ኢዮብ
38 ከዚያም ይሖዋ ከአውሎ ነፋስ ውስጥ ለኢዮብ መለሰለት፦+
2 “ሐሳቤን የሚሰውርና
ያለእውቀት የሚናገር ይህ ማን ነው?+
3 እስቲ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፤
እኔ እጠይቅሃለሁ፤ አንተም ንገረኝ።
4 ምድርን በመሠረትኩ ጊዜ አንተ የት ነበርክ?+
ማስተዋል አለኝ የምትል ከሆነ ንገረኝ።
5 የምታውቅ ከሆነ፣ መለኪያዎቿን የወሰነ፣
ወይስ መለኪያ ገመድ በላይዋ ላይ የዘረጋ ማን ነው?
8 ባሕሩ ከማህፀን አፈትልኮ በወጣ ጊዜ፣
በር የዘጋበት ማን ነው?+
9 ደመና ባለበስኩት ጊዜ፣
በድቅድቅ ጨለማም በጠቀለልኩት ጊዜ፣
10 በላዩም ድንበሬን በወሰንኩ ጊዜ፣
መቀርቀሪያዎችና በሮች ባደረግኩለት ጊዜ፣+
11 ደግሞም ‘እስከዚህ ድረስ መምጣት ትችላለህ፤ ከዚህ ግን አታልፍም፤
የኩሩው ማዕበልህም ገደብ ይህ ነው’ ባልኩ ጊዜ+ አንተ የት ነበርክ?
12 ለመሆኑ ንጋትን አዘህ ታውቃለህ?
ወይስ ጎህ ስፍራውን እንዲያውቅ አድርገሃል?+
13 የማለዳ ብርሃን ወደ ምድር ዳርቻዎች እንዲሄድ፣
ክፉዎችንም ከላይዋ እንዲያራግፍ ያዘዝከው አንተ ነህ?+
14 ምድር ከማኅተም በታች እንዳለ የሸክላ ጭቃ ትለወጣለች፤
ገጽታዎቿም እንደሚያምር ልብስ ጎልተው ይታያሉ።
15 የክፉዎች ብርሃን ግን ከእነሱ ተወስዷል፤
ከፍ ያለው ክንዳቸውም ተሰብሯል።
16 ወደ ባሕሩ ምንጮች ወርደሃል?
ወይስ ጥልቁን ውኃ መርምረሃል?+
18 ምድር ምን ያህል ሰፊ እንደሆነች አስተውለሃል?+
ይህን ሁሉ የምታውቅ ከሆነ ተናገር።
19 ብርሃን የሚኖረው በየት አቅጣጫ ነው?+
የጨለማ ስፍራስ የት ነው?
20 ወደ ክልሉ ልትወስደው ትችላለህ?
ወደ ቤቱስ የሚወስደውን ጎዳና ታውቃለህ?
21 በዚያን ጊዜ ተወልደህ ስለነበር፣
ዕድሜህም ትልቅ ስለሆነ* ይህን ሳታውቅ አትቀርም!
25 ለዶፍ መውረጃን፣
ነጎድጓድ ለቀላቀለ ጥቁር ደመናም መንገድን ያዘጋጀ ማን ነው?+
26 አንድም ሰው በሌለበት ቦታ፣
ሰውም በማይኖርበት ምድረ በዳ የሚያዘንበው፣+
27 የወደመውን ጠፍ መሬት የሚያረካው፣
ሣርንም የሚያበቅለው ማን ነው?+
29 በረዶ የሚወጣው ከማን ማህፀን ነው?
የሰማዩንስ አመዳይ የወለደው ማን ነው?+
30 ውኃዎች በድንጋይ የተሸፈኑ ያህል እንዲሆኑ፣
የጥልቁ ውኃም ገጽ ግግር በረዶ እንዲሆን የሚያደርገው ማን ነው?+
34 ጎርፍ ይሸፍንህ ዘንድ፣
ድምፅህን ወደ ደመናት ማንሳት ትችላለህ?+
35 የመብረቅ ብልጭታዎችን መላክ ትችላለህ?
እነሱስ አንተ ጋ ቀርበው ‘ይኸው መጥተናል!’ ይሉሃል?
37 ደመናትን ለመቁጠር የሚያስችል ጥበብ ያለው ማን ነው?
ወይስ የሰማይን የውኃ ማሰሮዎች ሊደፋ የሚችል ማን ነው?+
38 አፈሩ ቦክቶ እንዲጋገር፣
የምድር ጓሎችም እንዲጣበቁ ሊያደርግ የሚችል ማን ነው?
39 ለአንበሳ አድነህ ግዳይ ልታመጣለት፣
ወይስ የተራቡ የአንበሳ ግልገሎችን ልታጠግብ ትችላለህ?+
40 እነሱ በዋሻቸው ውስጥ አድፍጠው፣
ወይም በጎሬአቸው አድብተው ሳለ ይህን ልታደርግ ትችላለህ?