አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 1 ጢሞቴዎስ የመጽሐፉ ይዘት ለጢሞቴዎስ የተጻፈ የመጀመሪያው ደብዳቤ የመጽሐፉ ይዘት 1 ሰላምታ (1, 2) ሐሰተኛ አስተማሪዎችን በተመለከተ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ (3-11) አምላክ ለጳውሎስ ያሳየው ጸጋ (12-16) የዘላለም ንጉሥ (17) ‘መልካሙን ውጊያ መዋጋትህን ቀጥል’ (18-20) 2 ለሁሉም ዓይነት ሰዎች ጸልዩ (1-7) አንድ አምላክ፣ አንድ መካከለኛ (5) ለሁሉም የሚሆን ተመጣጣኝ ቤዛ (6) ለወንዶችና ለሴቶች የተሰጠ መመሪያ (8-15) ልከኛ አለባበስ (9, 10) 3 የበላይ ተመልካቾች ብቃት (1-7) የጉባኤ አገልጋዮች ብቃት (8-13) “ለአምላክ የማደር ቅዱስ ሚስጥር” (14-16) 4 የአጋንንትን ትምህርት በተመለከተ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ (1-5) “የክርስቶስ ኢየሱስ ጥሩ አገልጋይ” (6-10) የአካል ብቃት እንቅስቃሴና ለአምላክ ማደር (8) ‘ለምታስተምረው ትምህርት ትኩረት ስጥ’ (11-16) 5 ወጣቶችንና አረጋውያንን በአግባቡ መያዝ (1, 2) ለመበለቶች የሚሰጥ ድጋፍ (3-16) ለቤተሰብ አባላት የሚያስፈልገውን ማቅረብ (8) ተግተው የሚሠሩ ሽማግሌዎችን ማክበር (17-25) ‘ለሆድህ ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጣ’ (23) 6 ባሮች ጌቶቻቸውን ያክብሩ (1, 2) የሐሰት አስተማሪዎችና የገንዘብ ፍቅር (3-10) ለአምላክ ሰው የተሰጠ መመሪያ (11-16) በመልካም ሥራዎች ባለጸጋ ሁኑ (17-19) “በአደራ የተሰጠህን ነገር ጠብቅ” (20, 21)