የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሕዝቅኤል 26
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ሕዝቅኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • በጢሮስ ላይ የተነገረ ትንቢት (1-21)

        • “የመረብ ማስጫ ቦታ” (5, 14)

        • ድንጋዮቿና አፈሯ ወደ ባሕር ይጣላሉ (12)

ሕዝቅኤል 26:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዩ 3:4-6፤ አሞጽ 1:9
  • +ሰቆ 1:1

ሕዝቅኤል 26:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 23:11፤ አሞጽ 1:10፤ ዘካ 9:4

ሕዝቅኤል 26:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 27:32

ሕዝቅኤል 26:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ሴቶች ልጆቿም።”

ሕዝቅኤል 26:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ናቡከደረጾርን።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

  • *

    ቃል በቃል “ሰዎችን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 25:9፤ ሕዝ 29:18
  • +ዕን 1:8
  • +ኤር 4:13
  • +ዳን 2:37

ሕዝቅኤል 26:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በማጥቂያ መሣሪያ።”

  • *

    ወይም “በሰይፍ።”

ሕዝቅኤል 26:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የሠረገላ ተሽከርካሪ እግር።

ሕዝቅኤል 26:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 5:28፤ ዕን 1:8

ሕዝቅኤል 26:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 27:32, 33፤ 28:5, 18፤ ዘካ 9:3

ሕዝቅኤል 26:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 23:16

ሕዝቅኤል 26:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 26:4, 5

ሕዝቅኤል 26:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የታረዱት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 27:28

ሕዝቅኤል 26:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አለቆች።”

  • *

    ወይም “እጅጌ የሌለው ቀሚሳቸውንም።”

  • *

    ቃል በቃል “መንቀጥቀጥን እንደ ልብስ ይለብሳሉ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 27:35፤ 32:10

ሕዝቅኤል 26:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሐዘን እንጉርጉሮ ያሰማሉ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 27:32
  • +አሞጽ 1:9, 10
  • +ሕዝ 28:2

ሕዝቅኤል 26:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 23:5

ሕዝቅኤል 26:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 27:34

ሕዝቅኤል 26:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መቃብር።”

  • *

    ወይም “አስጌጣለሁ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 28:8

ሕዝቅኤል 26:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 27:36

ተዛማጅ ሐሳብ

ሕዝ. 26:2ኢዩ 3:4-6፤ አሞጽ 1:9
ሕዝ. 26:2ሰቆ 1:1
ሕዝ. 26:4ኢሳ 23:11፤ አሞጽ 1:10፤ ዘካ 9:4
ሕዝ. 26:5ሕዝ 27:32
ሕዝ. 26:7ኤር 25:9፤ ሕዝ 29:18
ሕዝ. 26:7ዕን 1:8
ሕዝ. 26:7ኤር 4:13
ሕዝ. 26:7ዳን 2:37
ሕዝ. 26:11ኢሳ 5:28፤ ዕን 1:8
ሕዝ. 26:12ሕዝ 27:32, 33፤ 28:5, 18፤ ዘካ 9:3
ሕዝ. 26:13ኢሳ 23:16
ሕዝ. 26:14ሕዝ 26:4, 5
ሕዝ. 26:15ሕዝ 27:28
ሕዝ. 26:16ሕዝ 27:35፤ 32:10
ሕዝ. 26:17ሕዝ 27:32
ሕዝ. 26:17አሞጽ 1:9, 10
ሕዝ. 26:17ሕዝ 28:2
ሕዝ. 26:18ኢሳ 23:5
ሕዝ. 26:19ሕዝ 27:34
ሕዝ. 26:20ሕዝ 28:8
ሕዝ. 26:21ሕዝ 27:36
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ሕዝቅኤል 26:1-21

ሕዝቅኤል

26 በ11ኛው ዓመት፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ጢሮስ ስለ ኢየሩሳሌም+ ‘እሰይ! የሕዝቦች በር ተሰበረች!+ አሁን እሷ ስለጠፋች ሁሉም ነገር ይሳካልኛል፤ ደግሞም እበለጽጋለሁ’ ስላለች፣ 3 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ጢሮስ ሆይ፣ እነሆ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ፤ ባሕር ሞገዱን እንደሚያስነሳ ብዙ ብሔራትን በአንቺ ላይ አስነሳለሁ። 4 እነሱ የጢሮስን ቅጥሮች ያፈርሳሉ፤ ማማዎቿንም ያወድማሉ፤+ አፈሯን ከላይዋ ጠርጌ አስወግዳለሁ፤ የሚያንጸባርቅ ገላጣ ዓለትም አደርጋታለሁ። 5 በባሕር መካከል የመረብ ማስጫ ቦታ ትሆናለች።’+

“‘እኔ ራሴ ተናግሬአለሁና፣’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ብሔራትም ይበዘብዟታል። 6 በገጠር ያሉ ሰፈሮቿም* በሰይፍ ይመታሉ፤ ሰዎችም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’

7 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘እነሆ፣ በጢሮስ ላይ የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነጾርን* ከሰሜን አመጣለሁ፤+ እሱ ፈረሶችን፣+ የጦር ሠረገሎችን፣+ ፈረሰኞችንና ብዙ ወታደሮችን* ያቀፈ ሠራዊት ያለው የነገሥታት ንጉሥ ነው።+ 8 በገጠር ያሉ ሰፈሮችሽን በሰይፍ ያወድማል፤ በአንቺም ላይ ለከበባ የሚያገለግል ግንብ ይገነባል፤ የአፈር ቁልልም ይደለድላል፤ በአንቺም ላይ ትልቅ ጋሻ ያነሳል። 9 ቅጥሮችሽን በግንብ መደርመሻ መሣሪያ* ይደበድባል፤ ማማዎችሽንም በመጥረቢያ* ያፈርሳል። 10 ፈረሶቹ እጅግ ብዙ ከመሆናቸው የተነሳ አቧራ ያለብሱሻል፤ ሰዎች ቅጥሮቿ ወደፈረሱባት ከተማ እንደሚገቡ ሁሉ እሱም በበሮችሽ በሚገባበት ጊዜ የፈረሰኞቹ፣ የመንኮራኩሮቹና* የሠረገሎቹ ድምፅ ቅጥሮችሽን ያናውጣል። 11 የፈረሶቹ ኮቴዎች ጎዳናዎችሽን ሁሉ ይረግጣሉ፤+ ሕዝብሽን በሰይፍ ይገድላል፤ ግዙፍ የሆኑት ዓምዶችሽ መሬት ላይ ይንኮታኮታሉ። 12 ሀብትሽን ይበዘብዛሉ፤ ሸቀጥሽን ይዘርፋሉ፤+ ቅጥሮችሽን ያፈርሳሉ፤ የሚያማምሩ ቤቶችሽንም ያወድማሉ፤ ከዚያም ድንጋዮችሽን፣ ሳንቃዎችሽንና አፈርሽን ወደ ባሕር ይጥላሉ።’

13 “‘የዘፈንሽ ጩኸት ጸጥ እንዲል አደርጋለሁ፤ የበገናሽም ድምፅ ከእንግዲህ አይሰማም።+ 14 የሚያንጸባርቅ ገላጣ ዓለትም አደርግሻለሁ፤ የመረብ ማስጫ ቦታ ትሆኛለሽ።+ ዳግመኛ አትገነቢም፤ እኔ ይሖዋ ራሴ ተናግሬአለሁና’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።

15 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ጢሮስን እንዲህ ይላል፦ ‘ሞት አፋፍ ላይ ያሉት* ሲያቃስቱና በመካከልሽ ጭፍጨፋ ሲካሄድ፣ ከውድቀትሽ ድምፅ የተነሳ ደሴቶች አይናወጡም?+ 16 የባሕርም ገዢዎች* ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ፤ ልብሳቸውንም * ያወልቃሉ፤ የተጠለፉ ሸማዎቻቸውንም አውልቀው ይጥላሉ፤ ደግሞም በጣም ይንቀጠቀጣሉ።* መሬት ላይ ተቀምጠው ያለማቋረጥ ይንቀጠቀጣሉ፤ በመገረምም አተኩረው ይመለከቱሻል።+ 17 በአንቺም ላይ ሙሾ ያወርዳሉ፤*+ እንዲህም ይሉሻል፦

“ባሕር አቋርጠው የመጡ ሰዎች የሰፈሩብሽ፣ የተወደስሽ ከተማ ሆይ፣ እንዴት ጠፋሽ!+

አንቺም ሆንሽ ነዋሪዎችሽ በምድር ነዋሪዎች ሁሉ ላይ

ሽብር የምትነዙ የባሕር ላይ ኃያላን ነበራችሁ።+

18 በምትወድቂበት ቀን ደሴቶች ይንቀጠቀጣሉ፤

ጥፋት በሚደርስብሽ ጊዜ በባሕር ላይ ያሉ ደሴቶች ይሸበራሉ።”’+

19 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘ሰው እንደማይኖርባቸው ከተሞች ባድማ ሳደርግሽ፣ የሚያጥለቀልቅ ውኃ ሳመጣብሽና ኃይለኛ ውኃ ሲሸፍንሽ፣+ 20 አንቺንም ሆነ ከአንቺ ጋር ወደ ጉድጓድ* የሚወርዱትን፣ የጥንት ዘመን ሰዎች ወዳሉበት አወርዳችኋለሁ፤ ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱት ጋር፣ ጥንት እንደወደሙት ቦታዎች እጅግ ዝቅተኛ በሆነ ምድር እንድትኖሪ አደርጋለሁ፤+ ይህም የሚሆነው ሰው እንዳይኖርብሽ ነው። ከዚያ በኋላ የሕያዋንን ምድር ከፍ ከፍ አደርጋለሁ።*

21 “‘በአንቺ ላይ ድንገተኛ ሽብር አመጣለሁ፤ ከእንግዲህም አትኖሪም።+ ይፈልጉሻል ግን ፈጽሞ አትገኚም’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ