የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሕዝቅኤል 10
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ሕዝቅኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • ከመንኮራኩሮቹ መካከል እሳት ተወሰደ (1-8)

      • የኪሩቦችና የመንኮራኩሮች መግለጫ (9-17)

      • የአምላክ ክብር ከቤተ መቅደሱ ተነስቶ ሄደ (18-22)

ሕዝቅኤል 10:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 6:1፤ ሕዝ 1:22, 26፤ ራእይ 4:2, 3

ሕዝቅኤል 10:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የሠረገላ ተሽከርካሪ እግር።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 9:2
  • +ሕዝ 1:16
  • +ሕዝ 1:13
  • +2ነገ 25:8, 9

ሕዝቅኤል 10:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 1:27, 28፤ 9:3
  • +ዘፀ 40:35፤ 2ዜና 5:13፤ ሕዝ 43:5

ሕዝቅኤል 10:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 29:3, 4፤ ሕዝ 1:24፤ ዮሐ 12:28, 29

ሕዝቅኤል 10:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 1:13
  • +ሕዝ 9:2

ሕዝቅኤል 10:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 1:8

ሕዝቅኤል 10:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 1:15-18

ሕዝቅኤል 10:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ራስ ወዳለበት።”

ሕዝቅኤል 10:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ራእይ 4:6, 8

ሕዝቅኤል 10:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    እያንዳንዱን ኪሩብ ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 1:6, 10፤ ራእይ 4:7

ሕዝቅኤል 10:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ያየሁት ሕያው ፍጡር ይኸው ነበር።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 1:3

ሕዝቅኤል 10:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 1:19-21

ሕዝቅኤል 10:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የሕያው ፍጡሩ መንፈስ።”

ሕዝቅኤል 10:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 1:27, 28
  • +ሕዝ 9:3፤ 10:4

ሕዝቅኤል 10:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 11:22

ሕዝቅኤል 10:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 1:1, 22

ሕዝቅኤል 10:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 1:8

ሕዝቅኤል 10:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 1:10
  • +ሕዝ 1:12፤ 10:11

ተዛማጅ ሐሳብ

ሕዝ. 10:1ኢሳ 6:1፤ ሕዝ 1:22, 26፤ ራእይ 4:2, 3
ሕዝ. 10:2ሕዝ 9:2
ሕዝ. 10:2ሕዝ 1:16
ሕዝ. 10:2ሕዝ 1:13
ሕዝ. 10:22ነገ 25:8, 9
ሕዝ. 10:4ሕዝ 1:27, 28፤ 9:3
ሕዝ. 10:4ዘፀ 40:35፤ 2ዜና 5:13፤ ሕዝ 43:5
ሕዝ. 10:5መዝ 29:3, 4፤ ሕዝ 1:24፤ ዮሐ 12:28, 29
ሕዝ. 10:7ሕዝ 1:13
ሕዝ. 10:7ሕዝ 9:2
ሕዝ. 10:8ሕዝ 1:8
ሕዝ. 10:9ሕዝ 1:15-18
ሕዝ. 10:12ራእይ 4:6, 8
ሕዝ. 10:14ሕዝ 1:6, 10፤ ራእይ 4:7
ሕዝ. 10:15ሕዝ 1:3
ሕዝ. 10:16ሕዝ 1:19-21
ሕዝ. 10:18ሕዝ 1:27, 28
ሕዝ. 10:18ሕዝ 9:3፤ 10:4
ሕዝ. 10:19ሕዝ 11:22
ሕዝ. 10:20ሕዝ 1:1, 22
ሕዝ. 10:21ሕዝ 1:8
ሕዝ. 10:22ሕዝ 1:10
ሕዝ. 10:22ሕዝ 1:12፤ 10:11
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ሕዝቅኤል 10:1-22

ሕዝቅኤል

10 እኔም እያየሁ ሳለ ከኪሩቦቹ ራስ በላይ ካለው ጠፈር በላይ እንደ ሰንፔር ድንጋይ ያለ ነገር ተገለጠ፤ መልኩም ዙፋን ይመስል ነበር።+ 2 ከዚያም አምላክ በፍታ የለበሰውን ሰው+ “በኪሩቦቹ ሥር ወደሚገኙት የሚሽከረከሩ መንኮራኩሮች*+ መሃል ግባና በኪሩቦቹ መካከል ካለው ፍም+ በእጆችህ ዘግነህ በከተማዋ ላይ በትነው”+ አለው። እሱም እኔ እያየሁት ገባ።

3 ሰውየው ወደዚያ ሲገባ ኪሩቦቹ ከቤተ መቅደሱ በስተ ቀኝ ቆመው ነበር፤ ደመናውም የውስጠኛውን ግቢ ሞላው። 4 የይሖዋም ክብር+ ከኪሩቦቹ ላይ ተነስቶ ወደ ቤተ መቅደሱ በር ደጃፍ ሄደ፤ ቤተ መቅደሱም ቀስ በቀስ በደመናው ተሞላ፤+ ግቢውም በይሖዋ ክብር ብርሃን ተሞላ። 5 የኪሩቦቹም ክንፎች ድምፅ ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ሲናገር እንደሚሰማው ድምፅ እስከ ውጨኛው ግቢ ድረስ ይሰማ ነበር።+

6 ከዚያም አምላክ፣ በፍታ የለበሰውን ሰው “ከሚሽከረከሩት መንኮራኩሮች መካከልና ከኪሩቦቹ መሃል እሳት ውሰድ” ብሎ አዘዘው፤ ሰውየውም ገብቶ ከመንኮራኩሩ አጠገብ ቆመ። 7 ከዚያም አንዱ ኪሩብ፣ በኪሩቦቹ መካከል ወዳለው እሳት+ እጁን ዘረጋ። የተወሰነ እሳት ወስዶ በፍታ በለበሰው ሰው+ እጆች ላይ አደረገ፤ እሱም እሳቱን ይዞ ወጣ። 8 ኪሩቦቹ ከክንፎቻቸው ሥር የሰው እጅ የሚመስል ነገር ነበራቸው።+

9 እኔም እያየሁ ሳለ በኪሩቦቹ አጠገብ አራት መንኮራኩሮች ተመለከትኩ፤ በእያንዳንዱ ኪሩብ አጠገብ አንድ መንኮራኩር ነበር፤ መንኮራኩሮቹም እንደ ክርስቲሎቤ ድንጋይ የሚያብረቀርቅ መልክ ነበራቸው።+ 10 የአራቱም መልክ ይመሳሰል ነበር፤ በአንድ መንኮራኩር ውስጥ በጎን በኩል ሌላ መንኮራኩር የተሰካ ይመስል ነበር። 11 በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ መዞር ሳያስፈልጋቸው በአራቱም አቅጣጫ መሄድ ይችሉ ነበር፤ ምክንያቱም መዞር ሳያስፈልጋቸው ፊታቸው ወደሚያይበት* አቅጣጫ ሁሉ ይሄዱ ነበር። 12 ሰውነታቸው ሁሉ፣ ጀርባቸው፣ እጃቸው፣ ክንፋቸው እንዲሁም መንኮራኩሮቹ ይኸውም የአራቱም መንኮራኩሮች ሁለመና በዓይን የተሞላ ነበር።+ 13 አንድ ድምፅ መንኮራኩሮቹን “ተሽከርካሪ መንኮራኩሮች!” ብሎ ሲጠራቸው ሰማሁ።

14 እያንዳንዳቸው* አራት አራት ፊት ነበራቸው። የመጀመሪያው ፊት የኪሩብ ፊት፣ ሁለተኛው ፊት የሰው ፊት፣ ሦስተኛውም የአንበሳ ፊት፣ አራተኛው ደግሞ የንስር ፊት ነበር።+

15 ኪሩቦቹም ወደ ላይ ተነሱ፤ በኬባር ወንዝ+ ያየኋቸው ሕያዋን ፍጥረታት እነዚሁ ነበሩ፤* 16 ኪሩቦቹ ሲንቀሳቀሱ፣ መንኮራኩሮቹም አጠገባቸው ሆነው ይንቀሳቀሱ ነበር፤ ኪሩቦቹ ከምድር በላይ ከፍ ከፍ ለማለት ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ሲዘረጉ መንኮራኩሮቹ ከአጠገባቸው አይለዩም ወይም አይርቁም ነበር።+ 17 እነሱ ሲቆሙ፣ መንኮራኩሮቹም ይቆማሉ፤ እነሱ ከፍ ከፍ ሲሉ መንኮራኩሮቹም አብረዋቸው ከፍ ከፍ ይሉ ነበር፤ በሕያዋን ፍጥረታቱ ላይ የሚሠራው መንፈስ* በውስጣቸው ነበርና።

18 ከዚያም የይሖዋ ክብር+ ከቤተ መቅደሱ በር ደጃፍ ተነስቶ በመሄድ ከኪሩቦቹ በላይ ቆመ።+ 19 ኪሩቦቹ እኔ እያየኋቸው ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ዘርግተው ከምድር ተነሱ። እነሱ ሲሄዱ መንኮራኩሮቹም አብረዋቸው ነበሩ። በይሖዋ ቤት በስተ ምሥራቅ በሚገኘው በር መግቢያም ላይ ቆሙ፤ የእስራኤል አምላክ ክብርም በላያቸው ነበር።+

20 እነዚህ በኬባር ወንዝ አቅራቢያ ከእስራኤል አምላክ በታች ያየኋቸው ሕያዋን ፍጥረታት ናቸው፤+ በመሆኑም ኪሩቦች መሆናቸውን አወቅኩ። 21 አራቱም፣ አራት አራት ፊትና አራት አራት ክንፍ ነበራቸው፤ ከክንፎቻቸውም ሥር የሰው እጆች የሚመስሉ ነገሮች ነበሯቸው።+ 22 የፊታቸውም መልክ በኬባር ወንዝ አቅራቢያ እንዳየኋቸው ፊቶች ነበር።+ እያንዳንዳቸው ቀጥ ብለው ወደ ፊት ይሄዱ ነበር።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ