የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሕዝቅኤል 19
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ሕዝቅኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • ስለ እስራኤል አለቆች የተነገረ ሙሾ (1-14)

ሕዝቅኤል 19:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሐዘን እንጉርጉሮ አሰማ።”

ሕዝቅኤል 19:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 36:1

ሕዝቅኤል 19:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 23:31-34፤ 2ዜና 36:4፤ ኤር 22:11, 12

ሕዝቅኤል 19:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 22:17

ሕዝቅኤል 19:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 28:15

ሕዝቅኤል 19:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “በወይን እርሻህ ውስጥ እንዳለ የወይን ተክል” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 80:8፤ ኢሳ 5:7

ሕዝቅኤል 19:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ዘንጎች።”

ሕዝቅኤል 19:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 5:5፤ ሕዝ 15:6
  • +2ነገ 23:34፤ 24:6፤ 25:5-7
  • +ዘዳ 32:22፤ ሕዝ 15:4

ሕዝቅኤል 19:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:48፤ ኤር 17:5, 6፤ 52:27

ሕዝቅኤል 19:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “እሳት ከዘንጎቿ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 17:16, 18

ተዛማጅ ሐሳብ

ሕዝ. 19:32ዜና 36:1
ሕዝ. 19:42ነገ 23:31-34፤ 2ዜና 36:4፤ ኤር 22:11, 12
ሕዝ. 19:6ኤር 22:17
ሕዝ. 19:7ምሳሌ 28:15
ሕዝ. 19:10መዝ 80:8፤ ኢሳ 5:7
ሕዝ. 19:12ኢሳ 5:5፤ ሕዝ 15:6
ሕዝ. 19:122ነገ 23:34፤ 24:6፤ 25:5-7
ሕዝ. 19:12ዘዳ 32:22፤ ሕዝ 15:4
ሕዝ. 19:13ዘዳ 28:48፤ ኤር 17:5, 6፤ 52:27
ሕዝ. 19:14ሕዝ 17:16, 18
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ሕዝቅኤል 19:1-14

ሕዝቅኤል

19 “ስለ እስራኤል አለቆች ሙሾ አውጣ፤* 2 እንዲህም በል፦

‘እናትህ ምን ነበረች? በአንበሶች መካከል ያለች እንስት አንበሳ ነበረች።

በብርቱ ደቦል አንበሶች መሃል ተኛች፤ ግልገሎቿንም በዚያ አሳደገች።

 3 ከግልገሎቿ መካከል አንዱን ተንከባክባ አሳደገችው፤ እሱም ብርቱ ደቦል አንበሳ ሆነ።+

አድኖ መብላት ተማረ፤

ሰዎችንም እንኳ ሳይቀር በላ።

 4 ብሔራት ስለ እሱ ሰሙ፤ ጉድጓዳቸው ውስጥ ገብቶም ያዙት፤

በስናግም እየጎተቱ ወደ ግብፅ ምድር አመጡት።+

 5 እሷም በትዕግሥት ስትጠባበቅ ከቆየች በኋላ የመመለስ ተስፋ እንደሌለው ተገነዘበች።

በመሆኑም ከግልገሎቿ መካከል ሌላውን ወስዳ እንደ ብርቱ ደቦል አንበሳ አድርጋ ላከችው።

 6 እሱም በአንበሶች መካከል ይጎማለል ጀመር፤ ብርቱ ደቦል አንበሳም ሆነ።

አድኖ መብላት ተማረ፤ ሰዎችንም እንኳ ሳይቀር በላ።+

 7 በማይደፈሩት ማማዎቻቸው መካከል አደባ፤ ከተሞቻቸውንም አወደመ፤

ከዚህም የተነሳ ግሳቱ ወና በሆነችው ምድር ላይ አስተጋባ።+

 8 በዙሪያው ባሉ ግዛቶች ያሉ ብሔራት መረባቸውን በእሱ ላይ ለመዘርጋት ተነሱበት፤

እሱም ጉድጓዳቸው ውስጥ ገብቶ ተያዘ።

 9 በስናግ ጎትተው በእንስሳት ጎጆ ውስጥ በመክተት ወደ ባቢሎን ንጉሥ አመጡት።

ከዚያ በኋላ ድምፁ በእስራኤል ተራሮች ላይ እንዳይሰማ በዚያ አሰሩት።

10 እናትህ በውኃዎች አጠገብ እንደተተከለ፣ በደምህ ውስጥ ያለ የወይን ተክል* ነበረች።+

ከውኃው ብዛት የተነሳ ፍሬ አፈራች፤ ብዙ ቅርንጫፎችም ነበሯት።

11 ለገዢዎች በትረ መንግሥት የሚሆኑ ጠንካራ ቅርንጫፎች* አወጣች።

አድጋ ከሌሎች ዛፎች ይበልጥ ረጅም ሆነች፤

ደግሞም ከርዝመቷና ከቅጠሎቿ ብዛት የተነሳ ጎልታ ታየች።

12 ሆኖም በቁጣ ተነቀለች፤+ ወደ ምድርም ተጣለች፤

የምሥራቅም ነፋስ ፍሬዋን አደረቀው።

ጠንካራ ቅርንጫፎቿ ተሰብረው ደረቁ፤+ እሳትም በላቸው።+

13 በዚህ ጊዜ በምድረ በዳ፣

ውኃ በሌለበት ደረቅ ምድር ተተከለች።+

14 እሳት ከቅርንጫፎቿ* ወጥቶ ቀንበጦቿንና ፍሬዋን በላ፤

በእሷም ላይ አንድም ጠንካራ ቅርንጫፍ፣ ለገዢዎችም የሚሆን በትረ መንግሥት አልተረፈም።+

“‘ይህ ሙሾ ነው፤ ሙሾ ሆኖም ያገለግላል።’”

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ