ሆሴዕ
14 “እስራኤል ሆይ፣ በበደልህ ስለተሰናከልክ
ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ተመለስ።+
2 ይህን ቃል ይዛችሁ ወደ ይሖዋ ተመለሱ፤
እንዲህ በሉት፦ ‘በደላችንን ይቅር በለን፤+ መልካም የሆነውንም ነገር ተቀበለን፤
3 አሦር አያድነንም።+
4 እኔም ከዳተኛነታቸውን እፈውሳለሁ።+
5 እኔ ለእስራኤል እንደ ጠል እሆናለሁ፤
እሱም እንደ አበባ ያብባል፤
እንደ ሊባኖስ ዛፎችም ሥሮቹን ይሰዳል።
6 ቀንበጦቹ ይንሰራፋሉ፤
ውበቱ እንደ ወይራ ዛፍ፣
መዓዛውም እንደ ሊባኖስ ዛፍ ይሆናል።
7 እነሱም ዳግመኛ በጥላው ሥር ይኖራሉ።
እህል ያበቅላሉ፤ እንደ ወይን ተክልም ያብባሉ።+
ዝናው* እንደ ሊባኖስ የወይን ጠጅ ይሆናል።
8 ኤፍሬም ‘ከእንግዲህ ከጣዖቶች ጋር ምን ጉዳይ አለኝ?’ ይላል።+
መልስ እሰጠዋለሁ፤ ደግሞም እጠብቀዋለሁ።+
እኔ እንደለመለመ የጥድ ዛፍ እሆናለሁ።
ከእኔም ፍሬ ታገኛላችሁ።”
9 ጥበበኛ ማን ነው? እነዚህን ነገሮች ያስተውል።
ልባም የሆነ ማን ነው? እነዚህን ነገሮች ይወቅ።