የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሕዝቅኤል 5
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ሕዝቅኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • ኢየሩሳሌም ጥፋት እንደሚደርስባት በምሳሌያዊ ሁኔታ ተገለጸ (1-17)

        • ነቢዩ ከተላጨ በኋላ ፀጉሩን ሦስት ቦታ ይከፍለዋል (1-4)

        • ኢየሩሳሌም ከሌሎች ብሔራት የከፋ ድርጊት ፈጽማለች (7-9)

        • በሦስት መንገድ ቅጣት ይደርስባታል (12)

ሕዝቅኤል 5:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 9:21፤ ሕዝ 4:8
  • +ኤር 15:2
  • +ዘሌ 26:33፤ ሕዝ 5:12

ሕዝቅኤል 5:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በቀሚስህ።”

ሕዝቅኤል 5:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 4:4

ሕዝቅኤል 5:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 16:46, 47

ሕዝቅኤል 5:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 21:9, 11፤ ኤር 2:11

ሕዝቅኤል 5:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 21:5፤ ሕዝ 15:7
  • +ዘዳ 29:22, 24፤ 1ነገ 9:8፤ ሰቆ 2:15

ሕዝቅኤል 5:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሰቆ 4:6፤ ዳን 9:12

ሕዝቅኤል 5:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ወደ ነፋስ ሁሉ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 26:29፤ ኤር 19:9፤ ሰቆ 4:10
  • +ዘሌ 26:33፤ ዘዳ 28:64

ሕዝቅኤል 5:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አሳንስሻለሁ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 20:3፤ 2ነገ 21:1, 7፤ 2ዜና 36:14፤ ኤር 32:34
  • +ሰቆ 2:21፤ ሕዝ 7:4

ሕዝቅኤል 5:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በበሽታ።”

  • *

    ቃል በቃል “ወደ ነፋስ ሁሉ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 14:12፤ 15:2፤ 21:9
  • +ዘሌ 26:33፤ ኤር 9:16፤ 42:16

ሕዝቅኤል 5:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 16:42
  • +ዘፀ 20:3, 5፤ 34:14፤ ዘዳ 6:15

ሕዝቅኤል 5:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:37፤ 1ነገ 9:7፤ ነህ 2:17

ሕዝቅኤል 5:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 79:4፤ ኤር 24:9፤ ሰቆ 2:15፤ 3:61, 62

ሕዝቅኤል 5:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የዳቦ በትሮቻችሁን በመስበር።” ዳቦ ለማስቀመጥ የሚያገለግሉ በትሮችን የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 32:23
  • +ዘሌ 26:26፤ ሕዝ 4:16

ሕዝቅኤል 5:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 26:22፤ ዘዳ 32:24፤ ሕዝ 14:21፤ 33:27
  • +ሕዝ 21:3

ተዛማጅ ሐሳብ

ሕዝ. 5:2ኤር 9:21፤ ሕዝ 4:8
ሕዝ. 5:2ኤር 15:2
ሕዝ. 5:2ዘሌ 26:33፤ ሕዝ 5:12
ሕዝ. 5:4ኤር 4:4
ሕዝ. 5:6ሕዝ 16:46, 47
ሕዝ. 5:72ነገ 21:9, 11፤ ኤር 2:11
ሕዝ. 5:8ኤር 21:5፤ ሕዝ 15:7
ሕዝ. 5:8ዘዳ 29:22, 24፤ 1ነገ 9:8፤ ሰቆ 2:15
ሕዝ. 5:9ሰቆ 4:6፤ ዳን 9:12
ሕዝ. 5:10ዘሌ 26:29፤ ኤር 19:9፤ ሰቆ 4:10
ሕዝ. 5:10ዘሌ 26:33፤ ዘዳ 28:64
ሕዝ. 5:11ዘሌ 20:3፤ 2ነገ 21:1, 7፤ 2ዜና 36:14፤ ኤር 32:34
ሕዝ. 5:11ሰቆ 2:21፤ ሕዝ 7:4
ሕዝ. 5:12ኤር 14:12፤ 15:2፤ 21:9
ሕዝ. 5:12ዘሌ 26:33፤ ኤር 9:16፤ 42:16
ሕዝ. 5:13ሕዝ 16:42
ሕዝ. 5:13ዘፀ 20:3, 5፤ 34:14፤ ዘዳ 6:15
ሕዝ. 5:14ዘዳ 28:37፤ 1ነገ 9:7፤ ነህ 2:17
ሕዝ. 5:15መዝ 79:4፤ ኤር 24:9፤ ሰቆ 2:15፤ 3:61, 62
ሕዝ. 5:16ዘዳ 32:23
ሕዝ. 5:16ዘሌ 26:26፤ ሕዝ 4:16
ሕዝ. 5:17ዘሌ 26:22፤ ዘዳ 32:24፤ ሕዝ 14:21፤ 33:27
ሕዝ. 5:17ሕዝ 21:3
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ሕዝቅኤል 5:1-17

ሕዝቅኤል

5 “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ እንደ ፀጉር አስተካካይ ምላጭ የምትጠቀምበት ስለታም ሰይፍ ውሰድ። የራስህን ፀጉርና ጢምህን ተላጭ፤ ከዚያም ሚዛን ወስደህ ፀጉሩን መዝነውና ከፋፍለው። 2 የከበባው ጊዜ ሲፈጸም+ አንድ ሦስተኛውን በከተማዋ ውስጥ በእሳት ታቃጥለዋለህ። ከዚያም ሌላ አንድ ሦስተኛ ወስደህ በከተማዋ ዙሪያ በሰይፍ ትመታዋለህ፤+ የመጨረሻውንም አንድ ሦስተኛ ለነፋስ ትበትነዋለህ፤ እኔም እነሱን ለማሳደድ ሰይፍ እመዛለሁ።+

3 “ደግሞም ከፀጉሮቹ ላይ ጥቂት ወስደህ በልብስህ እጥፋት* ቋጥራቸው። 4 የተወሰነውን ደግሞ ወስደህ እሳት ውስጥ ጨምረው፤ ሙሉ በሙሉም በእሳት አቃጥለው። ይህ እሳት ወጥቶ በእስራኤል ቤት ሁሉ ይሰራጫል።+

5 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ይህች ኢየሩሳሌም ናት። አገሮችን በዙሪያዋ አድርጌ፣ በብሔራት መካከል አስቀምጫታለሁ። 6 እሷ ግን ከብሔራትና በዙሪያዋ ካሉ አገሮች ሁሉ የባሰ ክፋት በመሥራት በድንጋጌዎቼና ባወጣኋቸው ደንቦች ላይ ዓምፃለች።+ ሕዝቡ ድንጋጌዎቼን ወደ ጎን ገሸሽ አድርጓልና፤ ደንቦቼንም አክብሮ አልተመላለሰም።’

7 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዙሪያችሁ ካሉት ብሔራት ይበልጥ አስቸጋሪ በመሆናችሁ፣ ደንቦቼን አክብራችሁ ባለመመላለሳችሁ ወይም ድንጋጌዎቼን ባለመጠበቃችሁ፣ ይልቁንም በዙሪያችሁ ያሉትን ብሔራት ድንጋጌዎች በመከተላችሁ፣+ 8 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አንቺ ከተማ ሆይ፣ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ፤+ ደግሞም እኔ ራሴ በብሔራት ፊት በመካከልሽ ፍርዴን አስፈጽማለሁ።+ 9 በአስጸያፊ ድርጊቶችሽ ሁሉ የተነሳ ከዚህ በፊት ፈጽሞ ያላደረግኩትን፣ ከዚህም በኋላ የማልደግመውን በአንቺ ላይ አደርጋለሁ።+

10 “‘“ስለዚህ በመካከልሽ አባቶች ልጆቻቸውን ይበላሉ፤+ ልጆችም አባቶቻቸውን ይበላሉ፤ በመካከልሽ ፍርዴን አስፈጽማለሁ፤ ከአንቺ የቀሩትንም በሙሉ በየአቅጣጫው* እበትናቸዋለሁ።”’+

11 “‘ስለዚህ በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘በአስጸያፊ ጣዖቶችሽ ሁሉና ጸያፍ በሆኑ ድርጊቶችሽ ሁሉ መቅደሴን ስላረከስሽ፣+ እኔ ራሴ እተውሻለሁ፤* ዓይኔ አያዝንም ደግሞም አልራራም።+ 12 ከአንቺም አንድ ሦስተኛው በቸነፈር* ይሞታል ወይም በመካከልሽ በረሃብ ያልቃል። ሌላ አንድ ሦስተኛ ደግሞ በዙሪያሽ በሰይፍ ይወድቃል።+ የመጨረሻውን አንድ ሦስተኛ ደግሞ በየአቅጣጫው* እበትነዋለሁ፤ እነሱንም ለማሳደድ ሰይፍ እመዛለሁ።+ 13 ከዚያም ቁጣዬ ይፈጸማል፤ በእነሱም ላይ የነደደው ቁጣዬ ይበርዳል፤ እኔም እረካለሁ።+ በእነሱም ላይ ቁጣዬን ፈጽሜ ባወረድኩ ጊዜ፣ እኔ ብቻ መመለክ የምፈልገው፣+ እኔ ይሖዋ ይህን እንደተናገርኩ ያውቃሉ።

14 “‘በዙሪያሽ ባሉ ብሔራት መካከል እንዲሁም በአጠገብሽ በሚያልፉ ሁሉ ፊት ባድማና መሳለቂያ አደርግሻለሁ።+ 15 በቁጣ፣ በንዴትና በኃይለኛ ቅጣት የፍርድ እርምጃ ስወስድብሽ በዙሪያሽ ባሉ ብሔራት ዘንድ መሳለቂያና መዘባበቻ+ ደግሞም የማስጠንቀቂያ ምሳሌና ማስፈራሪያ ትሆኛለሽ። እኔ ይሖዋ ይህን ተናግሬአለሁ።

16 “‘እነሱን ለማጥፋት ገዳይ የሆኑ የረሃብ ፍላጻዎችን እሰድባቸዋለሁ። የምሰዳቸው የረሃብ ፍላጻዎች ያጠፏችኋል።+ የምግብ አቅርቦታችሁ እንዲቋረጥ በማድረግ* ረሃቡን አባብሳለሁ።+ 17 በእናንተ ላይ ረሃብንና አደገኛ የዱር አራዊትን እሰዳለሁ፤+ እነሱም የወላድ መሃን ያደርጓችኋል። ቸነፈርና ደም መፋሰስ ያጥለቀልቋችኋል፤ ሰይፍም አመጣባችኋለሁ።+ እኔ ይሖዋ ይህን ተናግሬአለሁ።’”

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ