አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት 1 ኤርምያስ ነቢይ ሆኖ ተሾመ (1-10) የአልሞንድ ዛፍ ራእይ (11, 12) የተጣደው ድስት ራእይ (13-16) ኤርምያስ ተልእኮውን እንዲፈጽም ማበረታቻ ተሰጠው (17-19) 2 እስራኤል ይሖዋን ትታ ሌሎች አማልክትን ተከተለች (1-37) እስራኤል በባዕድ የወይን ተክል ተመሰለች (21) ልብሶቿ በደም ቆሽሸዋል (34) 3 እስራኤል የፈጸመችው ታላቅ ክህደት (1-5) እስራኤልና ይሁዳ አመነዘሩ (6-11) ንስሐ እንዲገቡ የቀረበ ጥሪ (12-25) 4 ንስሐ መግባት በረከት ያስገኛል (1-4) ከሰሜን ጥፋት ይመጣል (5-18) ኤርምያስ የተሰማው ሐዘን (19-31) 5 ሕዝቡ የይሖዋን ተግሣጽ አልሰማም (1-13) ጥፋት ቢደርስባቸውም ሙሉ በሙሉ አልጠፉም (14-19) ይሖዋ ሕዝቡን ተጠያቂ አደረገ (20-31) 6 ኢየሩሳሌም የምትከበብበት ጊዜ ተቃረበ (1-9) የይሖዋ ቁጣ በኢየሩሳሌም ላይ ነደደ (10-21) ‘ሰላም ሳይኖር “ሰላም ነው!” ይላሉ’ (14) ከሰሜን ምድር ጨካኝ ወራሪዎች ይመጣሉ (22-26) ኤርምያስ ብረትን እንደሚፈትን ሰው ሆኖ ያገለግላል (27-30) 7 “‘የይሖዋ ቤተ መቅደስ ነው!’ እያላችሁ በአሳሳች ቃል አትታመኑ” (1-11) ቤተ መቅደሱ እንደ ሴሎ ይሆናል (12-15) የሐሰት አምልኮ ተወገዘ (16-34) ‘የሰማይን ንግሥት’ አመለኩ (18) በሂኖም ልጆቻቸውን ሠዉ (31) 8 ሕዝቡ ብዙኃኑ የሚከተለውን መንገድ ተከተለ (1-7) የይሖዋን ቃል ንቀው ምን ዓይነት ጥበብ ሊኖራቸው ይችላል? (8-17) ኤርምያስ በይሁዳ ላይ በደረሰው ውድቀት የተነሳ አዘነ (18-22) “በጊልያድ የበለሳን ዘይት የለም?” (22) 9 ኤርምያስ የተሰማው ጥልቅ ሐዘን (1-3ሀ) ይሖዋ ይሁዳን ተጠያቂ አደረገ (3ለ-16) ከጽዮን የተሰማ የሐዘን እንጉርጉሮ (17-22) “እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ በማወቁ ይኩራራ” (23-26) 10 የብሔራት አማልክትና ሕያው የሆነው አምላክ (1-16) የሚጠፉበትና የሚማረኩበት ጊዜ ተቃረበ (17, 18) ኤርምያስ እጅግ አዘነ (19-22) ነቢዩ ያቀረበው ጸሎት (23-25) ሰው አካሄዱን አቃንቶ መምራት አይችልም (23) 11 ይሁዳ ከአምላክ ጋር የገባችውን ቃል ኪዳን አፈረሰች (1-17) “አማልክትህ የከተሞችህን ያህል በዝተዋል” (13) ኤርምያስ ለመታረድ እንደሚነዳ በግ ሆነ (18-20) ኤርምያስ ከአገሩ ሰዎች ተቃውሞ ገጠመው (21-23) 12 ኤርምያስ አቤቱታ አቀረበ (1-4) ይሖዋ የሰጠው መልስ (5-17) 13 ከተልባ እግር የተሠራው ቀበቶ ተበላሸ (1-11) በወይን ጠጅ የተሞሉ እንስራዎች ይሰባበራሉ (12-14) ይሁዳ ልትሻሻል ባለመቻሏ በምርኮ ትወሰዳለች (15-27) ‘ኢትዮጵያዊ መልኩን መለወጥ ይችላል?’ (23) 14 ድርቅ፣ ረሃብና ሰይፍ (1-12) ሐሰተኛ ነቢያት ተወገዙ (13-18) ኤርምያስ ሕዝቡ ኃጢአት መሥራቱን አምኖ ተቀበለ (19-22) 15 ይሖዋ ፍርዱን አይለውጥም (1-9) የኤርምያስ ስሞታ (10) ይሖዋ የሰጠው መልስ (11-14) ኤርምያስ ያቀረበው ጸሎት (15-18) የአምላክን ቃል መብላት የሚያስገኘው ደስታ (16) ይሖዋ ኤርምያስን አበረታታው (19-21) 16 ኤርምያስ እንዳያገባ፣ እንዳያለቅስና ወደ ግብዣ እንዳይሄድ ተነገረው (1-9) ከተቀጡ በኋላ ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው ይመለሳሉ (10-21) 17 የይሁዳ ኃጢአት በጽላት ላይ ተቀርጿል (1-4) በይሖዋ መታመን የሚያስገኘው በረከት (5-8) ልብ ከዳተኛ ነው (9-11) የእስራኤል ተስፋ የሆነው ይሖዋ (12, 13) ኤርምያስ ያቀረበው ጸሎት (14-18) “የሰንበትን ቀን ቀድሱ” (19-27) 18 በሸክላ ሠሪው እጅ ውስጥ ያለ ጭቃ (1-12) ይሖዋ ለእስራኤል ጀርባውን ሰጠ (13-17) በኤርምያስ ላይ የተጠነሰሰ ሴራና እሱ ያቀረበው ልመና (18-23) 19 ኤርምያስ ገንቦውን እንዲሰብር ተነገረው (1-15) ልጆቻቸውን ለባአል ሠዉ (5) 20 ጳስኮር ኤርምያስን መታው (1-6) ኤርምያስ መስበኩን ሊያቆም አልቻለም (7-13) የአምላክ ቃል እንደሚነድ እሳት ነው (9) ይሖዋ እንደ አስፈሪ ተዋጊ ነው (11) ኤርምያስ ያሰማው እሮሮ (14-18) 21 ይሖዋ ሴዴቅያስ ያቀረበውን ልመና አልሰማም (1-7) ‘የሕይወት መንገድና የሞት መንገድ’ (8-14) 22 በክፉ ነገሥታት ላይ የተላለፈ የፍርድ መልእክት (1-30) ስለ ሻሉም የተነገረ ቃል (10-12) ስለ ኢዮዓቄም የተነገረ ቃል (13-23) ስለ ኮንያሁ የተነገረ ቃል (24-30) 23 መልካምና ክፉ እረኞች (1-4) ‘በጻድቁ ቀንበጥ’ ሥር ያለስጋት መኖር (5-8) ሐሰተኛ ነቢያት ተወገዙ (9-32) “የይሖዋ ሸክም” (33-40) 24 ጥሩ በለሶችና መጥፎ በለሶች (1-10) 25 “ይሖዋ ከብሔራት ጋር ሙግት አለው” (1-38) ብሔራት ባቢሎንን 70 ዓመት ያገለግሏታል (11) የአምላክ ቁጣ ወይን ጠጅ ያለበት ጽዋ (15) “ጥፋት ብሔራትን አንድ በአንድ ያዳርሳል” (32) “ይሖዋ የገደላቸው” (33) 26 ኤርምያስን ‘እንገድልሃለን’ ብለው ዛቱበት (1-15) ኤርምያስ ከሞት ተረፈ (16-19) የሚክያስ ትንቢት ተጠቀሰ (18) ነቢዩ ዑሪያህ (20-24) 27 የባቢሎን ቀንበር (1-11) ሴዴቅያስ ለባቢሎን እንዲገዛ ተነገረው (12-22) 28 ኤርምያስና ሐሰተኛው ነቢይ ሃናንያህ (1-17) 29 ኤርምያስ በግዞት ወደ ባቢሎን ለተወሰዱት ሰዎች የጻፈው ደብዳቤ (1-23) እስራኤላውያን ከ70 ዓመት በኋላ ይመለሳሉ (10) ለሸማያህ የተላለፈ መልእክት (24-32) 30 ወደ ቀድሞው ሁኔታ እንደሚመለሱና እንደሚፈወሱ የተነገረ ቃል (1-24) 31 የእስራኤል ቀሪዎች ዳግመኛ በምድሪቱ ላይ ይሰፍራሉ (1-30) ‘ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች’ (15) “አዲስ ቃል ኪዳን” (31-40) 32 ኤርምያስ መሬት ገዛ (1-15) ኤርምያስ ያቀረበው ጸሎት (16-25) ይሖዋ የሰጠው መልስ (26-44) 33 ወደ ቀድሞው ሁኔታ እንደሚመለሱ ቃል ተገባላቸው (1-13) ‘በጻድቁ ቀንበጥ’ ሥር ያለስጋት መኖር (14-16) ከዳዊትና ከካህናቱ ጋር የተገባ ቃል ኪዳን (17-26) የቀንና የሌሊት ቃል ኪዳን (20) 34 ለሴዴቅያስ የተነገረ የፍርድ መልእክት (1-7) ለባሪያዎች ነፃነት አስገኝቶ የነበረው ቃል ኪዳን ፈረሰ (8-22) 35 ሬካባውያን የተዉት ግሩም የታዛዥነት ምሳሌ (1-19) 36 ኤርምያስ ባሮክን በቃሉ አስጻፈው (1-7) ባሮክ ከጥቅልሉ ላይ ጮክ ብሎ አነበበ (8-19) ኢዮዓቄም ጥቅልሉን አቃጠለው (20-26) መልእክቱ በአዲስ ጥቅልል ላይ በድጋሚ ተጻፈ (27-32) 37 ከለዳውያን ለጊዜው ኢየሩሳሌምን ለቀው ሄዱ (1-10) ኤርምያስ ታሰረ (11-16) ሴዴቅያስ ከኤርምያስ ጋር ተገናኘ (17-21) ኤርምያስ ዳቦ ይሰጠው ነበር (21) 38 ኤርምያስ ጉድጓድ ውስጥ ተጣለ (1-6) ኤቤድሜሌክ ኤርምያስን አዳነው (7-13) ኤርምያስ፣ እጁን እንዲሰጥ ሴዴቅያስን አሳሰበው (14-28) 39 በኢየሩሳሌም ላይ የደረሰው ጥፋት (1-10) ሴዴቅያስ ሲሸሽ ተያዘ (4-7) ኤርምያስ ጥበቃ አገኘ (11-14) ኤቤድሜሌክ ሕይወቱ እንደሚተርፍ ተነገረው (15-18) 40 ናቡዛራዳን ኤርምያስን በነፃ ለቀቀው (1-6) ጎዶልያስ በምድሪቱ ላይ ተሾመ (7-12) በጎዶልያስ ላይ ሴራ ተጠነሰሰ (13-16) 41 እስማኤል ጎዶልያስን ገደለው (1-10) ዮሃናን እስማኤልን አሳደደው (11-18) 42 ሕዝቡ ኤርምያስን እንዲጸልይላቸው ለመኑት (1-6) ይሖዋ “ወደ ግብፅ አትሂዱ” አላቸው (7-22) 43 ሕዝቡ አሻፈረን ብለው ወደ ግብፅ ሄዱ (1-7) የይሖዋ ቃል በግብፅ ወደነበረው ወደ ኤርምያስ መጣ (8-13) 44 በግብፅ የነበሩ አይሁዳውያን እንደሚጠፉ ተነገረ (1-14) ሕዝቡ የአምላክን ማስጠንቀቂያ አቃለለ (15-30) ‘የሰማይን ንግሥት’ አመለኩ (17-19) 45 ይሖዋ ለባሮክ ያስተላለፈው መልእክት (1-5) 46 በግብፅ ላይ የተነገረ ትንቢት (1-26) ናቡከደነጾር ግብፅን ድል ያደርጋል (13, 26) ለእስራኤል የተገባ ቃል (27, 28) 47 በፍልስጤማውያን ላይ የተነገረ ትንቢት (1-7) 48 በሞዓብ ላይ የተነገረ ትንቢት (1-47) 49 በአሞን ላይ የተነገረ ትንቢት (1-6) በኤዶም ላይ የተነገረ ትንቢት (7-22) ኤዶም ሙሉ በሙሉ ትደመሰሳለች (17, 18) በደማስቆ ላይ የተነገረ ትንቢት (23-27) በቄዳርና በሃጾር ላይ የተነገረ ትንቢት (28-33) በኤላም ላይ የተነገረ ትንቢት (34-39) 50 በባቢሎን ላይ የተነገረ ትንቢት (1-46) ከባቢሎን ሽሹ (8) እስራኤል ወደ ምድሩ ይመለሳል (17-19) የባቢሎን ውኃ ይደርቃል (38) ባቢሎን የሚኖርባት አይገኝም (39, 40) 51 በባቢሎን ላይ የተነገረ ትንቢት (1-64) ባቢሎን በድንገት በሜዶናውያን እጅ ትወድቃለች (8-12) መጽሐፉ ኤፍራጥስ ወንዝ ውስጥ ተወረወረ (59-64) 52 ሴዴቅያስ በባቢሎን ላይ ዓመፀ (1-3) ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን ከበበ (4-11) ከተማዋና ቤተ መቅደሱ በእሳት ጋዩ (12-23) ሕዝቡ በግዞት ወደ ባቢሎን ተወሰደ (24-30) ዮአኪን ተፈታ (31-34)