አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ አሞጽ የመጽሐፉ ይዘት አሞጽ የመጽሐፉ ይዘት 1 አሞጽ ከይሖዋ የተቀበለው መልእክት (1, 2) በተደጋጋሚ በተፈጸመ ዓመፅ የተነሳ የተላለፈ ፍርድ (3-15) ሶርያ (3-5)፣ ፍልስጤም (6-8)፣ ጢሮስ (9, 10)፣ ኤዶም (11, 12)፣ አሞን (13-15) 2 በተደጋጋሚ በተፈጸመ ዓመፅ የተነሳ የተላለፈ ፍርድ (1-16) ሞዓብ (1-3)፣ ይሁዳ (4, 5)፣ እስራኤል (6-16) 3 የአምላክን ፍርድ ማወጅ (1-8) ይሖዋ ለአገልጋዮቹ ሚስጥሩን ይገልጣል (7) ለሰማርያ የተነገረ የማስጠንቀቂያ መልእክት (9-15) 4 ለባሳን ላሞች የተነገረ የማስጠንቀቂያ መልእክት (1-3) ይሖዋ የእስራኤልን የሐሰት አምልኮ አንቋሸሸ (4, 5) እስራኤል የተሰጠውን ተግሣጽ አልተቀበለም (6-13) “አምላክህን ለመገናኘት ተዘጋጅ” (12) ‘አምላክ ሐሳቡን ለሰው ይገልጻል’ (13) 5 “ድንግሊቱ እስራኤል ወድቃለች” (1-3) አምላክን ፈልጉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ (4-17) “ክፉ የሆነውን ጥሉ፤ መልካም የሆነውንም ውደዱ” (15) የይሖዋ ቀን የጨለማ ቀን ነው (18-27) የእስራኤላውያን መሥዋዕት ተቀባይነት አጣ (22) 6 ዘና ብለው የሚኖሩ ወዮላቸው! (1-14) ከዝሆን ጥርስ የተሠራ አልጋ፤ የወይን ጠጅ የተሞላ ጽዋ (4, 6) 7 የእስራኤል ጥፋት እንደቀረበ የሚያሳዩ ራእዮች (1-9) አንበጦች (1-3)፣ እሳት (4-6)፣ ቱምቢ (7-9) አሞጽ መተንበዩን እንዲያቆም ተነገረው (10-17) 8 የበጋ ፍሬ የያዘው ቅርጫት ራእይ (1-3) ጨቋኞች ተወገዙ (4-14) መንፈሳዊ ረሃብ (11) 9 ከአምላክ ፍርድ ማምለጥ አይቻልም (1-10) የዳዊትን ዳስ መልሼ አቆማለሁ (11-15)