የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሕዝቅኤል 25
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ሕዝቅኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • በአሞን ላይ የተነገረ ትንቢት (1-7)

      • በሞዓብ ላይ የተነገረ ትንቢት (8-11)

      • በኤዶም ላይ የተነገረ ትንቢት (12-14)

      • በፍልስጤም ላይ የተነገረ ትንቢት (15-17)

ሕዝቅኤል 25:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 19:36, 38
  • +ኤር 49:1፤ አሞጽ 1:13፤ ሶፎ 2:9

ሕዝቅኤል 25:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በግንብ የታጠሩ ሰፈሮቻቸውን ይመሠርታሉ።”

ሕዝቅኤል 25:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 12:26፤ ሕዝ 21:20

ሕዝቅኤል 25:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስህ በንቀት ተሞልታ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሰቆ 2:15
  • +ሶፎ 2:8

ሕዝቅኤል 25:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 49:2፤ አሞጽ 1:14

ሕዝቅኤል 25:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 15:1፤ ኤር 48:1፤ አሞጽ 2:1
  • +ዘዳ 2:4

ሕዝቅኤል 25:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ጌጥ።”

  • *

    ወይም “የሞዓብ አቀበት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 32:37, 38፤ ኢያሱ 13:15, 19

ሕዝቅኤል 25:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 25:4
  • +ሕዝ 21:28, 32

ሕዝቅኤል 25:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 48:1

ሕዝቅኤል 25:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 28:17፤ መዝ 137:7፤ ሰቆ 4:22፤ አሞጽ 1:11፤ አብ 10

ሕዝቅኤል 25:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሚል 1:4
  • +ኤር 49:7, 8

ሕዝቅኤል 25:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 11:14፤ 63:1
  • +ናሆም 1:2

ሕዝቅኤል 25:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በነፍሳቸው ንቀት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 28:18፤ ኢሳ 9:11, 12፤ 14:29፤ ኤር 47:1፤ ኢዩ 3:4-6፤ አሞጽ 1:6

ሕዝቅኤል 25:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 25:17, 20፤ ሶፎ 2:4
  • +ሶፎ 2:5
  • +ኤር 47:4

ተዛማጅ ሐሳብ

ሕዝ. 25:2ዘፍ 19:36, 38
ሕዝ. 25:2ኤር 49:1፤ አሞጽ 1:13፤ ሶፎ 2:9
ሕዝ. 25:52ሳሙ 12:26፤ ሕዝ 21:20
ሕዝ. 25:6ሰቆ 2:15
ሕዝ. 25:6ሶፎ 2:8
ሕዝ. 25:7ኤር 49:2፤ አሞጽ 1:14
ሕዝ. 25:8ኢሳ 15:1፤ ኤር 48:1፤ አሞጽ 2:1
ሕዝ. 25:8ዘዳ 2:4
ሕዝ. 25:9ዘኁ 32:37, 38፤ ኢያሱ 13:15, 19
ሕዝ. 25:10ሕዝ 25:4
ሕዝ. 25:10ሕዝ 21:28, 32
ሕዝ. 25:11ኤር 48:1
ሕዝ. 25:122ዜና 28:17፤ መዝ 137:7፤ ሰቆ 4:22፤ አሞጽ 1:11፤ አብ 10
ሕዝ. 25:13ሚል 1:4
ሕዝ. 25:13ኤር 49:7, 8
ሕዝ. 25:14ኢሳ 11:14፤ 63:1
ሕዝ. 25:14ናሆም 1:2
ሕዝ. 25:152ዜና 28:18፤ ኢሳ 9:11, 12፤ 14:29፤ ኤር 47:1፤ ኢዩ 3:4-6፤ አሞጽ 1:6
ሕዝ. 25:16ኤር 25:17, 20፤ ሶፎ 2:4
ሕዝ. 25:16ሶፎ 2:5
ሕዝ. 25:16ኤር 47:4
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ሕዝቅኤል 25:1-17

ሕዝቅኤል

25 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን ወደ አሞናውያን+ አዙረህ በእነሱ ላይ ትንቢት ተናገር።+ 3 አሞናውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘የሉዓላዊውን ጌታ የይሖዋን ቃል ስሙ። ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “መቅደሴ በረከሰ ጊዜና የእስራኤል ምድር ባድማ በሆነ ጊዜ እንዲሁም የይሁዳ ቤት ሰዎች በግዞት በተወሰዱ ጊዜ ‘እሰይ!’ ስላላችሁ 4 ለምሥራቅ ሰዎች ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ። እነሱ በእናንተ ውስጥ ይሰፍራሉ፤* ድንኳኖቻቸውንም በመካከላችሁ ይተክላሉ። ፍሬያችሁን ይበላሉ፤ ወተታችሁንም ይጠጣሉ። 5 ራባን+ የግመሎች መሰማሪያ፣ የአሞናውያንን ምድርም መንጋ የሚያርፍበት ስፍራ አደርጋለሁ፤ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።”’”

6 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘በእጅህ ስላጨበጨብክና+ በእግርህ መሬቱን ስለመታህ እንዲሁም በእስራኤል ምድር ላይ የደረሰውን ሁኔታ ስታይ በንቀት ተሞልተህ* ሐሴት ስላደረግክ፣+ 7 ብሔራት እንዲበዘብዙህ ለእነሱ አሳልፌ እሰጥህ ዘንድ እጄን በአንተ ላይ እዘረጋለሁ። ከሕዝቦች መካከል አስወግድሃለሁ፤ ከአገራትም መካከል ለይቼ አጠፋሃለሁ።+ እደመስስሃለሁ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃለህ።’

8 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሞዓብና+ ሴይር+ “እነሆ፣ የይሁዳ ቤት ልክ እንደ ሌሎቹ ብሔራት ነው” ስላሉ፣ 9 በድንበሩ ላይ የሚገኙትና የምድሪቱ ውበት* የሆኑት ከተሞች ማለትም ከቤትየሺሞትና ከበዓልመዖን አንስቶ እስከ ቂርያታይም+ ድረስ ያለው የሞዓብ ክንፍ* ለጠላት እንዲጋለጥ አደርጋለሁ። 10 ከአሞናውያን ጋር ለምሥራቅ ሰዎች ርስት አድርጌ እሰጠዋለሁ፤+ ይህም አሞናውያን በብሔራት መካከል እንዳይታወሱ ለማድረግ ነው።+ 11 በሞዓብም ላይ የፍርድ እርምጃ እወስዳለሁ፤+ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’

12 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ኤዶም በቂም በቀል ተነሳስቶ በይሁዳ ቤት ላይ እርምጃ ወስዷል፤ ደግሞም እነሱን በመበቀል ከፍተኛ በደል ፈጽሟል፤+ 13 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እጄን በኤዶምም ላይ እዘረጋለሁ፤ ከምድሪቱም ላይ ሰውንም ሆነ ከብትን አጠፋለሁ፤ ባድማም አደርጋታለሁ።+ ከቴማን አንስቶ እስከ ዴዳን ድረስ በሰይፍ ይወድቃሉ።+ 14 ‘በሕዝቤ በእስራኤል እጅ ኤዶምን እበቀላለሁ።+ እነሱም፣ ኤዶም የምወስደውን የበቀል እርምጃ ይቀምስ ዘንድ ቁጣዬንና መዓቴን በኤዶም ላይ ያወርዳሉ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”’

15 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ፍልስጤማውያን በማይበርድ የጠላትነት ስሜት ተነሳስተው በክፋት* የበቀል እርምጃ ለመውሰድና ጥፋት ለማድረስ ጥረት አድርገዋል።+ 16 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በፍልስጤማውያን ላይ እጄን እዘረጋለሁ፤+ ከሪታውያንንም አጠፋለሁ፤+ በባሕሩ ዳርቻ ላይ የቀሩትንም ነዋሪዎች እደመስሳለሁ።+ 17 ኃይለኛ ቅጣት በመቅጣት ታላቅ የበቀል እርምጃ እወስድባቸዋለሁ፤ በምበቀላቸውም ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”’”

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ