አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ሮም የመጽሐፉ ይዘት ለሮም ሰዎች የተጻፈ ደብዳቤ የመጽሐፉ ይዘት 1 ሰላምታ (1-7) ጳውሎስ ወደ ሮም ለመሄድ የነበረው ጉጉት (8-15) ‘ጻድቅ በእምነት ይኖራል’ (16, 17) አምላክን የማያከብሩ ሰዎች የሚያመካኙበት ነገር የላቸውም (18-32) የአምላክ ባሕርያት በፍጥረት ሥራው ላይ ይታያሉ (20) 2 አምላክ በአይሁዳውያንና በግሪካውያን ላይ ይፈርዳል (1-16) ሕሊና የሚሠራበት መንገድ (14, 15) አይሁዳውያንና ሕጉ (17-24) የልብ ግርዘት (25-29) 3 “የአምላክ እውነተኝነት የተረጋገጠ ነው” (1-8) ‘አይሁዳውያንም ሆኑ ግሪካውያን የኃጢአት ተገዢዎች ናቸው’ (9-20) በእምነት መጽደቅ (21-31) ‘ሁሉም የአምላክን ክብር ማንጸባረቅ ተስኗቸዋል’ (23) 4 አብርሃም በእምነቱ ጻድቅ ተባለ (1-12) አብርሃም እምነት ላላቸው ሁሉ አባት ነው (11) በእምነቱ የተነሳ የተስፋ ቃል ተገባለት (13-25) 5 በክርስቶስ አማካኝነት ከአምላክ ጋር መታረቅ (1-11) በአዳም በኩል ሞት፣ በክርስቶስ በኩል ሕይወት (12-21) ኃጢአትና ሞት ለሰው ሁሉ ተዳረሰ (12) አንድ የጽድቅ ተግባር (18) 6 ክርስቶስ ውስጥ በመጠመቅ አዲስ ሕይወት ማግኘት (1-11) ኃጢአት በሰውነታችሁ ላይ እንዲነግሥ አትፍቀዱ (12-14) ከኃጢአት ባርነት ተላቆ የአምላክ ባሪያ መሆን (15-23) የኃጢአት ደሞዝ ሞት፣ የአምላክ ስጦታ ግን ሕይወት ነው (23) 7 ከሕጉ ነፃ መውጣትን የሚያሳይ ምሳሌ (1-6) ሕጉ የኃጢአትን ምንነት አሳወቀ (7-12) ከኃጢአት ጋር የሚደረግ ትግል (13-25) 8 በመንፈስ የሚገኝ ሕይወትና ነፃነት (1-11) ‘የአምላክ ልጆች መሆናችንን መንፈሱ ይመሠክራል’ (12-17) ፍጥረት የአምላክ ልጆች የሚያገኙትን ነፃነት ይጠባበቃል (18-25) ‘መንፈስ ይማልድልናል’ (26, 27) አምላክ አስቀድሞ የወሰናቸው (28-30) በአምላክ ፍቅር አማካኝነት ድል ማድረግ (31-39) 9 ጳውሎስ ለሥጋዊ እስራኤላውያን አዘነላቸው (1-5) የአብርሃም እውነተኛ ዘር (6-13) የአምላክን ምርጫ በተመለከተ ጥያቄ ማንሳት አንችልም (14-26) የቁጣና የምሕረት ዕቃዎች (22, 23) “የሚድኑት ቀሪዎች ብቻ ናቸው” (27-29) እስራኤል ተሰናከለ (30-33) 10 መጽደቅ የሚቻልበት መንገድ (1-15) እምነትን በይፋ መናገር (10) “የይሖዋን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል” (13) ያማሩ እግሮች ያሏቸው ሰባኪዎች (15) ምሥራቹን አንቀበልም አሉ (16-21) 11 አምላክ እስራኤልን ሙሉ በሙሉ አልተወውም (1-16) የወይራ ዛፉ ምሳሌ (17-32) ጥልቅ የሆነው የአምላክ ጥበብ (33-36) 12 ሰውነታችሁን ሕያው መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ (1, 2) የተለያዩ ስጦታዎች ያሉት አንድ አካል (3-8) የክርስትና አኗኗርን በተመለከተ የተሰጠ ምክር (9-21) 13 ለባለሥልጣናት መገዛት (1-7) ቀረጥ መክፈል (6, 7) “ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው” (8-10) በቀን ብርሃን መመላለስ (11-14) 14 አንዳችሁ በሌላው ላይ አትፍረዱ (1-12) ሌሎችን አታሰናክሉ (13-18) ሰላምና አንድነት እንዲሰፍን ጥረት አድርጉ (19-23) 15 ‘እንደ ክርስቶስ አንዳችሁ ሌላውን ተቀበሉ’ (1-13) የአሕዛብ አገልጋይ የሆነው ጳውሎስ (14-21) የጳውሎስ የጉዞ ዕቅድ (22-33) 16 ጳውሎስ ፌበንን አስተዋወቀ (1, 2) ለሮም ክርስቲያኖች የቀረበ ሰላምታ (3-16) ክፍፍል ከሚፈጥሩ ነገሮች መራቅ (17-20) የጳውሎስ የሥራ አጋሮች ያቀረቡት ሰላምታ (21-24) ተሰውሮ የቆየው ቅዱስ ሚስጥር ተገልጧል (25-27)