አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ሰቆቃወ ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት ሰቆቃወ ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት 1 ኢየሩሳሌም እንደ መበለት ተደርጋ ተገልጻለች ከተማዋ ብቻዋን ቀረች (1) ጽዮን የፈጸመችው ከባድ ኃጢአት (8, 9) ጽዮን በአምላክ ፊት ተቀባይነት አጣች (12-15) ጽዮንን የሚያጽናናት የለም (17) 2 የይሖዋ ቁጣ በኢየሩሳሌም ላይ ነደደ ርኅራኄ አላሳያትም (2) ይሖዋ ጠላት ሆነባት (5) በጽዮን የተነሳ የፈሰሰው እንባ (11-13) በመንገድ የሚያልፉ ውብ በነበረችው ከተማ ላይ ያፌዛሉ (15) ጠላቶች በጽዮን ላይ በደረሰው ጥፋት ይደሰታሉ (17) 3 ኤርምያስ ስሜቱንና ተስፋውን ገለጸ “በትዕግሥት እጠባበቃለሁ” (21) የአምላክ ምሕረት በየማለዳው አዲስ ነው (22, 23) ይሖዋ በእሱ ተስፋ ለሚያደርግ ሰው ጥሩ ነው (25) በልጅነት ቀንበር መሸከም ጥሩ ነው (27) አምላክ ወደ እሱ መቅረብ የሚቻልበትን መንገድ በደመና ዘግቷል (43, 44) 4 የኢየሩሳሌም መከበብ ያስከተለው መጥፎ ውጤት የምግብ እጦት (4, 5, 9) ሴቶች ልጆቻቸውን ቀቀሉ (10) “ይሖዋ ቁጣውን ገልጿል” (11) 5 ሕዝቡ ወደ ቀድሞው ሁኔታ ለመመለስ ያቀረበው ጸሎት “የደረሰብንን ነገር አስታውስ” (1) “ኃጢአት ስለሠራን ወዮልን!” (16) ‘ይሖዋ ሆይ፣ መልሰን’ (21) ‘ዘመናችንን አድስልን’ (21)