ኢዮብ
8 ከዚያም ሹሃዊው+ በልዳዶስ+ እንዲህ ሲል መለሰ፦
2 “እንዲህ የምትናገረው እስከ መቼ ነው?+
ከአፍህ የሚወጣው ቃል ብርቱ ነፋስ ነው!
3 አምላክ ፍትሕን ያዛባል?
ወይስ ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ጽድቅን ያጣምማል?
4 ልጆችህ በእሱ ላይ ኃጢአት ሠርተው ከሆነ፣
ለፈጸሙት ዓመፅ እንዲቀጡ አድርጓል፤*
5 አንተ ግን ወደ አምላክ ዞር ብትል፣+
ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ሞገስ እንዲያሳይህ ብትማጸን፣
6 በእርግጥ ንጹሕና ቅን ብትሆን፣+
እሱ ትኩረት ይሰጥሃል፤*
ወደ ትክክለኛ ቦታህም ይመልስሃል።
7 ጅማሬህ አነስተኛ ቢሆንም፣
የወደፊት ሕይወትህ ታላቅ ይሆናል።+
8 እስቲ የቀድሞውን ትውልድ ጠይቅ፤
አባቶቻቸው ለተገነዘቧቸው ነገሮችም ትኩረት ስጥ።+
9 እኛ የተወለድነው ገና ትናንት ስለሆነ የምናውቀው ነገር የለም፤
ምክንያቱም በምድር ላይ ዘመናችን እንደ ጥላ ነው።
10 እነሱ አያስተምሩህም?
ደግሞስ የሚያውቁትን ነገር* አይነግሩህም?
11 ደንገል ረግረጋማ ባልሆነ ስፍራ ያድጋል?
ሸምበቆስ ውኃ በሌለበት ቦታ ያድጋል?
12 ገና ሳያብብና ሳይቆረጥ፣
ከሌላው ተክል ሁሉ በፊት ይደርቃል።
13 አምላክን የሚረሱ ሰዎች ሁሉ መጨረሻቸው እንደዚህ ነው፤*
አምላክ የለሽ የሆነ* ሰው ተስፋ ይጨልማልና፤
14 የሚመካበት ነገር ከንቱ ነው፤
የሚታመንበትም ነገር ከሸረሪት ድር* የማይሻል ነው።
15 እሱ ቤቱን ይደገፈዋል፤ ሆኖም ቤቱ ጸንቶ አይቆምም፤
አጥብቆ ሊይዘው ይሞክራል፤ ሆኖም አይጸናም።
16 እሱ በፀሐይ ብርሃን እንደሚያድግ እርጥበት ያለው ተክል ነው፤
ቅርንጫፎቹም በአትክልት ስፍራው ውስጥ ይንሰራፋሉ።+
17 ሥሩም በድንጋይ ክምር ውስጥ ይጠላለፋል፤
በድንጋዮቹ መካከል ቤት ይፈልጋል።*
22 የሚጠሉህ ኀፍረት ይከናነባሉ፤
የክፉዎችም ድንኳን ይጠፋል።”