አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ሚክያስ የመጽሐፉ ይዘት ሚክያስ የመጽሐፉ ይዘት 1 በሰማርያና በይሁዳ ላይ የተላለፈ ፍርድ (1-16) ኃጢአትና ዓመፅ ችግር አስከተለ (5) 2 ጨቋኞች ወዮላቸው! (1-11) እስራኤልን መልሼ በአንድነት አኖራለሁ (12, 13) ምድሪቱ በሕዝብ ሁካታ ትሞላለች (12) 3 መሪዎችና ነቢያት ተወገዙ (1-12) ሚክያስ በይሖዋ መንፈስ አማካኝነት ኃይል ተሞላ (8) “ካህናቷ በክፍያ ያስተምራሉ” (11) “ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች” (12) 4 የይሖዋ ተራራ ከፍ ከፍ ይላል (1-5) ሰይፋቸውን ማረሻ ያደርጋሉ (3) ‘በይሖዋ ስም እንሄዳለን’ (5) ዳግመኛ የተቋቋመችው ጽዮን ብርቱ ትሆናለች (6-13) 5 በመላው ምድር ላይ ታላቅ የሚሆን ገዢ (1-6) ከቤተልሔም የሚወጣ ገዢ (2) የተረፉት እንደ ጠልና እንደ አንበሳ ይሆናሉ (7-9) ምድሪቱ ትነጻለች (10-15) 6 አምላክ ከእስራኤል ጋር ይሟገታል (1-5) “ይሖዋ ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው?” (6-8) ፍትሕ፣ ታማኝነት፣ ልክን ማወቅ (8) የእስራኤል በደልና የደረሰበት ቅጣት (9-16) 7 የእስራኤል ብልሹ ሥነ ምግባር (1-6) “የሰው ጠላቶቹ ቤተሰቦቹ ናቸው” (6) “በትዕግሥት እጠብቃለሁ” (7) በአምላክ ሕዝብ ላይ የተሰነዘረው ነቀፋ ይወገዳል (8-13) ሚክያስ ለአምላክ ያቀረበው ጸሎትና ውዳሴ (14-20) ይሖዋ የሰጠው መልስ (15-17) ‘እንደ ይሖዋ ያለ አምላክ ማን ነው?’ (18)