የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሶፎንያስ 2
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ሶፎንያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • የቁጣው ቀን ሳይደርስባችሁ ይሖዋን ፈልጉ (1-3)

        • ጽድቅንና የዋህነትን ፈልጉ (3)

        • ‘ምናልባት ትሰወሩ ይሆናል’ (3)

      • በአጎራባች ብሔራት ላይ የተላለፈ ፍርድ (4-15)

ሶፎንያስ 2:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 1:4፤ ኤር 6:15
  • +ኢዩ 1:14፤ 2:15, 16

ሶፎንያስ 2:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 23:26፤ 2ዜና 36:16, 17፤ ኤር 23:20፤ ሰቆ 4:11

ሶፎንያስ 2:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ፍርዶቹን።”

  • *

    ወይም “ትሑታን።”

  • *

    ወይም “ትሕትናን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 55:6፤ አሞጽ 5:6
  • +ዘፍ 7:13, 16፤ ኢሳ 26:20፤ ኢዩ 2:12, 14፤ አሞጽ 5:15

ሶፎንያስ 2:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በቀትር።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 47:5
  • +ኤር 25:17, 20፤ አሞጽ 1:6-8፤ ዘካ 9:5, 6

ሶፎንያስ 2:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 25:16, 17

ሶፎንያስ 2:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “እንክብካቤ ያደርግላቸዋልና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 11:11፤ ኤር 31:7፤ ሐጌ 1:12
  • +መዝ 126:1፤ ኤር 23:3፤ ሕዝ 39:25፤ አሞጽ 9:14፤ ሚክ 2:12፤ 4:10፤ ሶፎ 3:20

ሶፎንያስ 2:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 48:26, 27፤ ሕዝ 25:8, 9
  • +ኤር 49:1፤ ሕዝ 25:3
  • +መዝ 83:2, 4

ሶፎንያስ 2:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 25:11፤ አሞጽ 2:1, 2
  • +ዘፍ 19:24, 25
  • +አሞጽ 1:13-15፤ ይሁዳ 7

ሶፎንያስ 2:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 16:6፤ ኤር 48:29

ሶፎንያስ 2:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሚያሸብር።”

  • *

    ወይም “ያመነምናቸዋልና።”

  • *

    ወይም “እሱን ያመልኩታል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 22:27፤ ሚል 1:11

ሶፎንያስ 2:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 43:3፤ ሕዝ 30:4, 5

ሶፎንያስ 2:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ናሆም 3:7

ሶፎንያስ 2:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “አንድ ብሔር ያለው እንስሳ ሁሉ።”

  • *

    ወይም “ገርጌሶ።” ጠፍጠፍ ያለ ረጅም መንቆር ያለው ትልቅ አሞራ።

ሶፎንያስ 2:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ናሆም 3:1, 19

ተዛማጅ ሐሳብ

ሶፎ. 2:1ኢሳ 1:4፤ ኤር 6:15
ሶፎ. 2:1ኢዩ 1:14፤ 2:15, 16
ሶፎ. 2:22ነገ 23:26፤ 2ዜና 36:16, 17፤ ኤር 23:20፤ ሰቆ 4:11
ሶፎ. 2:3ኢሳ 55:6፤ አሞጽ 5:6
ሶፎ. 2:3ዘፍ 7:13, 16፤ ኢሳ 26:20፤ ኢዩ 2:12, 14፤ አሞጽ 5:15
ሶፎ. 2:4ኤር 47:5
ሶፎ. 2:4ኤር 25:17, 20፤ አሞጽ 1:6-8፤ ዘካ 9:5, 6
ሶፎ. 2:5ሕዝ 25:16, 17
ሶፎ. 2:7ኢሳ 11:11፤ ኤር 31:7፤ ሐጌ 1:12
ሶፎ. 2:7መዝ 126:1፤ ኤር 23:3፤ ሕዝ 39:25፤ አሞጽ 9:14፤ ሚክ 2:12፤ 4:10፤ ሶፎ 3:20
ሶፎ. 2:8ኤር 48:26, 27፤ ሕዝ 25:8, 9
ሶፎ. 2:8ኤር 49:1፤ ሕዝ 25:3
ሶፎ. 2:8መዝ 83:2, 4
ሶፎ. 2:9ሕዝ 25:11፤ አሞጽ 2:1, 2
ሶፎ. 2:9ዘፍ 19:24, 25
ሶፎ. 2:9አሞጽ 1:13-15፤ ይሁዳ 7
ሶፎ. 2:10ኢሳ 16:6፤ ኤር 48:29
ሶፎ. 2:11መዝ 22:27፤ ሚል 1:11
ሶፎ. 2:12ኢሳ 43:3፤ ሕዝ 30:4, 5
ሶፎ. 2:13ናሆም 3:7
ሶፎ. 2:15ናሆም 3:1, 19
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ሶፎንያስ 2:1-15

ሶፎንያስ

2 እናንተ ኀፍረት የማይሰማችሁ ሕዝቦች ሆይ፣+

በአንድነት ተሰብሰቡ፤ አዎ ተሰብሰቡ።+

 2 የተላለፈው ውሳኔ ከመፈጸሙ በፊት፣

ቀኑ እንደ ገለባ ከማለፉ በፊት፣

የሚነደው የይሖዋ ቁጣ ሳይመጣባችሁ፣+

የይሖዋ የቁጣ ቀን ሳይደርስባችሁ፣

 3 እናንተ የጽድቅ ድንጋጌዎቹን* የምታከብሩ፣

በምድር ላይ የምትኖሩ የዋሆች* ሁሉ ይሖዋን ፈልጉ።+

ጽድቅን ፈልጉ፤ የዋህነትን* ፈልጉ።

ምናልባት በይሖዋ የቁጣ ቀን ትሰወሩ ይሆናል።+

 4 ጋዛ የተተወች ከተማ ትሆናለችና፤

አስቀሎንም ባድማ ትሆናለች።+

አሽዶድ በጠራራ ፀሐይ* ትባረራለች፤

ኤቅሮንም ከሥሯ ትመነገላለች።+

 5 “በባሕሩ ዳርቻ ለሚኖረው ሕዝብ ይኸውም ለከሪታውያን ብሔር ወዮለት!+

የይሖዋ ቃል በአንተ ላይ ነው።

የፍልስጤማውያን ምድር የሆንሽው ከነአን ሆይ፣ አጠፋሻለሁ፤

አንድም ነዋሪ አይተርፍም።

 6 የባሕሩ ዳርቻም መሰማሪያ ይሆናል፤

ለእረኞች የውኃ ጉድጓድና ለበጎች ከድንጋይ የተሠራ ጉረኖ ይኖረዋል።

 7 ከይሁዳ ቤት ለቀሩት ሰዎች መኖሪያ ስፍራ ይሆናል፤+

በዚያም የግጦሽ ቦታ ያገኛሉ።

በምሽት በአስቀሎን ቤቶች ውስጥ ይተኛሉ።

አምላካቸው ይሖዋ ትኩረቱን በእነሱ ላይ ያደርጋልና፤*

የተማረኩባቸውንም ሰዎች መልሶ ይሰበስባል።”+

 8 “ሞዓብ የሰነዘረችውን ነቀፋና+ የአሞናውያንን ስድብ ሰምቻለሁ፤+

እነሱ በሕዝቤ ላይ ተሳልቀዋል፤ ግዛታቸውንም ለመውሰድ በእብሪት ዝተዋል።+

 9 ስለዚህ በሕያውነቴ እምላለሁ” ይላል የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣

“ሞዓብ እንደ ሰዶም፣+

አሞናውያንም እንደ ገሞራ ይሆናሉ፤+

ሳማ የወረሰው ምድርና የጨው ጉድጓድ ይሆናሉ፤ ለዘለቄታውም ባድማ ሆነው ይቀራሉ።+

የሕዝቤ ቀሪዎች ይዘርፏቸዋል፤

ከገዛ ብሔሬ የቀሩት ሰዎችም ይወርሷቸዋል።

10 ከኩራታቸው የተነሳ ይህ ይደርስባቸዋል፤+

ምክንያቱም በሠራዊት ጌታ በይሖዋ ሕዝብ ላይ ተሳልቀዋል፤ ራሳቸውንም ከፍ ከፍ አድርገዋል።

11 ይሖዋ በእነሱ ዘንድ የተፈራ* ይሆናል፤

በምድር ላይ ያሉትን አማልክት ሁሉ እንዳልነበሩ ያደርጋቸዋልና፤*

የብሔራት ደሴቶች ሁሉ በያሉበት ሆነው

ለእሱ ይሰግዳሉ።*+

12 እናንተም ኢትዮጵያውያን በሰይፌ ትገደላላችሁ።+

13 እሱ እጁን ወደ ሰሜን ይዘረጋል፤ አሦርንም ያጠፋል፤

ነነዌንም ባድማና እንደ በረሃ ደረቅ ያደርጋታል።+

14 መንጎች ይኸውም ሁሉም ዓይነት የዱር እንስሳት* በውስጧ ይተኛሉ።

ሻላ* እና ጃርት በፈራረሱት ዓምዶቿ መካከል ያድራሉ።

የዝማሬ ድምፅ በመስኮት ይሰማል።

ደጃፍ ላይ ፍርስራሽ ይኖራል፤

የአርዘ ሊባኖስ እንጨቶቹ እንዲጋለጡ ያደርጋልና።

15 በልቧ ‘እኔ ብቻ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለም’ ስትል የነበረችው

ያለስጋት የተቀመጠችው ኩሩዋ ከተማ ይህች ናት።

ምንኛ አስፈሪ ቦታ ሆነች!

የዱር እንስሳት የሚተኙባት ስፍራ ሆናለች።

በእሷ በኩል የሚያልፍ ሁሉ ያፏጫል፤ ራሱንም ይነቀንቃል።”+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ