የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዕንባቆም 2
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዕንባቆም የመጽሐፉ ይዘት

      • ‘የሚናገረውን ለማየት በንቃት እጠባበቃለሁ’ (1)

      • ይሖዋ ለነቢዩ የሰጠው መልስ (2-​20)

        • ‘ራእዩን በተስፋ ጠብቅ!’ (3)

        • ‘ጻድቅ በታማኝነቱ በሕይወት ይኖራል’ (4)

        • ለከለዳውያን የተነገሩ አምስት ወዮታዎች (6-20)

          • ምድር ይሖዋን በማወቅ ትሞላለች (14)

ዕንባቆም 2:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 21:8፤ ሚክ 7:7

ዕንባቆም 2:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አቀላጥፎ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 31:9, 11
  • +ዘፀ 17:14

ዕንባቆም 2:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሚዘገይ ቢመስልም።”

  • *

    ወይም “ቢዘገይ እንኳ በጉጉት ጠብቀው!”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሚክ 7:7

ዕንባቆም 2:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “እነሆ፣ ነፍሱ በትዕቢት ተወጥራለች።”

  • *

    “በእምነቱ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 3:36፤ ሮም 1:17፤ ገላ 3:11፤ ዕብ 10:38

ዕንባቆም 2:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሱን።”

  • *

    ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 14:16, 17

ዕንባቆም 2:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 14:4

ዕንባቆም 2:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 51:11

ዕንባቆም 2:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 13:19፤ ኤር 27:6, 7፤ ዘካ 2:7-9
  • +2ዜና 36:17፤ መዝ 137:8

ዕንባቆም 2:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በነፍስህ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 14:20

ዕንባቆም 2:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 51:58

ዕንባቆም 2:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 72:19፤ ኢሳ 11:9፤ ዘካ 14:9

ዕንባቆም 2:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ተንገዳገድም” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 75:8፤ ኢሳ 51:22, 23፤ ኤር 25:28፤ 51:57

ዕንባቆም 2:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 137:8፤ ኤር 50:28፤ 51:24

ዕንባቆም 2:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቀልጦ የተሠራ ሐውልትና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 42:17፤ 44:19, 20፤ 45:20

ዕንባቆም 2:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 40:19፤ 46:6
  • +ኤር 51:17

ዕንባቆም 2:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 6:1
  • +መዝ 76:8፤ 115:3፤ ዘካ 2:13

ተዛማጅ ሐሳብ

ዕን. 2:1ኢሳ 21:8፤ ሚክ 7:7
ዕን. 2:2ዘዳ 31:9, 11
ዕን. 2:2ዘፀ 17:14
ዕን. 2:3ሚክ 7:7
ዕን. 2:4ዮሐ 3:36፤ ሮም 1:17፤ ገላ 3:11፤ ዕብ 10:38
ዕን. 2:5ኢሳ 14:16, 17
ዕን. 2:6ኢሳ 14:4
ዕን. 2:7ኤር 51:11
ዕን. 2:8ኢሳ 13:19፤ ኤር 27:6, 7፤ ዘካ 2:7-9
ዕን. 2:82ዜና 36:17፤ መዝ 137:8
ዕን. 2:10ኢሳ 14:20
ዕን. 2:13ኤር 51:58
ዕን. 2:14መዝ 72:19፤ ኢሳ 11:9፤ ዘካ 14:9
ዕን. 2:16መዝ 75:8፤ ኢሳ 51:22, 23፤ ኤር 25:28፤ 51:57
ዕን. 2:17መዝ 137:8፤ ኤር 50:28፤ 51:24
ዕን. 2:18ኢሳ 42:17፤ 44:19, 20፤ 45:20
ዕን. 2:19ኢሳ 40:19፤ 46:6
ዕን. 2:19ኤር 51:17
ዕን. 2:20ኢሳ 6:1
ዕን. 2:20መዝ 76:8፤ 115:3፤ ዘካ 2:13
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዕንባቆም 2:1-20

ዕንባቆም

2 በጥበቃ ቦታዬ ላይ እሰየማለሁ፤+

በመከላከያ ግንቧም ላይ እቆማለሁ።

በእኔ አማካኝነት ምን መናገር እንደሚፈልግ ለማየትና

በምወቀስበት ጊዜ ምን መልስ እንደምሰጥ ለማወቅ በንቃት እጠባበቃለሁ።

 2 ይሖዋም እንዲህ ሲል መለሰልኝ፦

“ድምፁን ከፍ አድርጎ የሚያነበው ሰው በቀላሉ* እንዲያነበው+

ራእዩን ጻፈው፤ በጽላትም ላይ ግልጽ በሆነ መንገድ ቅረጸው።+

 3 ራእዩ የተወሰነለትን ጊዜ ገና ይጠብቃልና፤

ወደ ፍጻሜውም ይቸኩላል፤ ደግሞም አይዋሽም።

ቢዘገይ* እንኳ በተስፋ ጠብቀው!*+

ያላንዳች ጥርጥር ይፈጸማልና።

ራእዩ አይዘገይም!

 4 ኩሩ የሆነውን ተመልከት፤*

ውስጡ ቀና አይደለም።

ጻድቅ ግን በታማኝነቱ* በሕይወት ይኖራል።+

 5 በእርግጥም የወይን ጠጅ አታላይ ስለሆነ

እብሪተኛው ሰው ግቡን አይመታም።

ፍላጎቱን* እንደ መቃብር* ያሰፋል፤

እሱ እንደ ሞት ነው፤ ደግሞም ሊጠግብ አይችልም።

ብሔራትን ሁሉ ወደ ራሱ መሰብሰቡን ይቀጥላል፤

ሕዝቦችንም ሁሉ ለራሱ ያከማቻል።+

 6 እነዚህ ሁሉ ሰዎች በእሱ ላይ አይተርቱም? ደግሞስ አሽሙርና ግራ የሚያጋባ ቃል አይሰነዝሩም?+

እንዲህ ይላሉ፦

‘የራሱ ያልሆነውን የሚያጋብስ፣

ዕዳውንም የሚያበዛ ወዮለት!

ይህን የሚያደርገው እስከ መቼ ነው?

 7 አበዳሪዎችህ በድንገት አይነሱም?

ተነስተው በኃይል ይነቀንቁሃል፤

በእነሱም እጅ ለብዝበዛ ትዳረጋለህ።+

 8 ብዙ ብሔራትን ስለዘረፍክ

ከሕዝቦቹ መካከል የቀሩት ሁሉ ይዘርፉሃል፤+

ምክንያቱም አንተ የሰው ልጆችን ደም አፍስሰሃል፤

በምድሪቱ፣ በከተሞችና

በዚያ በሚኖሩት ሁሉ ላይ ግፍ ፈጽመሃል።+

 9 ከጥፋት እጅ ያመልጥ ዘንድ

ጎጆውን ከፍ ባለ ቦታ ላይ ለመሥራት

ለቤቱ አግባብ ያልሆነ ጥቅም የሚሰበስብ ወዮለት!

10 በቤትህ ላይ አሳፋሪ ነገር አሲረሃል።

ብዙ ሕዝቦችን ጠራርገህ በማጥፋት በራስህ* ላይ ኃጢአት ሠርተሃል።+

11 ድንጋይ ከግንቡ ውስጥ ይጮኻል፤

ከጣሪያው እንጨቶችም መካከል አንድ ወራጅ ይመልስለታል።

12 ከተማን ደም በማፍሰስ ለሚገነባና

በዓመፅ ለሚመሠርታት ወዮለት!

13 እነሆ፣ ሰዎች እሳት ለሚበላው ነገር እንዲደክሙ፣

ብሔራትም ከንቱ ለሆነ ነገር እንዲለፉ የሚያደርገው የሠራዊት ጌታ ይሖዋ አይደለም?+

14 ውኃ ባሕርን እንደሚሸፍን፣

ምድርም የይሖዋን ክብር በማወቅ ትሞላለችና።+

15 እርቃናቸውን ለማየት ሲል

ታላቅ ቁጣውንና ንዴቱን ቀላቅሎ

ለባልንጀሮቹ መጠጥ በመስጠት እንዲሰክሩ ለሚያደርግ ሰው ወዮለት!

16 በክብር ፋንታ ውርደት ትሞላለህ።

አንተ ራስህም ጠጣ፤ ያልተገረዝክ መሆንህንም አሳይ።*

በይሖዋ ቀኝ እጅ ያለው ጽዋ ወደ አንተ ይዞራል፤+

ክብርህም በውርደት ይሸፈናል፤

17 በሊባኖስ ላይ የተፈጸመው ግፍ ይሸፍንሃል፤

አራዊትንም ያሸበረው ጥፋት በአንተ ላይ ይደርሳል፤

ምክንያቱም አንተ የሰዎችን ደም አፍስሰሃል፤

በምድር፣ በከተሞቿና

በውስጧ በሚኖሩ ሁሉ ላይ ግፍ ፈጽመሃል።+

18 የተቀረጸ ምስል፣

ሠሪው የቀረጸው ከሆነ ምን ጥቅም አለው?

ሠሪው እምነት ቢጥልበትም እንኳ

ከብረት የተሠራ ሐውልትና* ሐሰትን የሚናገር አስተማሪ ምን ፋይዳ አለው?

መናገር የማይችሉ ከንቱ አማልክት መሥራት ምን እርባና አለው?+

19 እንጨቱን “ንቃ!”

መናገር የማይችለውንም ድንጋይ “ተነስ! አስተምረን!” ለሚል ወዮለት!

እነሆ፣ በወርቅና በብር ተለብጧል፤+

በውስጡም እስትንፋስ የለም።+

20 ይሖዋ ግን በቅዱስ ቤተ መቅደሱ ውስጥ ነው።+

ምድር ሁሉ በፊቱ ጸጥ በይ!’”+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ