የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሕዝቅኤል 39
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ሕዝቅኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • በጎግና በወታደሮቹ ላይ የሚደርስ ጥፋት (1-10)

      • በሃሞን ጎግ ሸለቆ የሚፈጸም ቀብር (11-20)

      • የእስራኤል መልሶ መቋቋም (21-29)

        • የአምላክ መንፈስ በእስራኤል ላይ ይፈስሳል (29)

ሕዝቅኤል 39:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ዋነኛ ገዢ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 38:2
  • +ሕዝ 27:13፤ 32:26

ሕዝቅኤል 39:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 38:4, 15

ሕዝቅኤል 39:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 38:21
  • +ራእይ 19:17, 18

ሕዝቅኤል 39:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 25:33

ሕዝቅኤል 39:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 38:22

ሕዝቅኤል 39:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 6:3
  • +ሕዝ 38:16

ሕዝቅኤል 39:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    አብዛኛውን ጊዜ ቀስተኞች የሚይዙት ትንሽ ጋሻ።

  • *

    “የጦር ዱላዎቹንና” ማለትም ሊሆን ይችላል። ጫፉ ሹል የሆነ የጦር መሣሪያ ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 46:9

ሕዝቅኤል 39:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ስፍር ቁጥር የሌለው የጎግ ሠራዊት ሸለቆ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 38:2
  • +ሕዝ 39:15

ሕዝቅኤል 39:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 21:22, 23

ሕዝቅኤል 39:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 38:16

ሕዝቅኤል 39:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 39:11

ሕዝቅኤል 39:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ስፍር ቁጥር የሌለው ሠራዊት” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 39:12

ሕዝቅኤል 39:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 34:6-8፤ ኤር 46:10፤ ሶፎ 1:7
  • +ራእይ 19:17, 18

ሕዝቅኤል 39:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 38:4-6፤ ሐጌ 2:22፤ ራእይ 19:17, 18

ሕዝቅኤል 39:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እጅ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 7:4፤ 14:4፤ ኢሳ 37:20፤ ሕዝ 38:16፤ ሚል 1:11

ሕዝቅኤል 39:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 7:21, 22
  • +ዘዳ 31:18፤ ኢሳ 59:2
  • +ዘሌ 26:24, 25፤ ዘዳ 32:30፤ መዝ 106:40, 41

ሕዝቅኤል 39:25

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ለቅዱስ ስሜ እቀናለሁ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 30:3፤ ሕዝ 34:13
  • +ሆሴዕ 1:11፤ ዘካ 1:16
  • +ሕዝ 36:21

ሕዝቅኤል 39:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዳን 9:16
  • +ዘሌ 26:5, 6

ሕዝቅኤል 39:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 30:10፤ አሞጽ 9:14፤ ሶፎ 3:20
  • +ኢሳ 5:16፤ ሕዝ 36:23

ሕዝቅኤል 39:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 30:4

ሕዝቅኤል 39:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 45:17፤ 54:8፤ ኤር 29:14
  • +ኢሳ 32:14, 15፤ ኢዩ 2:28

ተዛማጅ ሐሳብ

ሕዝ. 39:1ሕዝ 38:2
ሕዝ. 39:1ሕዝ 27:13፤ 32:26
ሕዝ. 39:2ሕዝ 38:4, 15
ሕዝ. 39:4ሕዝ 38:21
ሕዝ. 39:4ራእይ 19:17, 18
ሕዝ. 39:5ኤር 25:33
ሕዝ. 39:6ሕዝ 38:22
ሕዝ. 39:7ኢሳ 6:3
ሕዝ. 39:7ሕዝ 38:16
ሕዝ. 39:9መዝ 46:9
ሕዝ. 39:11ሕዝ 38:2
ሕዝ. 39:11ሕዝ 39:15
ሕዝ. 39:12ዘዳ 21:22, 23
ሕዝ. 39:13ሕዝ 38:16
ሕዝ. 39:15ሕዝ 39:11
ሕዝ. 39:16ሕዝ 39:12
ሕዝ. 39:17ኢሳ 34:6-8፤ ኤር 46:10፤ ሶፎ 1:7
ሕዝ. 39:17ራእይ 19:17, 18
ሕዝ. 39:20ሕዝ 38:4-6፤ ሐጌ 2:22፤ ራእይ 19:17, 18
ሕዝ. 39:21ዘፀ 7:4፤ 14:4፤ ኢሳ 37:20፤ ሕዝ 38:16፤ ሚል 1:11
ሕዝ. 39:232ዜና 7:21, 22
ሕዝ. 39:23ዘዳ 31:18፤ ኢሳ 59:2
ሕዝ. 39:23ዘሌ 26:24, 25፤ ዘዳ 32:30፤ መዝ 106:40, 41
ሕዝ. 39:25ኤር 30:3፤ ሕዝ 34:13
ሕዝ. 39:25ሆሴዕ 1:11፤ ዘካ 1:16
ሕዝ. 39:25ሕዝ 36:21
ሕዝ. 39:26ዳን 9:16
ሕዝ. 39:26ዘሌ 26:5, 6
ሕዝ. 39:27ኤር 30:10፤ አሞጽ 9:14፤ ሶፎ 3:20
ሕዝ. 39:27ኢሳ 5:16፤ ሕዝ 36:23
ሕዝ. 39:28ዘዳ 30:4
ሕዝ. 39:29ኢሳ 45:17፤ 54:8፤ ኤር 29:14
ሕዝ. 39:29ኢሳ 32:14, 15፤ ኢዩ 2:28
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ሕዝቅኤል 39:1-29

ሕዝቅኤል

39 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ በጎግ ላይ ትንቢት ተናገር፤+ እንዲህም በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የመሼቅና የቱባል+ ዋና አለቃ* የሆንከው ጎግ ሆይ፣ እኔ በአንተ ላይ ተነስቻለሁ። 2 እመልስሃለሁ፤ ደግሞም እነዳሃለሁ፤ ራቅ ካለውም የሰሜን ምድር አምጥቼ+ ወደ እስራኤል ተራሮች እወስድሃለሁ። 3 በግራ እጅህ ያለውን ደጋንህንም ሆነ በቀኝ እጅህ የያዝካቸውን ፍላጻዎችህን አስጥልሃለሁ። 4 አንተና ወታደሮችህ ሁሉ እንዲሁም ከአንተ ጋር የሚሆኑት ሕዝቦች በእስራኤል ተራሮች ላይ ትወድቃላችሁ።+ ለተለያዩ አዳኝ አሞሮች ሁሉና ለዱር አራዊት መብል አድርጌ እሰጥሃለሁ።”’+

5 “‘አውላላ ሜዳ ላይ ትወድቃለህ፤+ እኔ ራሴ ተናግሬአለሁና’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።

6 “‘በማጎግና ያለስጋት በደሴቶች በሚኖሩት ላይም እሳት እሰዳለሁ፤+ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። 7 ቅዱስ ስሜ በሕዝቤ በእስራኤል መካከል እንዲታወቅ አደርጋለሁ፤ ከእንግዲህ ቅዱስ ስሜ እንዲረክስ አልፈቅድም፤ ብሔራትም እኔ ይሖዋ፣ የእስራኤል ቅዱስ+ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’+

8 “‘አዎ፣ በትንቢት የተነገረው ነገር ይመጣል፤ ደግሞም ይፈጸማል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘ያ ያልኩት ቀን ይህ ነው። 9 በእስራኤል ከተሞች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ወጥተው፣ የጦር መሣሪያዎቹን ይኸውም ትናንሾቹንና* ትላልቆቹን ጋሻዎች፣ ደጋኖቹን፣ ፍላጻዎቹን፣ የጦር ቆመጦቹንና* ጦሮቹን እሳት ያነዱባቸዋል። ለሰባት ዓመታትም እሳት ለማንደድ ይጠቀሙባቸዋል።+ 10 የጦር መሣሪያዎቹን እሳት ለማንደድ ስለሚጠቀሙባቸው ከሜዳ እንጨት መልቀም ወይም ከጫካ ማገዶ መሰብሰብ አያስፈልጋቸውም።’

“‘የበዘበዟቸውን ይበዘብዛሉ፤ የመዘበሯቸውንም ይመዘብራሉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።

11 “‘በዚያ ቀን በእስራኤል ምድር፣ ከባሕሩ በስተ ምሥራቅ በሚጓዙት ሰዎች ሸለቆ ለጎግ+ የመቃብር ቦታ እሰጠዋለሁ፤ በዚያ የሚያልፉትንም ሰዎች መንገድ ይዘጋል። ጎግንና ስፍር ቁጥር የሌለውን ሠራዊቱን ሁሉ በዚያ ይቀብራሉ፤ ሸለቆውንም የሃሞን ጎግ ሸለቆ*+ ብለው ይጠሩታል። 12 የእስራኤል ቤት ሰዎች እነሱን ቀብረው ምድሪቱን ለማንጻት ሰባት ወር ይፈጅባቸዋል።+ 13 የምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ እነሱን ይቀብራል፤ ይህም ራሴን በማስከብርበት ቀን ዝና ያስገኝላቸዋል’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።

14 “‘ምድሪቱ ትነጻ ዘንድ፣ ሰዎች በየጊዜው በምድሪቱ ላይ እንዲያልፉና በምድሪቱ ላይ የቀሩትን አስከሬኖች እንዲቀብሩ ይመደባሉ። ለሰባት ወራትም ፍለጋቸውን ይቀጥላሉ። 15 በምድሪቱ ላይ የሚያልፉት ሰዎች የሰው አፅም ሲያዩ በአጠገቡ ምልክት ያደርጋሉ። ከዚያም እንዲቀብሩ የተመደቡት አፅሙን በሃሞን ጎግ ሸለቆ+ ይቀብሩታል። 16 በዚያም ሃሞና* ተብላ የምትጠራ ከተማ ትኖራለች። እነሱም ምድሪቱን ያነጻሉ።’+

17 “አንተም፣ የሰው ልጅ ሆይ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ለተለያዩ ወፎችና ለዱር አራዊት ሁሉ እንዲህ በል፦ “አንድ ላይ ተሰብስባችሁ ኑ። ለእናንተ በማዘጋጀው መሥዋዕቴ ዙሪያ ተሰብሰቡ፤ ይህም በእስራኤል ተራሮች ላይ የሚዘጋጅ ታላቅ መሥዋዕት ነው።+ ሥጋ ትበላላችሁ፤ ደምም ትጠጣላችሁ።+ 18 የኃያላንን ሥጋ ትበላላችሁ፤ የምድርንም አለቆች ደም ትጠጣላችሁ፤ እነሱ አውራ በጎች፣ ጠቦቶች፣ አውራ ፍየሎችና ወይፈኖች ሲሆኑ ሁሉም የሰቡ የባሳን ከብቶች ናቸው። 19 እናንተም እኔ ከማዘጋጅላችሁ መሥዋዕት፣ እስክትጠግቡ ድረስ ስብ ትሰለቅጣላችሁ፤ እስክትሰክሩም ደም ትጠጣላችሁ።”’

20 “‘በማዕዴም ፈረሶችንና ሠረገለኞችን እንዲሁም ኃያላን ሰዎችንና ሁሉንም ዓይነት ተዋጊዎች እስክትጠግቡ ትበላላችሁ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።

21 “‘በብሔራት መካከል ክብሬን እገልጣለሁ፤ ብሔራት ሁሉ የወሰድኩትን የፍርድ እርምጃና በእነሱ መካከል የገለጥኩትን ኃይል* ያያሉ።+ 22 ከዚያ ቀን አንስቶ የእስራኤል ቤት ሰዎች እኔ አምላካቸው ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። 23 ብሔራትም የእስራኤል ቤት ሰዎች በግዞት የተወሰዱት በገዛ ራሳቸው በደል ይኸውም ለእኔ ታማኝ ሳይሆኑ በመቅረታቸው እንደሆነ ያውቃሉ።+ ስለዚህ ፊቴን ከእነሱ ሰወርኩ፤+ ለጠላቶቻቸውም አሳልፌ ሰጠኋቸው፤+ ሁሉም በሰይፍ ወደቁ። 24 እንደ ርኩሰታቸውና እንደ በደላቸው መጠን አደረግኩባቸው፤ ፊቴንም ከእነሱ ሰወርኩ።’

25 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በምርኮ የተወሰዱትን የያዕቆብ ወገኖች እመልሳለሁ፤+ ለእስራኤል ቤት ሰዎች ሁሉ ምሕረት አደርግላቸዋለሁ፤+ የስሜንም ቅድስና አስከብራለሁ።*+ 26 ለእኔ ታማኝ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ውርደት ከደረሰባቸው+ በኋላ የሚያስፈራቸው ሳይኖር በምድራቸው ላይ ያለስጋት ይኖራሉ።+ 27 ከሕዝቦች መካከል መልሼ ሳመጣቸውና ከጠላቶቻቸው አገሮች ስሰበስባቸው፣+ በብዙ ብሔራት ፊት፣ በመካከላቸው ራሴን እቀድሳለሁ።’+

28 “‘በብሔራት መካከል በግዞት እንዲኖሩ ሳደርግና ከዚያም አንዳቸውንም ሳላስቀር ወደ ገዛ ምድራቸው መልሼ ሳመጣቸው፣ እኔ አምላካቸው ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።+ 29 ከእንግዲህ ፊቴን ከእስራኤል ቤት ሰዎች አልሰውርም፤+ በእነሱ ላይ መንፈሴን አፈሳለሁና’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ