የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሕዝቅኤል 30
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ሕዝቅኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • በግብፅ ላይ የተነገረ ትንቢት (1-19)

        • ናቡከደነጾር ጥቃት እንደሚሰነዝር ትንቢት ተነገረ (10)

      • የፈርዖን ክንድ ተሰበረ (20-26)

ሕዝቅኤል 30:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +አብ 15
  • +ሕዝ 32:7
  • +መዝ 110:6

ሕዝቅኤል 30:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 32:11, 12

ሕዝቅኤል 30:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ከሌሎች ብሔራት የተውጣጡ ሁሉ።”

  • *

    ከግብፅ ጋር የተባበሩትን እስራኤላውያን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሶፎ 2:12
  • +ናሆም 3:8, 9

ሕዝቅኤል 30:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 30:18
  • +ኤር 44:1
  • +ሕዝ 29:10

ሕዝቅኤል 30:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 46:19፤ ሕዝ 29:12፤ 32:18

ሕዝቅኤል 30:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በናቡከደረጾር።” ናቡከደነጾር የሚለው ስም የሚጻፍበት ሌላው መንገድ ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 29:19፤ 32:11

ሕዝቅኤል 30:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕን 1:6
  • +ሕዝ 29:5

ሕዝቅኤል 30:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 29:3
  • +ሕዝ 31:12

ሕዝቅኤል 30:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል “ፋንድያ” ከሚለው ቃል ጋር ዝምድና ሊኖረው የሚችል ሲሆን ንቀትን ለማመልከት ተሠርቶበታል።

  • *

    ወይም “የሜምፊስ።”

  • *

    ወይም “አለቃ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 43:12፤ 46:14
  • +ኤር 46:5

ሕዝቅኤል 30:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቴብስን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 10:13, 14፤ ኤር 44:1
  • +ኤር 46:25

ሕዝቅኤል 30:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሜምፊስ።”

ሕዝቅኤል 30:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ሂልያፖሊስን ያመለክታል።

ሕዝቅኤል 30:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 30:8
  • +ኤር 46:20፤ ሕዝ 31:18
  • +ኤር 46:19

ሕዝቅኤል 30:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 46:25፤ ሕዝ 29:3
  • +2ነገ 24:7፤ ኤር 46:2
  • +ኤር 46:21

ሕዝቅኤል 30:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 29:12

ሕዝቅኤል 30:24

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ለባቢሎን ንጉሥ ኃይል እጨምርለታለሁ።”

  • *

    በባቢሎን ንጉሥ ፊት ማለት ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 27:6
  • +ሕዝ 32:11, 12

ሕዝቅኤል 30:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 29:19, 20

ሕዝቅኤል 30:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 29:12

ተዛማጅ ሐሳብ

ሕዝ. 30:3አብ 15
ሕዝ. 30:3ሕዝ 32:7
ሕዝ. 30:3መዝ 110:6
ሕዝ. 30:4ሕዝ 32:11, 12
ሕዝ. 30:5ሶፎ 2:12
ሕዝ. 30:5ናሆም 3:8, 9
ሕዝ. 30:6ሕዝ 30:18
ሕዝ. 30:6ኤር 44:1
ሕዝ. 30:6ሕዝ 29:10
ሕዝ. 30:7ኤር 46:19፤ ሕዝ 29:12፤ 32:18
ሕዝ. 30:10ሕዝ 29:19፤ 32:11
ሕዝ. 30:11ዕን 1:6
ሕዝ. 30:11ሕዝ 29:5
ሕዝ. 30:12ሕዝ 29:3
ሕዝ. 30:12ሕዝ 31:12
ሕዝ. 30:13ኤር 43:12፤ 46:14
ሕዝ. 30:13ኤር 46:5
ሕዝ. 30:14ዘፍ 10:13, 14፤ ኤር 44:1
ሕዝ. 30:14ኤር 46:25
ሕዝ. 30:18ሕዝ 30:8
ሕዝ. 30:18ኤር 46:20፤ ሕዝ 31:18
ሕዝ. 30:18ኤር 46:19
ሕዝ. 30:22ኤር 46:25፤ ሕዝ 29:3
ሕዝ. 30:222ነገ 24:7፤ ኤር 46:2
ሕዝ. 30:22ኤር 46:21
ሕዝ. 30:23ሕዝ 29:12
ሕዝ. 30:24ኤር 27:6
ሕዝ. 30:24ሕዝ 32:11, 12
ሕዝ. 30:25ሕዝ 29:19, 20
ሕዝ. 30:26ሕዝ 29:12
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ሕዝቅኤል 30:1-26

ሕዝቅኤል

30 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“ዋይ ዋይ በሉ፤ ‘ቀኑ ስለቀረበ ወዮ!’

 3 ቀኑ ቀርቧልና፤ አዎ፣ የይሖዋ ቀን ቀርቧል።+

የደመናት ቀን፣+ በብሔራትም ላይ የሚፈረድበት ቀን ይሆናል።+

 4 ሰይፍ በግብፅ ላይ ይመጣል፤ የታረዱት በግብፅ ሲወድቁ፣

ሀብቷ ሲወሰድ እንዲሁም መሠረቶቿ ሲፈራርሱ ኢትዮጵያ በሽብር ትዋጣለች።+

 5 ኢትዮጵያ፣+ ፑጥ፣+ ሉድና ድብልቅ ሕዝቦች ሁሉ*

እንዲሁም ኩብ፣ ከቃል ኪዳኑ ምድር ልጆች* ጋር

ሁሉም በሰይፍ ይወድቃሉ።”’

 6 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

‘ለግብፅ ድጋፍ የሚሰጡም ይወድቃሉ፤

የምትታበይበት ኃይሏም ይወገዳል።’+

“‘ከሚግዶል+ እስከ ሰዌኔ+ በምድሪቱ ላይ በሰይፍ ይወድቃሉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 7 ‘ከሌሎች አገሮች በከፋ ሁኔታ ባድማ ይሆናሉ፤ ከተሞቿም ከሌሎች ከተሞች በከፋ ሁኔታ ይወድማሉ።+ 8 በግብፅም ላይ እሳት በማነድበትና ተባባሪዎቿ ሁሉ በሚደቁበት ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። 9 በዚያን ቀን በራሷ የምትታመነውን ኢትዮጵያን ለማንቀጥቀጥ መልእክተኞችን በመርከብ እልካለሁ፤ ግብፅ በምትጠፋበት ቀን በሽብር ይዋጣሉ፤ ቀኑ በእርግጥ ይመጣልና።’

10 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ስፍር ቁጥር የሌለውን የግብፅ ሕዝብ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር* እጅ አጠፋለሁ።+ 11 ከብሔራት መካከል እጅግ ጨካኝ የሆኑት፣ እሱና ሠራዊቱ+ ምድሪቱን ለማውደም ይመጣሉ። እነሱም በግብፅ ላይ ሰይፋቸውን ይመዛሉ፤ ምድሪቱንም ሬሳ በሬሳ ያደርጋሉ።+ 12 የአባይን የመስኖ ቦዮች አደርቃለሁ፤+ ምድሪቱንም ለክፉ ሰዎች እሸጣለሁ። ምድሪቱና በውስጧ ያለው ሁሉ በባዕዳን እጅ እንዲጠፉ አደርጋለሁ።+ እኔ ይሖዋ ራሴ ይህን ተናግሬአለሁ።’

13 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አስጸያፊ የሆኑትንም ጣዖቶች* አጠፋለሁ፤ ከንቱ የሆኑትንም የኖፍ*+ አማልክት አስወግዳለሁ። ከእንግዲህ ከግብፅ ምድር የሚወጣ ገዢ* አይኖርም፤ በግብፅም ምድር ፍርሃት እሰዳለሁ።+ 14 ጳትሮስን+ ባድማ አደርጋለሁ፤ በጾዓን እሳት አነዳለሁ፤ ደግሞም በኖእ*+ ላይ የፍርድ እርምጃ እወስዳለሁ። 15 የግብፅ ምሽግ በሆነችው በሲን ላይ ቁጣዬን አፈስሳለሁ፤ የኖእንም ሕዝብ አጠፋለሁ። 16 በግብፅ ላይ እሳት አነዳለሁ፤ ሲን በሽብር ትዋጣለች፤ ኖእ ቅጥሯ ይፈርሳል፤ ኖፍ* ደግሞ በጠራራ ፀሐይ ጥቃት ይሰነዘርባታል! 17 የኦንና* የጲበሰት ወጣቶች በሰይፍ ይወድቃሉ፤ የከተሞቹም ነዋሪዎች በግዞት ይወሰዳሉ። 18 በዚያ የግብፅን ቀንበር በምሰብርበት ጊዜ በጣፍነስ ቀኑ ይጨልማል።+ የምትታበይበት ኃይሏ ይጠፋል፤+ ደመናት ይሸፍኗታል፤ የከተሞቿም ነዋሪዎች በግዞት ይወሰዳሉ።+ 19 በግብፅ ላይ የፍርድ እርምጃ እወስዳለሁ፤ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’”

20 በ11ኛውም ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በሰባተኛው ቀን፣ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 21 “የሰው ልጅ ሆይ፣ የግብፅን ንጉሥ የፈርዖንን ክንድ ሰብሬአለሁ፤ እንዲድን አይታሰርም፤ ወይም ጠንክሮ ሰይፍ እንዲይዝ በጨርቅ አይጠቀለልም።”

22 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ እኔ በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ላይ ተነስቻለሁ፤+ ብርቱውንና የተሰበረውን፣ ሁለቱንም ክንዶቹን እሰብራለሁ፤+ ሰይፉም ከእጁ ላይ እንዲወድቅ አደርጋለሁ።+ 23 ከዚያም ግብፃውያንን በብሔራት መካከል እበትናቸዋለሁ፤ በአገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ።+ 24 የባቢሎንን ንጉሥ ክንዶች አበረታለሁ፤*+ ሰይፌንም አስጨብጠዋለሁ፤+ የፈርዖንን ክንዶች እሰብራለሁ፤ እሱም ሊሞት እያጣጣረ እንዳለ ሰው በፊቱ* እጅግ ያቃስታል። 25 የባቢሎንን ንጉሥ ክንዶች አበረታለሁ፤ የፈርዖን ክንዶች ግን ይዝላሉ፤ ሰይፌንም ለባቢሎን ንጉሥ ሳስጨብጠውና በግብፅ ምድር ላይ ሲሰነዝረው እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።+ 26 ግብፃውያንንም በብሔራት መካከል እበትናቸዋለሁ፤ በአገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ፤+ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’”

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ