የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ዜና መዋዕል 19
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

1 ዜና መዋዕል የመጽሐፉ ይዘት

      • አሞናውያን የዳዊትን መልእክተኞች አዋረዷቸው (1-5)

      • በአሞናውያንና በሶርያውያን ላይ የተገኘ ድል (6-19)

1 ዜና መዋዕል 19:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 10:1-5

1 ዜና መዋዕል 19:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 9:7
  • +ዘፍ 19:36, 38

1 ዜና መዋዕል 19:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 19:27

1 ዜና መዋዕል 19:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 16:34

1 ዜና መዋዕል 19:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ከአራምናሃራይም።”

  • *

    አንድ ታላንት 34.2 ኪሎ ግራም ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 14:47፤ 2ሳሙ 8:3፤ 10:6

1 ዜና መዋዕል 19:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 13:8, 9

1 ዜና መዋዕል 19:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 8:16
  • +2ሳሙ 10:7, 8፤ 23:8

1 ዜና መዋዕል 19:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 10:9-12

1 ዜና መዋዕል 19:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እጅ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 11:20, 21

1 ዜና መዋዕል 19:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 8:5

1 ዜና መዋዕል 19:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 31:6፤ ኢያሱ 1:9

1 ዜና መዋዕል 19:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 26:7, 8፤ ዘዳ 28:7፤ 2ሳሙ 10:13, 14

1 ዜና መዋዕል 19:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ኤፍራጥስን ያመለክታል።

  • *

    በ2ሳሙ 10:16 ላይ ሾባክ ተብሎም ተጠርቷል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 8:3
  • +2ሳሙ 10:15, 16

1 ዜና መዋዕል 19:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 10:17-19

1 ዜና መዋዕል 19:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 18:39
  • +1ዜና 14:17፤ መዝ 18:44

ተዛማጅ ሐሳብ

1 ዜና 19:12ሳሙ 10:1-5
1 ዜና 19:22ሳሙ 9:7
1 ዜና 19:2ዘፍ 19:36, 38
1 ዜና 19:4ዘሌ 19:27
1 ዜና 19:51ነገ 16:34
1 ዜና 19:61ሳሙ 14:47፤ 2ሳሙ 8:3፤ 10:6
1 ዜና 19:7ኢያሱ 13:8, 9
1 ዜና 19:82ሳሙ 8:16
1 ዜና 19:82ሳሙ 10:7, 8፤ 23:8
1 ዜና 19:102ሳሙ 10:9-12
1 ዜና 19:111ዜና 11:20, 21
1 ዜና 19:122ሳሙ 8:5
1 ዜና 19:13ዘዳ 31:6፤ ኢያሱ 1:9
1 ዜና 19:14ዘሌ 26:7, 8፤ ዘዳ 28:7፤ 2ሳሙ 10:13, 14
1 ዜና 19:162ሳሙ 8:3
1 ዜና 19:162ሳሙ 10:15, 16
1 ዜና 19:172ሳሙ 10:17-19
1 ዜና 19:19መዝ 18:39
1 ዜና 19:191ዜና 14:17፤ መዝ 18:44
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
1 ዜና መዋዕል 19:1-19

አንደኛ ዜና መዋዕል

19 ከጊዜ በኋላ የአሞናውያን ንጉሥ ናሃሽ ሞተ፤ በእሱም ፋንታ ልጁ ነገሠ።+ 2 በዚህ ጊዜ ዳዊት “አባቱ ታማኝ ፍቅር+ ስላሳየኝ እኔም ለናሃሽ ልጅ ለሃኑን ታማኝ ፍቅር አሳየዋለሁ” አለ። በመሆኑም ዳዊት በአባቱ ሞት ከደረሰበት ሐዘን እንዲያጽናኑት መልእክተኞችን ላከ። ሆኖም የዳዊት አገልጋዮች ሃኑንን ለማጽናናት ወደ አሞናውያን+ ምድር ሲደርሱ 3 የአሞናውያን መኳንንት ሃኑንን እንዲህ አሉት፦ “ዳዊት አጽናኞችን ወደ አንተ የላከው አባትህን አክብሮ ይመስልሃል? አገልጋዮቹ ወደ አንተ የመጡት ምድሪቱን በሚገባ ለማጥናትና በውስጧ ያለውን ነገር ለመሰለል እንዲሁም አንተን ለመገልበጥ አይደለም?” 4 በመሆኑም ሃኑን የዳዊትን አገልጋዮች ወስዶ ላጫቸው፤+ ልብሳቸውንም እስከ መቀመጫቸው ድረስ አሳጥሮ በመቁረጥ መልሶ ላካቸው። 5 በአገልጋዮቹ ላይ የደረሰውን ነገር ለዳዊት በነገሩት ጊዜ ሰዎቹ በኀፍረት ተውጠው ስለነበር ዳዊት ወዲያውኑ መልእክተኞችን ወደ እነሱ ላከ፤ ንጉሡም “ጢማችሁ እስኪያድግ ድረስ በኢያሪኮ+ ቆዩ፤ ከዚያ በኋላ ተመለሱ” አላቸው።

6 ውሎ አድሮ አሞናውያን በዳዊት ዘንድ እንደ ጥንብ እንደተቆጠሩ ተገነዘቡ፤ በመሆኑም ሃኑን እና አሞናውያን ከሜሶጶጣሚያ፣* ከአራምመዓካና ከጾባህ+ ሠረገሎችንና ፈረሰኞችን ለመቅጠር 1,000 የብር ታላንት* ላኩ። 7 በዚህ መንገድ 32,000 ሠረገሎችን፣ የማአካን ንጉሥና ሕዝቡን ለራሳቸው ቀጠሩ። እነሱም መጥተው በመደባ+ ፊት ለፊት ሰፈሩ። አሞናውያን ደግሞ ከየከተሞቻቸው ተሰብስበው ለጦርነት መጡ።

8 ዳዊት ይህን በሰማ ጊዜ ኢዮአብን+ እንዲሁም እጅግ ኃያላን የሆኑትን ተዋጊዎቹን ጨምሮ መላውን ሠራዊት ላከ።+ 9 አሞናውያንም ወጥተው በከተማዋ መግቢያ ላይ ለውጊያ ተሰለፉ፤ የመጡት ነገሥታት ደግሞ ለብቻቸው ሜዳ ላይ ተሰለፉ።

10 ኢዮዓብ ወታደሮቹ ከፊትና ከኋላ ጥቃት ለመሰንዘር ወደ እሱ እየገሰገሱ መምጣታቸውን ሲያይ በእስራኤል ካሉት ምርጥ የሆኑ ተዋጊዎች መካከል የተወሰኑትን መርጦ ሶርያውያንን እንዲገጥሙ አሰለፋቸው።+ 11 የቀሩትን ሰዎች ደግሞ በወንድሙ በአቢሳ+ አመራር ሥር* ሆነው አሞናውያንን እንዲገጥሙ አሰለፋቸው። 12 ከዚያም እንዲህ አለው፦ “ሶርያውያን+ ከበረቱብኝ አንተ ትደርስልኛለህ፤ አሞናውያን ከበረቱብህ ደግሞ እኔ እደርስልሃለሁ። 13 ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተሞች ስንል ብርቱና ደፋር መሆን አለብን፤+ ይሖዋም በፊቱ መልካም የሆነውን ነገር ያደርጋል።”

14 ከዚያም ኢዮዓብና አብረውት የነበሩት ሰዎች ሶርያውያንን ለመግጠም ወደ እነሱ ሲገሰግሱ ሶርያውያኑ ከፊቱ ሸሹ።+ 15 አሞናውያንም ሶርያውያን እንደ ሸሹ ሲያዩ እነሱም ከወንድሙ ከአቢሳ ፊት ሸሽተው ወደ ከተማዋ ገቡ። ከዚያም ኢዮዓብ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።

16 ሶርያውያን በእስራኤላውያን ድል እንደተመቱ ሲያዩ መልእክተኞች ልከው በወንዙ*+ አካባቢ የነበሩትን ሶርያውያን አስጠሩ፤ የሃዳድኤዜር ሠራዊት አለቃ የሆነውም ሾፋክ* ይመራቸው ነበር።+

17 ዳዊት ወሬው በተነገረው ጊዜ ወዲያውኑ እስራኤልን ሁሉ ሰብስቦ ዮርዳኖስን በመሻገር ወደ እነሱ መጣ፤ ተዋጊዎቹንም በእነሱ ላይ አሰለፈ። ዳዊት ሶርያውያንን ለመግጠም ተዋጊዎቹን ባሰለፈ ጊዜ ከእሱ ጋር ተዋጉ።+ 18 ይሁንና ሶርያውያን ከእስራኤል ፊት ሸሹ፤ ዳዊትም ከሶርያውያን መካከል 7,000 ሠረገለኞችንና 40,000 እግረኛ ወታደሮችን ገደለ፤ የሠራዊቱ አዛዥ የሆነውን ሾፋክንም ገደለው። 19 የሃዳድኤዜር አገልጋዮች በእስራኤል እንደተሸነፉ+ ባዩ ጊዜ ወዲያውኑ ከዳዊት ጋር እርቅ በመፍጠር ለእሱ ተገዙ፤+ ሶርያም ከዚህ በኋላ አሞናውያንን ለመርዳት ፈቃደኛ አልሆነችም።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ