የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሕዝቅኤል 20
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ሕዝቅኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • የእስራኤላውያን ዓመፅ (1-32)

      • እስራኤላውያን ተመልሰው እንደሚቋቋሙ የተገባላቸው የተስፋ ቃል (33-44)

      • በደቡብ ላይ የተነገረ ትንቢት (45-49)

ሕዝቅኤል 20:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 1:12, 15፤ ሕዝ 14:3

ሕዝቅኤል 20:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የፍርድ ውሳኔ ለማስተላለፍ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 16:51፤ 22:2፤ ሉቃስ 11:47

ሕዝቅኤል 20:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እጄን አነሳሁ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 7:6
  • +ዘፀ 4:31፤ 6:7, 8

ሕዝቅኤል 20:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ለእነሱ ወደሰለልኳት።”

  • *

    ወይም “የምድር ሁሉ ጌጥ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 3:8

ሕዝቅኤል 20:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል “ፋንድያ” ከሚለው ቃል ጋር ዝምድና ሊኖረው የሚችል ሲሆን ንቀትን ለማመልከት ተሠርቶበታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 18:3፤ ዘዳ 29:16, 17፤ ኢያሱ 24:14
  • +ዘሌ 20:7

ሕዝቅኤል 20:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 32:4

ሕዝቅኤል 20:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    እስራኤልን ያመለክታል።

  • *

    እስራኤልን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 14:13-16፤ ዘዳ 9:27, 28፤ 1ሳሙ 12:22
  • +ዘፀ 32:11, 12፤ ኢያሱ 2:9, 10፤ 9:3, 9፤ 1ሳሙ 4:7, 8

ሕዝቅኤል 20:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 13:17, 18፤ 15:22

ሕዝቅኤል 20:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 4:8
  • +ዘዳ 8:3፤ 30:16

ሕዝቅኤል 20:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 31:13፤ 35:2
  • +ዘፀ 20:8-10፤ ዘሌ 23:3, 24፤ 25:4, 11

ሕዝቅኤል 20:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 32:8፤ ዘኁ 14:22, 23
  • +ዘኁ 14:11, 12

ሕዝቅኤል 20:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    እስራኤልን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 7:9፤ ሕዝ 36:22

ሕዝቅኤል 20:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የምድር ሁሉ ጌጥ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 13:26, 27
  • +ዘኁ 14:30፤ መዝ 95:11፤ 106:26, 27

ሕዝቅኤል 20:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 32:1, 4፤ ዘኁ 25:1, 2፤ ሥራ 7:42

ሕዝቅኤል 20:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ዓይኔ . . . ራራላቸው።”

ሕዝቅኤል 20:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 14:33
  • +መዝ 78:8

ሕዝቅኤል 20:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 4:1

ሕዝቅኤል 20:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 17:22
  • +ዘፀ 31:13

ሕዝቅኤል 20:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 25:1፤ ዘዳ 9:23
  • +ኢሳ 63:10

ሕዝቅኤል 20:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    እስራኤልን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 78:38
  • +መዝ 25:11፤ 79:9፤ ኤር 14:7፤ ዳን 9:19

ሕዝቅኤል 20:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 26:33፤ መዝ 106:26, 27

ሕዝቅኤል 20:24

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ዓይናቸው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 26:15, 16
  • +ኤር 2:7

ሕዝቅኤል 20:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 81:12

ሕዝቅኤል 20:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 18:21፤ ኤር 7:31

ሕዝቅኤል 20:28

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሚያረጋጋውን፤ የሚያበርደውን።” ቃል በቃል “እረፍት የሚሰጠውን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 23:5
  • +ዘዳ 12:2

ሕዝቅኤል 20:29

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ከፍ ያለ የማምለኪያ ቦታ” ወይም የሐሰት ሃይማኖት የአምልኮ ቦታ የሚል ትርጉም ያለው የዕብራይስጥ ቃል ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 16:24, 25

ሕዝቅኤል 20:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 2:19፤ 2ዜና 21:13፤ ኤር 13:26, 27

ሕዝቅኤል 20:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 18:10, 12፤ መዝ 106:36-38፤ ኤር 7:31
  • +ኢሳ 1:15
  • +ዘካ 7:13

ሕዝቅኤል 20:32

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “እንደሚያገለግሉት።”

  • *

    ቃል በቃል “ወደ መንፈሳችሁ የመጣው ነገር።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 44:17

ሕዝቅኤል 20:33

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 21:5፤ ሕዝ 8:18

ሕዝቅኤል 20:34

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 27:13፤ ሕዝ 34:16

ሕዝቅኤል 20:35

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 2:9

ሕዝቅኤል 20:37

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እስራት ውስጥ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 27:32፤ ሕዝ 34:17

ሕዝቅኤል 20:38

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 34:20, 21
  • +ሕዝ 13:9

ሕዝቅኤል 20:39

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 10:14፤ መዝ 81:12
  • +ኢሳ 1:13፤ ሕዝ 23:39

ሕዝቅኤል 20:40

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 2:2, 3፤ 66:20
  • +ኢሳ 56:7፤ ዘካ 8:22
  • +ሚል 3:4

ሕዝቅኤል 20:41

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በሚያረጋጋው፤ በሚያበርደው።” ቃል በቃል “እረፍት በሚሰጠው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 11:11፤ ኤር 23:3
  • +ኢሳ 5:16፤ ሕዝ 38:23

ሕዝቅኤል 20:42

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 11:17
  • +ሕዝ 36:23

ሕዝቅኤል 20:43

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ፊታችሁን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 26:40፤ ሕዝ 6:9፤ 16:61
  • +ኤር 31:18

ሕዝቅኤል 20:44

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 79:9፤ ሕዝ 36:22, 23

ሕዝቅኤል 20:47

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የምድር ገጽ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 32:22፤ ኤር 21:14
  • +ኢሳ 66:24

ሕዝቅኤል 20:48

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሰውም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 7:20፤ ሰቆ 2:17

ሕዝቅኤል 20:49

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ምሳሌያዊ አባባል።”

ተዛማጅ ሐሳብ

ሕዝ. 20:3ኢሳ 1:12, 15፤ ሕዝ 14:3
ሕዝ. 20:4ሕዝ 16:51፤ 22:2፤ ሉቃስ 11:47
ሕዝ. 20:5ዘዳ 7:6
ሕዝ. 20:5ዘፀ 4:31፤ 6:7, 8
ሕዝ. 20:6ዘፀ 3:8
ሕዝ. 20:7ዘሌ 18:3፤ ዘዳ 29:16, 17፤ ኢያሱ 24:14
ሕዝ. 20:7ዘሌ 20:7
ሕዝ. 20:8ዘፀ 32:4
ሕዝ. 20:9ዘኁ 14:13-16፤ ዘዳ 9:27, 28፤ 1ሳሙ 12:22
ሕዝ. 20:9ዘፀ 32:11, 12፤ ኢያሱ 2:9, 10፤ 9:3, 9፤ 1ሳሙ 4:7, 8
ሕዝ. 20:10ዘፀ 13:17, 18፤ 15:22
ሕዝ. 20:11ዘዳ 4:8
ሕዝ. 20:11ዘዳ 8:3፤ 30:16
ሕዝ. 20:12ዘፀ 31:13፤ 35:2
ሕዝ. 20:12ዘፀ 20:8-10፤ ዘሌ 23:3, 24፤ 25:4, 11
ሕዝ. 20:13ዘፀ 32:8፤ ዘኁ 14:22, 23
ሕዝ. 20:13ዘኁ 14:11, 12
ሕዝ. 20:14ኢያሱ 7:9፤ ሕዝ 36:22
ሕዝ. 20:15ዘኁ 13:26, 27
ሕዝ. 20:15ዘኁ 14:30፤ መዝ 95:11፤ 106:26, 27
ሕዝ. 20:16ዘፀ 32:1, 4፤ ዘኁ 25:1, 2፤ ሥራ 7:42
ሕዝ. 20:18ዘኁ 14:33
ሕዝ. 20:18መዝ 78:8
ሕዝ. 20:19ዘዳ 4:1
ሕዝ. 20:20ኤር 17:22
ሕዝ. 20:20ዘፀ 31:13
ሕዝ. 20:21ዘኁ 25:1፤ ዘዳ 9:23
ሕዝ. 20:21ኢሳ 63:10
ሕዝ. 20:22መዝ 78:38
ሕዝ. 20:22መዝ 25:11፤ 79:9፤ ኤር 14:7፤ ዳን 9:19
ሕዝ. 20:23ዘሌ 26:33፤ መዝ 106:26, 27
ሕዝ. 20:24ዘሌ 26:15, 16
ሕዝ. 20:24ኤር 2:7
ሕዝ. 20:25መዝ 81:12
ሕዝ. 20:26ዘሌ 18:21፤ ኤር 7:31
ሕዝ. 20:28ኢያሱ 23:5
ሕዝ. 20:28ዘዳ 12:2
ሕዝ. 20:29ሕዝ 16:24, 25
ሕዝ. 20:30መሳ 2:19፤ 2ዜና 21:13፤ ኤር 13:26, 27
ሕዝ. 20:31ዘዳ 18:10, 12፤ መዝ 106:36-38፤ ኤር 7:31
ሕዝ. 20:31ኢሳ 1:15
ሕዝ. 20:31ዘካ 7:13
ሕዝ. 20:32ኤር 44:17
ሕዝ. 20:33ኤር 21:5፤ ሕዝ 8:18
ሕዝ. 20:34ኢሳ 27:13፤ ሕዝ 34:16
ሕዝ. 20:35ኤር 2:9
ሕዝ. 20:37ዘሌ 27:32፤ ሕዝ 34:17
ሕዝ. 20:38ሕዝ 34:20, 21
ሕዝ. 20:38ሕዝ 13:9
ሕዝ. 20:39መሳ 10:14፤ መዝ 81:12
ሕዝ. 20:39ኢሳ 1:13፤ ሕዝ 23:39
ሕዝ. 20:40ኢሳ 2:2, 3፤ 66:20
ሕዝ. 20:40ኢሳ 56:7፤ ዘካ 8:22
ሕዝ. 20:40ሚል 3:4
ሕዝ. 20:41ኢሳ 11:11፤ ኤር 23:3
ሕዝ. 20:41ኢሳ 5:16፤ ሕዝ 38:23
ሕዝ. 20:42ሕዝ 11:17
ሕዝ. 20:42ሕዝ 36:23
ሕዝ. 20:43ዘሌ 26:40፤ ሕዝ 6:9፤ 16:61
ሕዝ. 20:43ኤር 31:18
ሕዝ. 20:44መዝ 79:9፤ ሕዝ 36:22, 23
ሕዝ. 20:47ዘዳ 32:22፤ ኤር 21:14
ሕዝ. 20:47ኢሳ 66:24
ሕዝ. 20:482ዜና 7:20፤ ሰቆ 2:17
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
  • 36
  • 37
  • 38
  • 39
  • 40
  • 41
  • 42
  • 43
  • 44
  • 45
  • 46
  • 47
  • 48
  • 49
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ሕዝቅኤል 20:1-49

ሕዝቅኤል

20 በሰባተኛው ዓመት፣ በአምስተኛው ወር፣ ከወሩም በአሥረኛው ቀን ከእስራኤል ሽማግሌዎች መካከል አንዳንዶቹ ይሖዋን ለመጠየቅ መጥተው በፊቴ ተቀመጡ። 2 ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 3 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ለእስራኤል ሽማግሌዎች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የመጣችሁት እኔን ለመጠየቅ ነው? ‘በሕያውነቴ እምላለሁ፤ ለጥያቄያችሁ ምላሽ አልሰጥም’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”’

4 “የሰው ልጅ ሆይ፣ በእነሱ ላይ ለመፍረድ* ተዘጋጅተሃል? በእነሱ ላይ ለመፍረድ ተዘጋጅተሃል? አባቶቻቸው የሠሯቸውን አስጸያፊ ነገሮች አሳውቃቸው።+ 5 እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እስራኤልን በመረጥኩበት ቀን፣+ ለያዕቆብ ቤት ዘሮች ማልኩላቸው፤* በግብፅም ምድር ራሴን አሳወቅኳቸው።+ አዎ፣ ማልኩላቸው፤ ደግሞም ‘እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ’ አልኳቸው። 6 በዚያ ቀን፣ ከግብፅ ምድር አውጥቼ ለእነሱ ወደመረጥኳት* ወተትና ማር ወደምታፈሰው ምድር እንደማስገባቸው ማልኩላቸው።+ እሷም ከሌሎች አገሮች ሁሉ ይበልጥ ውብ* ነበረች። 7 ከዚያም እንዲህ አልኳቸው፦ ‘እያንዳንዳችሁ በዓይናችሁ ፊት ያሉትን ጸያፍ ነገሮች አስወግዱ፤ አስጸያፊ በሆኑት የግብፅ ጣዖቶች* ራሳችሁን አታርክሱ።+ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።’+

8 “‘“እነሱ ግን በእኔ ላይ ዓመፁ፤ እኔን ለመስማትም ፈቃደኞች አልነበሩም። በፊታቸው ያሉትን ጸያፍ ነገሮች አላስወገዱም፤ እንዲሁም አስጸያፊ የሆኑትን የግብፅ ጣዖቶች አልተዉም።+ በመሆኑም በግብፅ ምድር ንዴቴን በላያቸው ለማፍሰስና ቁጣዬን በእነሱ ላይ ሙሉ በሙሉ ለማውረድ ቃል ገባሁ። 9 ይሁንና እነሱ በሚኖሩባቸው ብሔራት ፊት ስሜ እንዳይረክስ ስል ስለ ስሜ እርምጃ ወሰድኩ።+ እነሱን* ከግብፅ ምድር ባወጣሁበት ጊዜ በእነዚህ ብሔራት ፊት ማንነቴን አሳውቄአቸዋለሁና።*+ 10 ስለሆነም ከግብፅ ምድር አውጥቼ ወደ ምድረ በዳ መራኋቸው።+

11 “‘“ከዚያም ደንቦቼን ሰጠኋቸው፤ ድንጋጌዎቼንም አሳወቅኳቸው፤+ ይህን ያደረግኩት እነሱን የሚከተል ሰው በእነሱ አማካኝነት በሕይወት እንዲኖር ነው።+ 12 ደግሞም በእኔና በእነሱ መካከል ምልክት እንዲሆን+ ሰንበቶቼን ሰጠኋቸው፤+ ይህን ያደረግኩት የምቀድሳቸው እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ እንዲያውቁ ነው።

13 “‘“ሆኖም የእስራኤል ቤት ሰዎች በምድረ በዳ በእኔ ላይ ዓመፁ።+ ደንቦቼን አክብረው አልተመላለሱም፤ ሰው ቢከተላቸው በሕይወት እንዲኖር የሚያደርጉትን ድንጋጌዎቼን አቃለዋል። ሰንበቶቼንም ፈጽሞ አረከሱ። በመሆኑም ጨርሶ አጠፋቸው ዘንድ በምድረ በዳ በእነሱ ላይ ታላቅ ቁጣዬን ለማፍሰስ ቃል ገባሁ።+ 14 እነሱን* ሳወጣቸው ባዩት ብሔራት ፊት ስሜ እንዳይረክስ ስል ስለ ስሜ እርምጃ ወሰድኩ።+ 15 ደግሞም ለእነሱ ወደሰጠኋት ወተትና ማር ወደምታፈሰው፣+ ከሌሎች አገሮች ሁሉ ይበልጥ ውብ* ወደሆነችው ምድር እንደማላስገባቸው በምድረ በዳ ማልኩ፤+ 16 ምክንያቱም እነሱ ድንጋጌዎቼን አቃለዋል፤ ደንቦቼንም አክብረው አልተመላለሱም፤ ሰንበቶቼንም አርክሰዋል፤ ልባቸው አስጸያፊ የሆኑትን ጣዖቶቻቸውን ተከትሏልና።+

17 “‘“እኔ* ግን እንዳላጠፋቸው ራራሁላቸው፤ ደግሞም አላጠፋኋቸውም፤ በምድረ በዳም ፈጽሜ አልፈጀኋቸውም። 18 በምድረ በዳ ልጆቻቸውን እንዲህ አልኳቸው፦+ ‘የአባቶቻችሁን ሥርዓት አትከተሉ፤+ ድንጋጌዎቻቸውንም አታክብሩ፤ ወይም አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻቸው ራሳችሁን አታርክሱ። 19 እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። ደንቦቼን አክብራችሁ ተመላለሱ፤ ድንጋጌዎቼንም ጠብቁ፤ በሥራም አውሏቸው።+ 20 ደግሞም ሰንበቶቼን ቀድሱ፤+ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቁ ዘንድ በእኔና በእናንተ መካከል ምልክት ሆነው ያገለግላሉ።’+

21 “‘“ሆኖም ልጆቹ በእኔ ላይ ያምፁ ጀመር።+ ደንቦቼን አክብረው አልተመላለሱም፤ ሰው ቢከተላቸው በሕይወት እንዲኖር የሚያደርጉትን ድንጋጌዎቼን አላከበሩም፤ ደግሞም በሥራ ላይ አላዋሉም። ሰንበቶቼን አረከሱ። በመሆኑም በምድረ በዳ ንዴቴን በላያቸው ለማፍሰስና ቁጣዬን በእነሱ ላይ ሙሉ በሙሉ ለማውረድ ቃል ገባሁ።+ 22 ይሁንና እነሱን* ሳወጣቸው ባዩት ብሔራት ፊት ስሜ እንዳይረክስ ስል እጄን መለስኩ፤+ ስለ ስሜም ስል እርምጃ ወሰድኩ።+ 23 ደግሞም በብሔራት መካከል እንደምበታትናቸውና ወደተለያዩ አገሮች እንደምሰዳቸው በምድረ በዳ ማልኩ፤+ 24 ምክንያቱም እነሱ ድንጋጌዎቼን አላከበሩም፤ ደንቦቼንም አቃለዋል፤+ ሰንበቶቼን አርክሰዋል፤ ደግሞም እነሱ* አስጸያፊ የሆኑትን የአባቶቻቸውን ጣዖቶች ተከትለዋል።+ 25 እኔም ጥሩ ባልሆነ ሥርዓት እንዲመላለሱና ሕይወት የማያስገኙላቸውን ድንጋጌዎች እንዲከተሉ ተውኳቸው።+ 26 አስከፊ ሁኔታ ይደርስባቸው ዘንድ እያንዳንዱን የበኩር ልጅ ለእሳት አሳልፈው ሲሰጡ+ በገዛ መሥዋዕታቸው እንዲረክሱ አደረግኩ፤ ይህም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቁ ዘንድ ነው።”’

27 “ስለዚህ የሰው ልጅ ሆይ፣ ለእስራኤል ቤት ሰዎች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በዚህም መንገድ አባቶቻችሁ ለእኔ ያላቸውን ታማኝነት በማጉደል ሰደቡኝ። 28 ለእነሱ ለመስጠት ወደማልኩላቸው ምድር አመጣኋቸው።+ ከፍ ያለ ኮረብታና የለመለመ ዛፍ ሁሉ ባዩ ጊዜ+ በዚያ መሥዋዕታቸውንና ቁጣ የሚያነሳሳ መባቸውን ያቀርቡ ጀመር። በዚያም ደስ የሚያሰኘውን* የመሥዋዕቶቻቸውን መዓዛ አቀረቡ፤ የመጠጥ መባቸውንም አፈሰሱ። 29 እኔም እንዲህ አልኳቸው፦ ‘እናንተ የምትሄዱበት ይህ ከፍ ያለ የማምለኪያ ቦታ ምንድን ነው? (ይህ ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ ባማ * ተብሎ ይጠራል።)’”’+

30 “እንግዲህ ለእስራኤል ቤት ሰዎች እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አባቶቻችሁ አስጸያፊ ከሆኑ ጣዖቶቻቸው ጋር መንፈሳዊ ምንዝር ለመፈጸም ሲሉ እነሱን በመከተል ራሳቸውን እንዳረከሱ ሁሉ እናንተም ራሳችሁን ታረክሳላችሁ?+ 31 አስጸያፊ ለሆኑት ጣዖቶቻችሁ ሁሉ መሥዋዕት በማቅረብ ይኸውም ልጆቻችሁን ለእሳት አሳልፋችሁ በመስጠት እስከ ዛሬ ድረስ ራሳችሁን እያረከሳችሁ ነው?+ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ታዲያ እንዲህ እያደረጋችሁ ለጥያቄያችሁ ምላሽ መስጠት ይኖርብኛል?”’+

“‘በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ለጥያቄያችሁ ምላሽ አልሰጥም።+ 32 “እንጨትና ድንጋይ እንደሚያመልኩት* ብሔራት፣ እንደ ሌሎቹም አገሮች ሕዝቦች እንሁን”+ በማለት የምታውጠነጥኑት ሐሳብ* ፈጽሞ አይሳካም።’”

33 “‘በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘በኃያል እጅና በተዘረጋች ክንድ እንዲሁም ታላቅ ቁጣ በማፍሰስ በእናንተ ላይ ንጉሥ ሆኜ እገዛለሁ።+ 34 በኃያል እጅና በተዘረጋች ክንድ እንዲሁም ታላቅ ቁጣ በማፍሰስ ከሕዝቦች መካከል አወጣችኋለሁ፤ ከተበተናችሁባቸውም አገሮች እሰበስባችኋለሁ።+ 35 ወደ ሕዝቦች ምድረ በዳ አመጣችኋለሁ፤ በዚያም ፊት ለፊት እፋረዳችኋለሁ።+

36 “‘አባቶቻችሁን በግብፅ ምድረ በዳ እንደተፋረድኳቸው ሁሉ እናንተንም እፋረዳችኋለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 37 ‘ከእረኛ በትር በታች አሳልፋችኋለሁ፤+ ደግሞም በቃል ኪዳኑ ግዴታ ውስጥ* እንድትገቡ አደርጋለሁ። 38 ሆኖም በእኔ ላይ የሚያምፁትንና በደል የሚፈጽሙትን ከመካከላችሁ አስወግዳለሁ።+ የባዕድ አገር ሰው ሆነው ከሚኖሩበት ምድር አወጣቸዋለሁና፤ ወደ እስራኤል ምድር ግን አይገቡም፤+ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’

39 “የእስራኤል ቤት ሰዎች ሆይ፣ እናንተን በተመለከተ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እያንዳንዳችሁ ሄዳችሁ አስጸያፊ የሆኑትን ጣዖቶቻችሁን አገልግሉ።+ ከዚያ በኋላ ግን እኔን ባለመስማታችሁ መዘዙን ትቀበላላችሁ፤ በመሥዋዕቶቻችሁና አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻችሁ ከእንግዲህ ወዲህ ቅዱስ ስሜን አታረክሱም።’+

40 “‘በቅዱሱ ተራራዬ፣ ከፍ ባለውም የእስራኤል ተራራ ላይ፣’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘መላው የእስራኤል ቤት ሰዎች፣ አዎ ሁሉም በዚያ በምድሪቱ ላይ ያገለግሉኛልና።+ በዚያም በእነሱ ደስ እሰኛለሁ፤ ደግሞም ቅዱስ ከሆኑት ነገሮቻችሁ ሁሉ መዋጮዎቻችሁንና የመባችሁን የፍሬ በኩራት እሻለሁ።+ 41 ከሕዝቦች መካከል በማወጣችሁና ከተበተናችሁባቸው አገሮች በምሰበስባችሁ ጊዜ+ ደስ በሚያሰኘው* መዓዛ የተነሳ በእናንተ እረካለሁ፤ በብሔራትም ፊት በእናንተ መካከል እቀደሳለሁ።’+

42 “‘ለአባቶቻችሁ ለመስጠት ወደማልኩላቸው አገር፣ ወደ እስራኤል ምድር ሳመጣችሁ+ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።+ 43 በዚያም ራሳችሁን ያረከሳችሁባቸውን ምግባራችሁንና ድርጊቶቻችሁን ሁሉ ታስታውሳላችሁ፤+ በሠራችኋቸውም መጥፎ ነገሮች ሁሉ የተነሳ ራሳችሁን* ትጸየፋላችሁ።+ 44 የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እንደ ክፉ ምግባራችሁ ወይም እንደ ብልሹ ተግባራችሁ ሳይሆን፣ ስለ ስሜ ስል እርምጃ በምወስድበት ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”

45 የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 46 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን በስተ ደቡብ አቅጣጫ አዙረህ ወደ ደቡብ ተናገር፤ በደቡብም ምድር ባለው ደን ላይ ትንቢት ተናገር። 47 በደቡብ ለሚገኘው ደን እንዲህ በል፦ ‘የይሖዋን ቃል ስማ። ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በአንተ ላይ እሳት አነዳለሁ፤+ እሳቱም በአንተ ውስጥ ያለውን የለመለመውንና ደረቁን ዛፍ ሁሉ ይበላል። የሚንቦገቦገው ነበልባል አይጠፋም፤+ እሱም ከደቡብ እስከ ሰሜን ያለውን ፊት* ሁሉ ይለበልባል። 48 ሥጋ ለባሽም* ሁሉ እሳቱን ያነደድኩት እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያያል፤ በመሆኑም እሳቱ አይጠፋም።”’”+

49 እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ወዮ! እነሱ ስለ እኔ ‘ሁልጊዜ የሚናገረው እንቆቅልሽ* ነው’ ይላሉ።”

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ