ዕንባቆም
2 በጥበቃ ቦታዬ ላይ እሰየማለሁ፤+
በመከላከያ ግንቧም ላይ እቆማለሁ።
በእኔ አማካኝነት ምን መናገር እንደሚፈልግ ለማየትና
በምወቀስበት ጊዜ ምን መልስ እንደምሰጥ ለማወቅ በንቃት እጠባበቃለሁ።
2 ይሖዋም እንዲህ ሲል መለሰልኝ፦
3 ራእዩ የተወሰነለትን ጊዜ ገና ይጠብቃልና፤
ወደ ፍጻሜውም ይቸኩላል፤ ደግሞም አይዋሽም።
ያላንዳች ጥርጥር ይፈጸማልና።
ራእዩ አይዘገይም!
4 ኩሩ የሆነውን ተመልከት፤*
ውስጡ ቀና አይደለም።
5 በእርግጥም የወይን ጠጅ አታላይ ስለሆነ
እብሪተኛው ሰው ግቡን አይመታም።
ብሔራትን ሁሉ ወደ ራሱ መሰብሰቡን ይቀጥላል፤
ሕዝቦችንም ሁሉ ለራሱ ያከማቻል።+
6 እነዚህ ሁሉ ሰዎች በእሱ ላይ አይተርቱም? ደግሞስ አሽሙርና ግራ የሚያጋባ ቃል አይሰነዝሩም?+
እንዲህ ይላሉ፦
‘የራሱ ያልሆነውን የሚያጋብስ፣
ዕዳውንም የሚያበዛ ወዮለት!
ይህን የሚያደርገው እስከ መቼ ነው?
7 አበዳሪዎችህ በድንገት አይነሱም?
ተነስተው በኃይል ይነቀንቁሃል፤
በእነሱም እጅ ለብዝበዛ ትዳረጋለህ።+
8 ብዙ ብሔራትን ስለዘረፍክ
ከሕዝቦቹ መካከል የቀሩት ሁሉ ይዘርፉሃል፤+
ምክንያቱም አንተ የሰው ልጆችን ደም አፍስሰሃል፤
በምድሪቱ፣ በከተሞችና
በዚያ በሚኖሩት ሁሉ ላይ ግፍ ፈጽመሃል።+
9 ከጥፋት እጅ ያመልጥ ዘንድ
ጎጆውን ከፍ ባለ ቦታ ላይ ለመሥራት
ለቤቱ አግባብ ያልሆነ ጥቅም የሚሰበስብ ወዮለት!
10 በቤትህ ላይ አሳፋሪ ነገር አሲረሃል።
ብዙ ሕዝቦችን ጠራርገህ በማጥፋት በራስህ* ላይ ኃጢአት ሠርተሃል።+
11 ድንጋይ ከግንቡ ውስጥ ይጮኻል፤
ከጣሪያው እንጨቶችም መካከል አንድ ወራጅ ይመልስለታል።
12 ከተማን ደም በማፍሰስ ለሚገነባና
በዓመፅ ለሚመሠርታት ወዮለት!
13 እነሆ፣ ሰዎች እሳት ለሚበላው ነገር እንዲደክሙ፣
ብሔራትም ከንቱ ለሆነ ነገር እንዲለፉ የሚያደርገው የሠራዊት ጌታ ይሖዋ አይደለም?+
14 ውኃ ባሕርን እንደሚሸፍን፣
ምድርም የይሖዋን ክብር በማወቅ ትሞላለችና።+
15 እርቃናቸውን ለማየት ሲል
ታላቅ ቁጣውንና ንዴቱን ቀላቅሎ
ለባልንጀሮቹ መጠጥ በመስጠት እንዲሰክሩ ለሚያደርግ ሰው ወዮለት!
16 በክብር ፋንታ ውርደት ትሞላለህ።
አንተ ራስህም ጠጣ፤ ያልተገረዝክ መሆንህንም አሳይ።*
በይሖዋ ቀኝ እጅ ያለው ጽዋ ወደ አንተ ይዞራል፤+
ክብርህም በውርደት ይሸፈናል፤
17 በሊባኖስ ላይ የተፈጸመው ግፍ ይሸፍንሃል፤
አራዊትንም ያሸበረው ጥፋት በአንተ ላይ ይደርሳል፤
ምክንያቱም አንተ የሰዎችን ደም አፍስሰሃል፤
በምድር፣ በከተሞቿና
በውስጧ በሚኖሩ ሁሉ ላይ ግፍ ፈጽመሃል።+
18 የተቀረጸ ምስል፣
ሠሪው የቀረጸው ከሆነ ምን ጥቅም አለው?
ሠሪው እምነት ቢጥልበትም እንኳ
ከብረት የተሠራ ሐውልትና* ሐሰትን የሚናገር አስተማሪ ምን ፋይዳ አለው?
መናገር የማይችሉ ከንቱ አማልክት መሥራት ምን እርባና አለው?+
19 እንጨቱን “ንቃ!”
መናገር የማይችለውንም ድንጋይ “ተነስ! አስተምረን!” ለሚል ወዮለት!
20 ይሖዋ ግን በቅዱስ ቤተ መቅደሱ ውስጥ ነው።+
ምድር ሁሉ በፊቱ ጸጥ በይ!’”+