የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሕዝቅኤል 17
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ሕዝቅኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • የሁለቱ ንስሮችና የወይን ተክሉ እንቆቅልሽ (1-21)

      • ለጋ የሆነው ቀንበጥ የሚያምር አርዘ ሊባኖስ ሆነ (22-24)

ሕዝቅኤል 17:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሆሴዕ 12:10

ሕዝቅኤል 17:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:49, 50፤ ኤር 4:13፤ ሰቆ 4:19
  • +ኤር 22:23
  • +2ነገ 24:12፤ 2ዜና 36:9, 10፤ ኤር 24:1

ሕዝቅኤል 17:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ከነአን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 24:15

ሕዝቅኤል 17:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የአኻያ ዛፍ የሚመስል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 24:17፤ ኤር 37:1

ሕዝቅኤል 17:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 17:13, 14
  • +2ዜና 36:11

ሕዝቅኤል 17:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 37:5, 7፤ ሕዝ 17:15
  • +2ነገ 24:20፤ 2ዜና 36:11, 13

ሕዝቅኤል 17:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 37:1

ሕዝቅኤል 17:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 21:7
  • +2ነገ 25:7

ሕዝቅኤል 17:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 24:12, 14፤ ኢሳ 39:7፤ ኤር 22:24, 25፤ 52:31, 32

ሕዝቅኤል 17:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 24:17፤ ኤር 37:1
  • +2ዜና 36:11, 13
  • +2ነገ 24:15፤ ኤር 24:1

ሕዝቅኤል 17:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 27:12፤ 38:17

ሕዝቅኤል 17:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 17:16
  • +ኤር 37:5
  • +2ነገ 24:20፤ 2ዜና 36:11, 13
  • +ኤር 32:3, 4

ሕዝቅኤል 17:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ሴዴቅያስን ያመለክታል።

  • *

    ናቡከደነጾርን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 34:2, 3፤ 52:11

ሕዝቅኤል 17:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 37:7, 8፤ ሰቆ 4:17፤ ሕዝ 29:6

ሕዝቅኤል 17:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እጁን ቢሰጠውም።”

ሕዝቅኤል 17:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 5:11

ሕዝቅኤል 17:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 12:13
  • +ሕዝ 20:36

ሕዝቅኤል 17:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ወደ ነፋስ ሁሉ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 12:14
  • +ሕዝ 6:13

ሕዝቅኤል 17:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 11:1፤ ኤር 23:5
  • +ኢሳ 53:2
  • +መዝ 2:6

ሕዝቅኤል 17:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 9:6፤ ሕዝ 21:26, 27፤ ዳን 4:17፤ አሞጽ 9:11
  • +1ሳሙ 2:7, 8፤ ሉቃስ 1:52

ተዛማጅ ሐሳብ

ሕዝ. 17:2ሆሴዕ 12:10
ሕዝ. 17:3ዘዳ 28:49, 50፤ ኤር 4:13፤ ሰቆ 4:19
ሕዝ. 17:3ኤር 22:23
ሕዝ. 17:32ነገ 24:12፤ 2ዜና 36:9, 10፤ ኤር 24:1
ሕዝ. 17:42ነገ 24:15
ሕዝ. 17:52ነገ 24:17፤ ኤር 37:1
ሕዝ. 17:6ሕዝ 17:13, 14
ሕዝ. 17:62ዜና 36:11
ሕዝ. 17:7ኤር 37:5, 7፤ ሕዝ 17:15
ሕዝ. 17:72ነገ 24:20፤ 2ዜና 36:11, 13
ሕዝ. 17:8ኤር 37:1
ሕዝ. 17:9ኤር 21:7
ሕዝ. 17:92ነገ 25:7
ሕዝ. 17:122ነገ 24:12, 14፤ ኢሳ 39:7፤ ኤር 22:24, 25፤ 52:31, 32
ሕዝ. 17:132ነገ 24:17፤ ኤር 37:1
ሕዝ. 17:132ዜና 36:11, 13
ሕዝ. 17:132ነገ 24:15፤ ኤር 24:1
ሕዝ. 17:14ኤር 27:12፤ 38:17
ሕዝ. 17:15ዘዳ 17:16
ሕዝ. 17:15ኤር 37:5
ሕዝ. 17:152ነገ 24:20፤ 2ዜና 36:11, 13
ሕዝ. 17:15ኤር 32:3, 4
ሕዝ. 17:16ኤር 34:2, 3፤ 52:11
ሕዝ. 17:17ኤር 37:7, 8፤ ሰቆ 4:17፤ ሕዝ 29:6
ሕዝ. 17:19ዘዳ 5:11
ሕዝ. 17:20ሕዝ 12:13
ሕዝ. 17:20ሕዝ 20:36
ሕዝ. 17:21ሕዝ 12:14
ሕዝ. 17:21ሕዝ 6:13
ሕዝ. 17:22ኢሳ 11:1፤ ኤር 23:5
ሕዝ. 17:22ኢሳ 53:2
ሕዝ. 17:22መዝ 2:6
ሕዝ. 17:24ኢሳ 9:6፤ ሕዝ 21:26, 27፤ ዳን 4:17፤ አሞጽ 9:11
ሕዝ. 17:241ሳሙ 2:7, 8፤ ሉቃስ 1:52
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ሕዝቅኤል 17:1-24

ሕዝቅኤል

17 የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ስለ እስራኤል ቤት እንቆቅልሽና ምሳሌ ተናገር።+ 3 እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ትላልቅ ክንፎችና ረጃጅም ማርገብገቢያዎች ያሉት እንዲሁም መላ አካሉ ዥጉርጉር በሆኑ ላባዎች የተሸፈነው ታላቁ ንስር+ ወደ ሊባኖስ+ መጥቶ የአርዘ ሊባኖስን ጫፍ ያዘ።+ 4 አናቱ ላይ ያለውን ቀንበጥ ቀጥፎ ወደ ነጋዴዎች* ምድር አመጣው፤ በነጋዴዎችም ከተማ ተከለው።+ 5 ከዚያም ከምድሪቱ ዘር የተወሰነውን ወስዶ+ ለም በሆነ መሬት ላይ ዘራው። እንደ ሪጋ* ዛፍ ብዙ ውኃ ባለበት ቦታ አጠገብ ተከለው። 6 በመሆኑም ዘሩ በቀለ፤ አጭርና የተንሰራፋ እንዲሁም ወደ ራሱ አቅጣጫ የበቀሉ ቅጠሎች ያሉት የወይን ተክል ሆነ፤+ ሥሮቹም ከበታቹ አደጉ። በዚህ ሁኔታ የወይን ተክል ሆነ፤ ቀንበጦችና ቅርንጫፎችም አወጣ።+

7 “‘“ደግሞም ትላልቅ ክንፎች ያሉትና የክንፎቹ ላባዎች ረጃጅም የሆኑ ሌላ ታላቅ ንስር መጣ።+ ከዚያም ይህ የወይን ተክል ሥሮቹን ከተተከለበት የአትክልት መደብ አሻግሮ በታላቅ ጉጉት ወደ እሱ ዘረጋ፤ ውኃ ያጠጣውም ዘንድ ቅርንጫፎቹን ወደ እሱ ሰደደ።+ 8 ቅርንጫፎችን እንዲያወጣና ፍሬ እንዲያፈራ እንዲሁም ያማረ የወይን ተክል እንዲሆን ብዙ ውኃ ባለበት አቅራቢያ መልካም መሬት ላይ ተተክሎ ነበር።”’+

9 “እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ያድግ ይሆን? ሰው ሥሮቹን ነቅሎ አይጥልም?+ ፍሬው እንዲበሰብስ አያደርግም? ቀንበጦቹስ እንዲጠወልጉ አያደርግም?+ የወይኑ ተክል በጣም ስለሚደርቅ ከሥሩ ለመንቀል ብርቱ ክንድም ሆነ ብዙ ሰው አያስፈልግም። 10 ተነቅሎ በሌላ ቦታ ቢተከልስ ያድግ ይሆን? የምሥራቅ ነፋስ ሲነፍስበት ሙሉ በሙሉ አይደርቅም? በበቀለበት የአትክልት መደብ ላይ ይደርቃል።”’”

11 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 12 “እባክህ፣ ለዓመፀኛው ቤት ይህን ተናገር፦ ‘የእነዚህ ነገሮች ትርጉም ምን እንደሆነ አትገነዘቡም?’ እንዲህ በል፦ ‘እነሆ፣ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ንጉሥዋንና መኳንንቷን ማረከ፤ ወደ ባቢሎንም ይዟቸው ተመለሰ።+ 13 በተጨማሪም ከንጉሣውያን ዘር አንዱን ወስዶ+ ከእሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፤ በመሐላም ቃል አስገባው።+ ከዚያም የምድሪቱን ታላላቅ ሰዎች ወሰደ፤+ 14 ይህም መንግሥቲቱ ዝቅ እንድትልና ማንሰራራት እንዳትችል እንዲሁም የእሱን ቃል ኪዳን በመጠበቅ ብቻ እንድትኖር ለማድረግ ነው።+ 15 ንጉሡ ግን በመጨረሻ ፈረሶችና+ ብዙ ሠራዊት እንዲልኩለት መልእክተኞቹን ወደ ግብፅ በመስደድ+ በእሱ ላይ ዓመፀ።+ ታዲያ ይሳካለት ይሆን? እነዚህን ነገሮች ያደረገው ከቅጣት ያመልጣል? ቃል ኪዳኑንስ አፍርሶ ማምለጥ ይችላል?’+

16 “‘“በሕያውነቴ እምላለሁ” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ “እሱን ንጉሥ* አድርጎ የሾመው ንጉሥ* በሚኖርበት ቦታ ይኸውም በባቢሎን ይሞታል፤ ይህ ሰው መሐላውን አቃሎበታል፤ ቃል ኪዳኑንም አፍርሶበታል።+ 17 ብዙ ሕይወት* ለማጥፋት የአፈር ቁልል በሚደለደልበትና ለከበባ የሚያገለግል ግንብ በሚሠራበት ጊዜ የፈርዖን ታላቅ ሠራዊትና ስፍር ቁጥር የሌላቸው ወታደሮች ሊረዱት አይችሉም።+ 18 እሱ መሐላውን አቃሏል፤ ቃል ኪዳኑንም አፍርሷል። ቃል ቢገባለትም* እንኳ እነዚህን ነገሮች ሁሉ አድርጓል፤ ስለዚህ ፈጽሞ አያመልጥም።”’

19 “‘በመሆኑም ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በሕያውነቴ እምላለሁ፤ መሐላዬን መናቁና ቃል ኪዳኔን ማፍረሱ የሚያስከትልበትን መዘዝ በራሱ ላይ አመጣበታለሁ።+ 20 መረቤን በላዩ ላይ እዘረጋለሁ፤ እሱም በማጥመጃ መረቤ ይያዛል።+ ወደ ባቢሎን አመጣዋለሁ፤ በእኔ ላይ ክህደት ስለፈጸመ በዚያ እፋረደዋለሁ።+ 21 ከወታደሮቹ መካከል የሸሹት ሁሉ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ በሕይወት የተረፉትም በየአቅጣጫው* ይበታተናሉ።+ በዚህ ጊዜም እኔ ይሖዋ ራሴ እንደተናገርኩ ታውቃላችሁ።”’+

22 “‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ከረጅሙ አርዘ ሊባኖስ ጫፍ ላይ ቀንበጥ+ ቀጥፌ እተክለዋለሁ፤ ከቀንበጦቹም ጫፍ ላይ ለጋ የሆነውን ቀጥፌ+ ረጅምና ግዙፍ በሆነ ተራራ ላይ እኔ ራሴ እተክለዋለሁ።+ 23 ረጅም በሆነ የእስራኤል ተራራ ላይ እተክለዋለሁ፤ ቅርንጫፎቹም ያድጋሉ፤ ፍሬም ያፈራል፤ ደግሞም የሚያምር አርዘ ሊባኖስ ይሆናል። በሥሩም የወፍ ዓይነቶች ሁሉ ይኖራሉ፤ በቅጠሎቹም ጥላ ሥር ያርፋሉ። 24 የዱር ዛፎች ሁሉ፣ ከፍ ያለውን ዛፍ ዝቅ ዝቅ ያደረግኩት፣ ዝቅ ያለውን ዛፍ ደግሞ ከፍ ከፍ ያደረግኩት እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ፤+ ለምለሙን ዛፍ አድርቄአለሁ፤ ደረቁም ዛፍ እንዲለመልም አድርጌአለሁ።+ እኔ ይሖዋ ራሴ ይህን ተናግሬአለሁ፤ ደግሞም አድርጌአለሁ።”’”

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ