው (18) 46 በባቢሎን ጣዖታትና በእስራኤል አምላክ መካከል ያለው ልዩነት (1-13) ይሖዋ ስለ ወደፊቱ ጊዜ አስቀድሞ ይናገራል (10) ከፀሐይ መውጫ የሚመጣ አዳኝ አሞራ (11) 47 የባቢሎን መውደቅ (1-15) ኮከብ ቆጣሪዎች ተጋለጡ (13-15) 48 እስራኤል ተወቀሰች፤ ደግሞም ጠራች (1-11) ይሖዋ በባቢሎን ላይ እርምጃ ይወስዳል (12-16ሀ) የአምላክ ትምህርት ጠቃሚ ነው (16ለ-19) “ከባቢሎን ውጡ!” (20-22) 49 ለይሖዋ አገልጋይ የተሰጠ ሥራ (1-12) “ለብሔራት ብርሃን” (6) ለእስራኤል የተነገረ ማጽናኛ (13-26) 50 የእስራኤል ኃጢአት ያስከተለው ችግር (1-3) የይሖዋ ታዛዥ አገልጋይ (4-11) ከአምላክ የተማሩ ሰዎች አንደበትና ጆሮ (4) 51 ጽዮን ተመልሳ እንደ ኤደን የአትክልት ስፍራ ትሆናለች (1-8) ጽዮንን የሠራው ኃያል አምላክ የተናገረው ማጽናኛ (9-16) የይሖዋ የቁጣ ጽዋ (17-23) 52 “ጽዮን ሆይ፣ ተነሺ!” (1-12) ምሥራች ይዘው የሚመጡ ያማሩ እግሮች (7) የጽዮን ጠባቂዎች በአንድነት እልል ይላሉ (8) የይሖዋን ዕቃ የሚሸከሙ ንጹሕ መሆን ይጠበቅባቸዋል (11) የይሖዋ አገልጋይ ከፍ ከፍ ይላል (13-15) ከሰው ልጆች ሁሉ ይልቅ ተጎሳቆለ (14) 53 የይሖዋ አገልጋይ የደረሰበት ሥቃይ፣ አሟሟቱና የተቀበረበት ሁኔታ (1-12) ሰዎች ናቁት፤ ደግሞም አገለሉት (3) ሕመማችንንና ሥቃያችንን ተሸከመ (4) “እንደ በግ ለመታረድ ተነዳ” (7) የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ (12) 54 መሃን የሆነችው ጽዮን ብዙ ልጆች ትወልዳለች (1-17) የጽዮን ባል የሆነው ይሖዋ (5) የጽዮን ልጆች ከይሖዋ የተማሩ ይሆናሉ (13) ጽዮንን ለማጥቃት የተሠራ መሣሪያ ይከሽፋል (17) 55 በነፃ እንዲበሉና እንዲጠጡ የቀረበ ግብዣ (1-5) ይሖዋንና አስተማማኝ የሆነውን ቃሉን ፈልጉ (6-13) የአምላክ መንገድ ከሰው መንገድ ከፍ ያለ ነው (8, 9) የአምላክ ቃል መፈጸሙ የተረጋገጠ ነው (10, 11) 56 የባዕድ አገር ሰውና ጃንደረባ የሚያገኙት በረከት (1-8) ለሰው ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት (7) ዕውር ጠባቂዎች፤ መናገር የማይችሉ ውሾች (9-12) 57 ጻድቅ ሰውም ሆነ ታማኝ ሰዎች ይሞታሉ (1, 2) እስራኤል የፈጸመችው መንፈሳዊ ምንዝር ተጋለጠ (3-13) ለችግረኞች የተነገረ ማጽናኛ (14-21) ክፉዎች የሚናወጥ ባሕር ናቸው (20) “ክፉዎች ሰላም የላቸውም” (21) 58 እውነተኛ ጾምና የይስሙላ ጾም (1-12) ሰንበትን በማክበር መደሰት (13, 14) 59 እስራኤል የፈጸመችው ኃጢአት ከአምላክ አራቃት (1-8) የኃጢአት ኑዛዜ (9-15ሀ) ይሖዋ ንስሐ ለገቡት ሲል ጣልቃ ገባ (15ለ-21) 60 የይሖዋ ክብር በጽዮን ላይ ያበራል (1-22) ‘ወደ ቤታቸው እንደሚተሙ ርግቦች’ (8) በመዳብ ፋንታ ወርቅ (17) ‘ጥቂት የሆነው ሺህ ይሆናል’ (22) 61 “ምሥራች እንድናገር ቀብቶኛል” (1-11) ‘ይሖዋ በጎ ፈቃድ የሚያሳይበት ዓመት’ (2) “ትላልቅ የጽድቅ ዛፎች” (3) የባዕድ አገር ሰዎች እርዳታ ያበረክታሉ (5) “የይሖዋ ካህናት” (6) 62 የጽዮን አዲስ ስም (1-12) 63 ይሖዋ በብሔራት ላይ የሚወስደው የበቀል እርምጃ (1-6) የይሖዋ ታማኝ ፍቅር (7-14) የንስሐ ጸሎት (15-19) 64 የንስሐ ጸሎት ቀጣይ ክፍል (1-12) ይሖዋ ሠሪያችን ነው (8) 65 ይሖዋ በጣዖት አምላኪዎች ላይ ያስተላለፈው ፍርድ (1-16) የመልካም ዕድልና የዕጣ አማልክት (11) “አገልጋዮቼ ይበላሉ” (13) አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር (17-25) ቤቶችን ይሠራሉ፤ ወይንንም ይተክላሉ (21) በከንቱ አይለፉም (23) 66 እውነተኛና ሐሰተኛ አምልኮ (1-6) ጽዮንና ወንዶች ልጆቿ (7-17) ሰዎች ለአምልኮ በኢየሩሳሌም ይሰበሰባሉ (18-24)