የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሕዝቅኤል 28
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ሕዝቅኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • በጢሮስ ንጉሥ ላይ የተነገረ ትንቢት (1-10)

        • “እኔ አምላክ ነኝ” (2, 9)

      • ስለ ጢሮስ ንጉሥ የተነገረ ሙሾ (11-19)

        • “በኤደን ነበርክ” (13)

        • “የተቀባህ፣ የምትጋርድ ኪሩብ” (14)

        • ‘ዓመፅ ተገኘብህ’ (15)

      • በሲዶና ላይ የተነገረ ትንቢት (20-24)

      • እስራኤል ተመልሳ ትቋቋማለች (25, 26)

ሕዝቅኤል 28:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 28:5
  • +ሕዝ 27:4

ሕዝቅኤል 28:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዳን 2:48

ሕዝቅኤል 28:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘካ 9:3

ሕዝቅኤል 28:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 23:1, 3፤ ሕዝ 27:12

ሕዝቅኤል 28:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 30:10, 11
  • +ኢሳ 23:9

ሕዝቅኤል 28:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ወደ መቃብር።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 27:26

ሕዝቅኤል 28:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሐዘን እንጉርጉሮ አሰማ።”

  • *

    ቃል በቃል “በማኅተም የጸደቀ ንድፍ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 28:3
  • +ሕዝ 27:3

ሕዝቅኤል 28:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 27:16

ሕዝቅኤል 28:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 14:13

ሕዝቅኤል 28:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዩ 3:4፤ አሞጽ 1:9

ሕዝቅኤል 28:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 10:11፤ 2ዜና 9:21፤ ሕዝ 27:12
  • +ኢዩ 3:6
  • +ኢሳ 23:9፤ ኤር 25:17, 22፤ 47:4፤ ኢዩ 3:8

ሕዝቅኤል 28:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 27:3
  • +ኢሳ 14:14
  • +ኢሳ 14:15

ሕዝቅኤል 28:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +አሞጽ 1:9, 10

ሕዝቅኤል 28:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 27:35
  • +ሕዝ 27:36

ሕዝቅኤል 28:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 23:4፤ ኤር 25:17, 22፤ ሕዝ 32:30

ሕዝቅኤል 28:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 26:6

ሕዝቅኤል 28:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 33:55፤ ኢያሱ 23:12, 13

ሕዝቅኤል 28:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 30:3፤ ኢሳ 11:12፤ ኤር 30:18፤ ሆሴዕ 1:11
  • +ኢሳ 5:16
  • +ዘፍ 28:13
  • +ኤር 23:8

ሕዝቅኤል 28:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 32:18፤ ኤር 23:6፤ ሆሴዕ 2:18
  • +ኢሳ 65:21, 22፤ ኤር 31:5፤ አሞጽ 9:14
  • +ኤር 30:16

ተዛማጅ ሐሳብ

ሕዝ. 28:2ሕዝ 28:5
ሕዝ. 28:2ሕዝ 27:4
ሕዝ. 28:3ዳን 2:48
ሕዝ. 28:4ዘካ 9:3
ሕዝ. 28:5ኢሳ 23:1, 3፤ ሕዝ 27:12
ሕዝ. 28:7ሕዝ 30:10, 11
ሕዝ. 28:7ኢሳ 23:9
ሕዝ. 28:8ሕዝ 27:26
ሕዝ. 28:12ሕዝ 28:3
ሕዝ. 28:12ሕዝ 27:3
ሕዝ. 28:13ሕዝ 27:16
ሕዝ. 28:14ኢሳ 14:13
ሕዝ. 28:15ኢዩ 3:4፤ አሞጽ 1:9
ሕዝ. 28:161ነገ 10:11፤ 2ዜና 9:21፤ ሕዝ 27:12
ሕዝ. 28:16ኢዩ 3:6
ሕዝ. 28:16ኢሳ 23:9፤ ኤር 25:17, 22፤ 47:4፤ ኢዩ 3:8
ሕዝ. 28:17ሕዝ 27:3
ሕዝ. 28:17ኢሳ 14:14
ሕዝ. 28:17ኢሳ 14:15
ሕዝ. 28:18አሞጽ 1:9, 10
ሕዝ. 28:19ሕዝ 27:35
ሕዝ. 28:19ሕዝ 27:36
ሕዝ. 28:21ኢሳ 23:4፤ ኤር 25:17, 22፤ ሕዝ 32:30
ሕዝ. 28:23ሕዝ 26:6
ሕዝ. 28:24ዘኁ 33:55፤ ኢያሱ 23:12, 13
ሕዝ. 28:25ዘዳ 30:3፤ ኢሳ 11:12፤ ኤር 30:18፤ ሆሴዕ 1:11
ሕዝ. 28:25ኢሳ 5:16
ሕዝ. 28:25ዘፍ 28:13
ሕዝ. 28:25ኤር 23:8
ሕዝ. 28:26ኢሳ 32:18፤ ኤር 23:6፤ ሆሴዕ 2:18
ሕዝ. 28:26ኢሳ 65:21, 22፤ ኤር 31:5፤ አሞጽ 9:14
ሕዝ. 28:26ኤር 30:16
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ሕዝቅኤል 28:1-26

ሕዝቅኤል

28 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ የጢሮስን ገዢ እንዲህ በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“ልብህ ከመታበዩ የተነሳ+ ‘እኔ አምላክ ነኝ።

በባሕሩ መካከል በአምላክ ዙፋን ላይ እቀመጣለሁ’ ትላለህ።+

በልብህ አምላክ እንደሆንክ የምታስብ ቢሆንም

አንተ ሰው እንጂ አምላክ አይደለህም።

 3 እነሆ፣ አንተ ከዳንኤል+ ይበልጥ ጥበበኛ እንደሆንክ ይሰማሃል።

ከአንተ የተሰወረ ሚስጥር እንደሌለ አድርገህ ታስባለህ።

 4 በጥበብህና በማስተዋልህ ራስህን አበልጽገሃል፤

በግምጃ ቤቶችህም ውስጥ ወርቅና ብር ማከማቸትህን ቀጥለሃል።+

 5 በንግድህ ስኬታማ ከመሆንህ የተነሳ ብዙ ሀብት አፈራህ፤+

ካካበትከውም ሀብት የተነሳ ልብህ ታበየ።”’

 6 “‘ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“በልብህ አምላክ እንደሆንክ ስለተሰማህ፣

 7 ከብሔራት መካከል እጅግ ጨካኝ የሆኑትን ባዕዳን አመጣብሃለሁ፤+

እነሱም በጥበብህ ውበት ላይ ሰይፋቸውን ይመዛሉ፤

ታላቅ ግርማህንም ያረክሳሉ።+

 8 ወደ ጉድጓድ* ያወርዱሃል፤

በተንጣለለውም ባሕር መካከል አስከፊ ሞት ትሞታለህ።+

 9 ያም ሆኖ በገዳይህ ፊት ‘እኔ አምላክ ነኝ’ ትላለህ?

በሚያረክሱህ ሰዎች እጅ ሰው እንጂ አምላክ አይደለህም።”’

10 ‘በባዕዳን እጅ፣ ያልተገረዙ ሰዎችን አሟሟት ትሞታለህ፤

እኔ ራሴ ተናግሬአለሁና’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”

11 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 12 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ስለ ጢሮስ ንጉሥ ሙሾ አውርድ፤* እንዲህም በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“አንተ ጥበብ የተሞላህና+ ፍጹም ውበት የተላበስክ+

የፍጽምና ተምሳሌት* ነበርክ።

13 በአምላክ የአትክልት ስፍራ በኤደን ነበርክ።

በከበሩ ድንጋዮች ሁሉ

ይኸውም በሩቢ፣ በቶጳዝዮን፣ በኢያስጲድ፣ በክርስቲሎቤ፣ በኦኒክስ፣ በጄድ፣ በሰንፔር፣ በበሉርና+ በመረግድ አጊጠህ ነበር፤

እነዚህ የከበሩ ድንጋዮች የተሰኩባቸው ማቀፊያዎችም ከወርቅ የተሠሩ ነበሩ።

በተፈጠርክበት ቀን ተዘጋጅተው ነበር።

14 የተቀባህ፣ የምትጋርድ ኪሩብ አድርጌ ሾምኩህ።

በአምላክ ቅዱስ ተራራ ላይ ነበርክ፤+ በእሳታማ ድንጋዮችም መካከል ትመላለስ ነበር።

15 ከተፈጠርክበት ቀን አንስቶ ዓመፅ እስከተገኘብህ ጊዜ ድረስ

በመንገድህ ሁሉ ምንም እንከን አልነበረብህም።+

16 ከንግድህ ብዛት የተነሳ+

ውስጥህ በዓመፅ ተሞላ፤ ኃጢአትም መሥራት ጀመርክ።+

የምትጋርድ ኪሩብ ሆይ፣ እንደ ርኩስ ቆጥሬ ከአምላክ ተራራ እጥልሃለሁ፤

ከእሳታማዎቹ ድንጋዮች መካከልም አስወግድሃለሁ።+

17 በውበትህ+ ምክንያት ልብህ ታበየ።

ከታላቅ ግርማህ የተነሳ ጥበብህን አበላሸህ።+

ወደ ምድር እጥልሃለሁ።+

በነገሥታት ፊት ትዕይንት አደርግሃለሁ።

18 ታላቅ በደል በመፈጸምና በንግድ ሥራ በማጭበርበር መቅደሶችህን አረከስክ።

እኔም ከመካከልህ እሳት እንዲወጣ አደርጋለሁ፤ እሳቱም ይበላሃል።+

በሚያዩህ ሁሉ ፊት በምድር ላይ አመድ አደርግሃለሁ።

19 ከሕዝቦች መካከል የሚያውቁህ ሁሉ በመገረም አተኩረው ያዩሃል።+

ፍጻሜህ ድንገተኛና አስከፊ ይሆናል፤

ደግሞም ለዘላለም ከሕልውና ውጭ ትሆናለህ።”’”+

20 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 21 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን ወደ ሲዶና+ አዙረህ በእሷ ላይ ትንቢት ተናገር። 22 እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“ሲዶና ሆይ፣ እነሆ እኔ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ፤ በመካከልሽም እከበራለሁ፤

ደግሞም በእሷ ላይ የፍርድ እርምጃ በምወስድበትና በእሷ አማካኝነት በምቀደስበት ጊዜ ሰዎች እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።

23 በእሷ ላይ ቸነፈር እሰዳለሁ፤ በጎዳናዎቿም ላይ ደም ይፈስሳል።

ከየአቅጣጫው ሰይፍ በሚመጣባት ጊዜ የታረዱት ሰዎች በመካከሏ ይወድቃሉ፤

እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።+

24 “‘“ከዚያ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ አደገኛ በሆነ አሜኬላና በሚያሠቃይ እሾህ+ ይኸውም በሚንቁት ብሔራት ዳግመኛ አይከበብም፤ ሰዎችም እኔ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”’

25 “‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤልን ቤት ሰዎች ከተበተኑባቸው ሕዝቦች መካከል ዳግመኛ በምሰበስባቸው ጊዜ+ በብሔራት ፊት በእነሱ መካከል እቀደሳለሁ።+ እነሱም ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት+ ምድራቸው ላይ ይኖራሉ።+ 26 በላይዋ ላይ ያለስጋት ይቀመጣሉ፤+ ቤቶችንም ይሠራሉ፤ ወይንንም ይተክላሉ፤+ ደግሞም በዙሪያቸው ባሉት በሚንቋቸው ሁሉ ላይ የፍርድ እርምጃ በምወስድበት ጊዜ ያለስጋት ይኖራሉ፤+ እኔም አምላካቸው ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”’”

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ