ኢዮብ
37 “ከዚህም የተነሳ ልቤ ይመታል፤
ከስፍራውም ይዘላል።
2 የድምፁን ጉምጉምታ፣
ከአፉም የሚወጣውን ነጎድጓድ በጥሞና ስሙ።
3 ከሰማያት በታች ይልከዋል፤
መብረቁንም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይሰደዋል።+
6 በረዶውን ‘ወደ መሬት ውረድ፣’+
ዶፉን ዝናብም ‘በኃይል ውረድ’ ይለዋልና።+
7 ሟች የሆነ ሰው ሁሉ ሥራውን እንዲያውቅ፣
አምላክ የእያንዳንዱን ሰው ሥራ ያስቆማል።*
8 የዱር አራዊት ወደ ጎሬአቸው ይገባሉ፤
በዋሻዎቻቸውም ውስጥ ይቀመጣሉ።
14 ኢዮብ ሆይ፣ ይህን ስማ፤
ቆም ብለህ የአምላክን ድንቅ ሥራዎች በጥሞና አስብ።+
15 አምላክ ደመናትን እንዴት እንደሚቆጣጠር፣*
ከደመናውም እንዴት መብረቅ እንደሚያበርቅ ታውቃለህ?
16 ደመናት እንዴት እንደሚንሳፈፉ ታውቃለህ?+
እነዚህ፣ እውቀቱ ፍጹም የሆነው አምላክ ድንቅ ሥራዎች ናቸው።+
17 ምድር በደቡብ ነፋስ ጸጥ ስትል፣
ልብስህ የሚሞቀው ለምንድን ነው?+
19 ለእሱ የምንለውን ንገረን፤
ጨለማ ውስጥ ስለሆን መልስ መስጠት አንችልም።
20 እኔ መናገር እንደምፈልግ ለእሱ ማሳወቅ ያስፈልጋል?
ወይስ እሱ ሊያውቀው የሚገባ ነገር የተናገረ ሰው አለ?+
22 ከሰሜን ወርቃማ ጨረር ይወጣል፤
የአምላክ ግርማ+ አስፈሪ ነው።
24 ስለዚህ ሰዎች ሊፈሩት ይገባል።+