የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሕዝቅኤል 3
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ሕዝቅኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • ሕዝቅኤል አምላክ የሰጠውን ጥቅልል እንዲበላ ታዘዘ (1-15)

      • ሕዝቅኤል ጠባቂ ሆኖ እንዲያገለግል ተሾመ (16-27)

        • ቸልተኛ መሆን የደም ዕዳ ያስከትላል (18-21)

ሕዝቅኤል 3:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ያገኘኸውን ብላ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ራእይ 10:9, 10

ሕዝቅኤል 3:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 119:103፤ ኤር 15:16፤ ራእይ 10:9, 10

ሕዝቅኤል 3:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮናስ 3:4, 5፤ ማቴ 11:21

ሕዝቅኤል 3:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 10:16
  • +ዘፀ 34:9፤ ኤር 3:3፤ 5:3

ሕዝቅኤል 3:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 1:18, 19፤ 15:20፤ ሚክ 3:8

ሕዝቅኤል 3:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 50:7
  • +ኤር 17:18

ሕዝቅኤል 3:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የሕዝብህ ወንዶች ልጆች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 24:12, 14
  • +ሕዝ 2:5

ሕዝቅኤል 3:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 8:3

ሕዝቅኤል 3:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የሠረገላ ተሽከርካሪ እግር።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 1:24
  • +ሕዝ 10:16

ሕዝቅኤል 3:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 1:3
  • +ኤር 23:9

ሕዝቅኤል 3:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 21:8፤ 62:6፤ ኤር 6:17
  • +ኢሳ 58:1፤ ሕዝ 33:7

ሕዝቅኤል 3:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ይሁንና ስለ ደሙ አንተን ተጠያቂ አደርግሃለሁ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 2:40፤ 1ጢሞ 4:16
  • +ሕዝ 33:4
  • +ሕዝ 33:8

ሕዝቅኤል 3:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስህን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 33:9፤ ሥራ 18:6፤ 20:26

ሕዝቅኤል 3:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ኢፍትሐዊ ድርጊት ቢፈጽም።”

  • *

    ወይም “ይሁንና ስለ ደሙ አንተን ተጠያቂ አደርግሃለሁ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 18:24, 26፤ 33:12, 18
  • +ዘሌ 19:17፤ ሕዝ 33:6፤ ዕብ 13:17

ሕዝቅኤል 3:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስህን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 17:10፤ ሕዝ 33:14, 15፤ ያዕ 5:19, 20

ሕዝቅኤል 3:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 1:1
  • +ሕዝ 1:27, 28

ሕዝቅኤል 3:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 2:2፤ ዳን 10:19

ሕዝቅኤል 3:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 24:27፤ 33:22
  • +ማቴ 11:15
  • +ኢሳ 30:9

ተዛማጅ ሐሳብ

ሕዝ. 3:1ራእይ 10:9, 10
ሕዝ. 3:3መዝ 119:103፤ ኤር 15:16፤ ራእይ 10:9, 10
ሕዝ. 3:6ዮናስ 3:4, 5፤ ማቴ 11:21
ሕዝ. 3:7ሉቃስ 10:16
ሕዝ. 3:7ዘፀ 34:9፤ ኤር 3:3፤ 5:3
ሕዝ. 3:8ኤር 1:18, 19፤ 15:20፤ ሚክ 3:8
ሕዝ. 3:9ኢሳ 50:7
ሕዝ. 3:9ኤር 17:18
ሕዝ. 3:112ነገ 24:12, 14
ሕዝ. 3:11ሕዝ 2:5
ሕዝ. 3:12ሕዝ 8:3
ሕዝ. 3:13ሕዝ 1:24
ሕዝ. 3:13ሕዝ 10:16
ሕዝ. 3:15ሕዝ 1:3
ሕዝ. 3:15ኤር 23:9
ሕዝ. 3:17ኢሳ 21:8፤ 62:6፤ ኤር 6:17
ሕዝ. 3:17ኢሳ 58:1፤ ሕዝ 33:7
ሕዝ. 3:18ሥራ 2:40፤ 1ጢሞ 4:16
ሕዝ. 3:18ሕዝ 33:4
ሕዝ. 3:18ሕዝ 33:8
ሕዝ. 3:19ሕዝ 33:9፤ ሥራ 18:6፤ 20:26
ሕዝ. 3:20ሕዝ 18:24, 26፤ 33:12, 18
ሕዝ. 3:20ዘሌ 19:17፤ ሕዝ 33:6፤ ዕብ 13:17
ሕዝ. 3:21ምሳሌ 17:10፤ ሕዝ 33:14, 15፤ ያዕ 5:19, 20
ሕዝ. 3:23ሕዝ 1:1
ሕዝ. 3:23ሕዝ 1:27, 28
ሕዝ. 3:24ሕዝ 2:2፤ ዳን 10:19
ሕዝ. 3:27ሕዝ 24:27፤ 33:22
ሕዝ. 3:27ማቴ 11:15
ሕዝ. 3:27ኢሳ 30:9
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ሕዝቅኤል 3:1-27

ሕዝቅኤል

3 ከዚያም “የሰው ልጅ ሆይ፣ በፊትህ ያለውን ብላ።* ይህን ጥቅልል ብላ፤ ሄደህም ለእስራኤል ቤት ተናገር” አለኝ።+

2 ስለዚህ አፌን ከፈትኩ፤ እሱም ጥቅልሉን እንድበላው ሰጠኝ። 3 ከዚያም “የሰው ልጅ ሆይ፣ ይህን የሰጠሁህን ጥቅልል ብላ፤ ሆድህንም ሙላ” አለኝ። እኔም ጥቅልሉን መብላት ጀመርኩ፤ በአፌም ውስጥ እንደ ማር ጣፈጠኝ።+

4 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ ወደ እስራኤል ቤት ሂድ፤ ቃሌንም ንገራቸው። 5 የተላክኸው ወደ እስራኤል ቤት እንጂ ለመረዳት የሚያዳግት ቋንቋ ወይም የማይታወቅ ልሳን ወደሚናገር ሕዝብ አይደለምና። 6 ለመረዳት የሚያዳግት ቋንቋ ወይም የማይታወቅ ልሳን ወደሚናገሩና ቃላቸው ሊገባህ ወደማይችል ብዙ ሕዝቦች አልተላክህም። ወደ እነሱ ብልክህማ ኖሮ ይሰሙህ ነበር።+ 7 የእስራኤል ቤት ግን ሊሰሙህ አይፈልጉም፤ እኔን መስማት አይፈልጉምና።+ የእስራኤል ቤት ወገኖች ሁሉ ግትርና ልበ ደንዳና ናቸው።+ 8 እነሆ፣ ፊትህን ልክ እንደ እነሱ ፊት ጠንካራ አድርጌዋለሁ፤ ግንባርህንም ልክ እንደ እነሱ ግንባር አጠንክሬዋለሁ።+ 9 ግንባርህን እንደ አልማዝ፣ ከባልጩትም ይበልጥ ጠንካራ አድርጌዋለሁ።+ አትፍራቸው፤ ከፊታቸውም የተነሳ አትሸበር፤+ እነሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና።”

10 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ የምነግርህን ቃል ሁሉ በልብህ ያዝ፤ ደግሞም አዳምጥ። 11 በምርኮ ወደተወሰዱት ወገኖችህ*+ ሄደህ ንገራቸው። ቢሰሙም ባይሰሙም ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል’ በላቸው።”+

12 ከዚያም መንፈስ ወደ ላይ አነሳኝ፤+ ከበስተ ኋላዬም ታላቅ የጉምጉምታ ድምፅ “የይሖዋ ክብር ከስፍራው ይወደስ” ሲል ሰማሁ። 13 በዚያም የሕያዋን ፍጥረታቱ ክንፎች እርስ በርስ ሲነካኩ የሚያሰሙት ድምፅ፣+ በአጠገባቸው ያሉት መንኮራኩሮች*+ የሚያሰሙት ድምፅና የታላቅ ጉምጉምታ ድምፅ ነበር። 14 መንፈስም ወደ ላይ አንስቶ ወሰደኝ፤ እኔም ተማርሬና መንፈሴ ተቆጥቶ ሄድኩ፤ የይሖዋም ብርቱ እጅ በእኔ ላይ አርፋ ነበር። 15 ስለሆነም በቴልአቢብ፣ በኬባር ወንዝ+ አቅራቢያ ይኖሩ ወደነበሩት በግዞት የተወሰዱ ሰዎች ሄድኩ፤ እነሱም በሚኖሩበት ስፍራ ተቀመጥኩ፤ በድንጋጤ ፈዝዤም+ በመካከላቸው ሰባት ቀን ቆየሁ።

16 ሰባቱ ቀናት ካለፉ በኋላ የይሖዋ ቃል ወደ እኔ መጣ፦

17 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ለእስራኤል ቤት ጠባቂ አድርጌ ሾሜሃለሁ፤+ ከአፌ የሚወጣውንም ቃል ስትሰማ ማስጠንቀቂያዬን ንገራቸው።+ 18 ክፉውን ሰው ‘በእርግጥ ትሞታለህ’ ባልኩት ጊዜ ባታስጠነቅቀው፣ ደግሞም ክፉው ሰው በሕይወት ይኖር ዘንድ ከክፉ መንገዱ እንዲመለስ ማስጠንቀቂያ ባትሰጠው፣+ እሱ ክፉ በመሆኑ በሠራው በደል ይሞታል፤+ ደሙን ግን ከአንተ እጅ እሻዋለሁ።*+ 19 ሆኖም ክፉውን ሰው አስጠንቅቀኸው ከክፋቱና ከክፉ መንገዱ ባይመለስ፣ እሱ በሠራው በደል ይሞታል፤ አንተ ግን የገዛ ሕይወትህን* በእርግጥ ታድናለህ።+ 20 ይሁንና ጻድቅ ሰው ጽድቅ ማድረጉን ቢተውና መጥፎ ነገር ቢፈጽም፣* እኔ በፊቱ መሰናክል አስቀምጣለሁ፤ እሱም ይሞታል።+ ሳታስጠነቅቀው ከቀረህ በሠራው ኃጢአት የተነሳ ይሞታል፤ ያከናወነውም የጽድቅ ሥራ አይታወስም፤ ደሙን ግን ከአንተ እጅ እሻዋለሁ።*+ 21 ሆኖም ጻድቁን ሰው ኃጢአት እንዳይሠራ ብታስጠነቅቀውና ኃጢአት ባይሠራ፣ ማስጠንቀቂያውን በመስማቱ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል፤+ አንተም የገዛ ሕይወትህን* ታድናለህ።”

22 በዚያም የይሖዋ እጅ በእኔ ላይ ሆነች፤ እሱም “ተነስተህ ወደ ሸለቋማው ሜዳ ሂድ፤ በዚያም አናግርሃለሁ” አለኝ። 23 ስለዚህ ተነስቼ ወደ ሸለቋማው ሜዳ ሄድኩ፤ እነሆም በኬባር ወንዝ+ አጠገብ ያየሁትን ክብር የሚመስል የይሖዋ ክብር በዚያ ነበር፤+ እኔም በግንባሬ ተደፋሁ። 24 ከዚያም መንፈስ ወደ ውስጤ ገብቶ በእግሬ አቆመኝ፤+ አምላክም አናገረኝ፤ እንዲህም አለኝ፦

“ወደ ቤትህ ሄደህ በርህን ዘግተህ ተቀመጥ። 25 የሰው ልጅ ሆይ፣ አንተን በገመድ ይጠፍሩሃል፤ በመካከላቸውም እንዳትመላለስ ያስሩሃል። 26 እኔም ምላስህን ከላንቃህ ጋር አጣብቃለሁ፤ ዱዳም ትሆናለህ፤ ልትወቅሳቸውም አትችልም፤ ምክንያቱም እነሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸው። 27 በማናግርህ ጊዜ ግን አፍህን እከፍታለሁ፤ አንተም ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል’ በላቸው።+ የሚሰማ ይስማ፤+ የማይሰማም አይስማ፤ ምክንያቱም እነሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸው።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ