ኢዮብ
7 “በምድር ላይ ያለ ሟች የሆነ ሰው ሕይወት፣ እንደ ግዳጅ አገልግሎት አይደለም?
የሕይወት ዘመኑስ እንደ ቅጥር ሠራተኛ ዘመን አይደለም?+
2 እንደ ባሪያ፣ ጥላ ለማግኘት ይመኛል፤
እንደ ቅጥር ሠራተኛም ደሞዙን ለመቀበል በጉጉት ይጠባበቃል።+
3 እኔም ከንቱ የሆኑ ወራት ተመድበውልኛል፤
በሥቃይ የተሞሉ ሌሊቶችም ተወስነውልኛል።+
4 በተኛሁ ጊዜ ‘የምነሳው መቼ ነው?’ እላለሁ።+
ሌሊቱም ሲረዝም ጎህ እስኪቀድ* ድረስ ያለእረፍት እገላበጣለሁ።
8 አሁን የሚያየኝ ዓይን ከእንግዲህ አያየኝም፤
ዓይኖችህ እኔን ይፈልጋሉ፤ እኔ ግን አልኖርም።+
10 ዳግመኛ ወደ ቤቱ አይመለስም፤
ስፍራውም ከእንግዲህ ወዲህ አያውቀውም።+
11 ስለዚህ እኔ ከመናገር ወደኋላ አልልም።
12 በእኔ ላይ ጠባቂ የምታቆመው፣
እኔ ባሕር ነኝ ወይስ ግዙፍ የባሕር ፍጥረት?
13 ‘መኝታዬ ያጽናናኛል፣
አልጋዬ ሥቃዬን ያቀልልኛል’ ባልኩ ጊዜ፣
16 ሕይወቴን ተጸየፍኳት፤+ በሕይወት መቀጠል አልፈልግም።
ዘመኔ እንደ እስትንፋስ+ ስለሆነ ተወት አድርገኝ።
18 በየማለዳው የምትመረምረው፣
በየጊዜውም የምትፈትነው ለምንድን ነው?+
20 የሰውን ልጅ የምትከታተል ሆይ፣+ ኃጢአት ብሠራ እንኳ አንተን እንዴት ልጎዳህ እችላለሁ?
ዒላማህ ያደረግከኝ ለምንድን ነው?
ሸክም ሆኜብሃለሁ?
21 መተላለፌን ይቅር የማትለው፣
በደሌንም በምሕረት የማታልፈው ለምንድን ነው?
ከጥቂት ጊዜ በኋላ አፈር ውስጥ እጋደማለሁና፤+
አንተም ትፈልገኛለህ፤ እኔ ግን አልገኝም።”