የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሕዝቅኤል 4
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ሕዝቅኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • የኢየሩሳሌም ከበባ በምሳሌያዊ ሁኔታ ተገለጸ (1-17)

        • በደሉን ለ390 ቀናትና ለ40 ቀናት ይሸከማል (4-7)

ሕዝቅኤል 4:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 24:11፤ ኤር 39:1
  • +2ነገ 25:1
  • +ኤር 6:6፤ 32:24
  • +ሕዝ 21:22

ሕዝቅኤል 4:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 12:6፤ 24:24

ሕዝቅኤል 4:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በላዩ ላይ።” የሕዝቅኤልን ግራ ጎን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 17:21

ሕዝቅኤል 4:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 14:34፤ 1ነገ 12:19, 20

ሕዝቅኤል 4:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 23:27

ሕዝቅኤል 4:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 52:4

ሕዝቅኤል 4:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 4:5

ሕዝቅኤል 4:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወደ 230 ግራም ገደማ ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

ሕዝቅኤል 4:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወደ 0.6 ሊትር ገደማ ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

ሕዝቅኤል 4:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሆሴዕ 9:3

ሕዝቅኤል 4:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሴ . . . በልታ የረከሰችበት ጊዜ የለም።”

  • *

    ወይም “የገማም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 22:31፤ ዘሌ 7:24፤ 11:40
  • +ዘዳ 14:3፤ ኢሳ 65:4፤ 66:17

ሕዝቅኤል 4:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የዳቦ በትሮቹን እሰብራለሁ።” ዳቦ ለማስቀመጥ የሚያገለግሉ በትሮችን የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 26:26፤ ኢሳ 3:1፤ ሕዝ 5:16
  • +2ነገ 25:3፤ ኤር 37:21፤ ሰቆ 1:11፤ 4:9፤ 5:9, 10
  • +ሕዝ 12:18

ተዛማጅ ሐሳብ

ሕዝ. 4:22ነገ 24:11፤ ኤር 39:1
ሕዝ. 4:22ነገ 25:1
ሕዝ. 4:2ኤር 6:6፤ 32:24
ሕዝ. 4:2ሕዝ 21:22
ሕዝ. 4:3ሕዝ 12:6፤ 24:24
ሕዝ. 4:42ነገ 17:21
ሕዝ. 4:5ዘኁ 14:34፤ 1ነገ 12:19, 20
ሕዝ. 4:62ነገ 23:27
ሕዝ. 4:7ኤር 52:4
ሕዝ. 4:9ሕዝ 4:5
ሕዝ. 4:13ሆሴዕ 9:3
ሕዝ. 4:14ዘፀ 22:31፤ ዘሌ 7:24፤ 11:40
ሕዝ. 4:14ዘዳ 14:3፤ ኢሳ 65:4፤ 66:17
ሕዝ. 4:16ዘሌ 26:26፤ ኢሳ 3:1፤ ሕዝ 5:16
ሕዝ. 4:162ነገ 25:3፤ ኤር 37:21፤ ሰቆ 1:11፤ 4:9፤ 5:9, 10
ሕዝ. 4:16ሕዝ 12:18
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ሕዝቅኤል 4:1-17

ሕዝቅኤል

4 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ አንድ ጡብ ወስደህ በፊትህ አስቀምጥ። በላዩም ላይ የኢየሩሳሌምን ከተማ ቅረጽበት። 2 ከተማዋን ክበብ፤+ ለከበባ የሚያገለግል ግንብ ሥራባት፤+ የአፈር ቁልል ደልድልባት፤+ የጦር ሰፈሮችን ሥራባት እንዲሁም በዙሪያዋ የመደርመሻ መሣሪያዎችን ደግንባት።+ 3 የብረት ምጣድ ወስደህ በአንተና በከተማዋ መካከል እንደ ብረት ቅጥር አቁመው። ፊትህንም በእሷ ላይ አዙር፤ ከተማዋም ትከበባለች፤ አንተም ትከባታለህ። ይህ ለእስራኤል ቤት ምልክት ይሆናል።+

4 “ከዚያም በግራ ጎንህ ትተኛለህ፤ የእስራኤልንም ቤት በደል በላይህ ላይ* ታኖራለህ።+ በጎንህ በተኛህበት ቀን ቁጥር በደላቸውን ትሸከማለህ። 5 እኔም በደል በፈጸሙባቸው ዓመታት መጠን 390 ቀናት በአንተ ላይ እመድባለሁ፤+ አንተም የእስራኤልን ቤት በደል ትሸከማለህ። 6 እነዚህንም ቀናት ማጠናቀቅ ይኖርብሃል።

“ከዚያም ለሁለተኛ ጊዜ በቀኝ ጎንህ ትተኛለህ፤ የይሁዳንም ቤት በደል+ ለ40 ቀናት ትሸከማለህ። ለአንድ ዓመት አንድ ቀን፣ ለአንድ ዓመት አንድ ቀን ሰጥቼሃለሁ። 7 ክንድህን ገልጠህ ፊትህን ወደ ኢየሩሳሌም ከበባ+ ታዞራለህ፤ በእሷም ላይ ትንቢት ትናገራለህ።

8 “እነሆ፣ የከበባህን ጊዜ እስክታጠናቅቅ ድረስ ከአንዱ ጎንህ ወደ ሌላው መገላበጥ እንዳትችል በገመድ አስርሃለሁ።

9 “አንተም ስንዴ፣ ገብስ፣ ባቄላ፣ ምስር፣ ማሽላና አጃ ወስደህ በአንድ ዕቃ ውስጥ አስቀምጣቸው፤ ለራስህም ዳቦ ጋግር። በጎንህ በምትተኛባቸው 390 ቀናት ትበላዋለህ።+ 10 በየቀኑ 20 ሰቅል* እየመዘንክ ትበላለህ። በየተወሰነ ጊዜ ትበላዋለህ።

11 “ደግሞም የሂን አንድ ስድስተኛ* ለክተህ ውኃ ትጠጣለህ። በየተወሰነ ጊዜ ትጠጣዋለህ።

12 “የገብስ ሙልሙል እንደምትበላ ትበላዋለህ፤ የደረቀን የሰው ዓይነ ምድር እንደ ማገዶ ተጠቅመህ በፊታቸው ትጋግረዋለህ።” 13 ከዚያም ይሖዋ “ልክ እንደዚሁ እስራኤላውያንም እነሱን በምበትንባቸው ብሔራት መካከል የረከሰ ምግብ ይበላሉ” አለ።+

14 ከዚያም እንዲህ አልኩ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ይህስ አይሁን! እኔ* ከልጅነቴ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ሞቶ የተገኘም ሆነ አውሬ የቦጫጨቀው እንስሳ ሥጋ በልቼ የረከስኩበት ጊዜ የለም፤+ የረከሰም * ሥጋ ወደ አፌ ገብቶ አያውቅም።”+

15 እሱም እንዲህ አለኝ፦ “መልካም፣ በሰው ዓይነ ምድር ፋንታ የከብት ኩበት እንድትጠቀም ፈቅጄልሃለሁ፤ የምትበላውንም ዳቦ በእሱ ትጋግራለህ።” 16 ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ በኢየሩሳሌም የምግብ አቅርቦቱ እንዲቋረጥ አደርጋለሁ፤*+ እነሱም እየተመጠነ የሚሰጣቸውን ዳቦ በሚዛን እየለኩ በከፍተኛ ጭንቀት ይበላሉ፤+ እየተመጠነ የሚሰጣቸውንም ውኃ እየለኩ በስጋት ይጠጣሉ።+ 17 ይህም የሚሆነው ምግብና ውኃ አጥተው እርስ በርስ በድንጋጤ እንዲተያዩ እንዲሁም ከበደላቸው የተነሳ እንዲመነምኑ ነው።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ