የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘካርያስ 4
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘካርያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ራእይ 5፦ መቅረዝና ሁለት የወይራ ዛፎች (1-14)

        • ‘በመንፈሴ እንጂ፣ በጉልበት አይደለም’ (6)

        • ሥራው በትንሹ የተጀመረበትን ቀን አትናቁ (10)

ዘካርያስ 4:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 25:31፤ 1ነገ 7:48, 49
  • +ዘፀ 25:37

ዘካርያስ 4:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘካ 4:11, 14፤ ራእይ 11:3, 4

ዘካርያስ 4:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 6:34፤ 15:14
  • +1ሳሙ 17:45፤ ሆሴዕ 1:7

ዘካርያስ 4:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሜዳ።”

  • *

    ወይም “ከላይ የሚቀመጠውን ድንጋይ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕዝራ 3:2፤ ሐጌ 1:1
  • +ኢሳ 40:4

ዘካርያስ 4:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕዝራ 3:8, 10፤ 5:14, 16
  • +ዕዝራ 6:14፤ ዘካ 6:12

ዘካርያስ 4:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የጥቂቱን ነገር ቀን።”

  • *

    ቃል በቃል “ድንጋዩን፣ ቆርቆሮውን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕዝራ 3:12፤ ሐጌ 2:3
  • +2ዜና 16:9፤ ምሳሌ 15:3፤ ኤር 16:17፤ ራእይ 5:6

ዘካርያስ 4:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘካ 4:2, 3

ዘካርያስ 4:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ብዙ ፍሬ የያዙትን የዛፉን ቅርንጫፎች ያመለክታል።

ዘካርያስ 4:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሐጌ 2:4፤ ራእይ 11:3, 4

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘካ. 4:2ዘፀ 25:31፤ 1ነገ 7:48, 49
ዘካ. 4:2ዘፀ 25:37
ዘካ. 4:3ዘካ 4:11, 14፤ ራእይ 11:3, 4
ዘካ. 4:6መሳ 6:34፤ 15:14
ዘካ. 4:61ሳሙ 17:45፤ ሆሴዕ 1:7
ዘካ. 4:7ዕዝራ 3:2፤ ሐጌ 1:1
ዘካ. 4:7ኢሳ 40:4
ዘካ. 4:9ዕዝራ 3:8, 10፤ 5:14, 16
ዘካ. 4:9ዕዝራ 6:14፤ ዘካ 6:12
ዘካ. 4:10ዕዝራ 3:12፤ ሐጌ 2:3
ዘካ. 4:102ዜና 16:9፤ ምሳሌ 15:3፤ ኤር 16:17፤ ራእይ 5:6
ዘካ. 4:11ዘካ 4:2, 3
ዘካ. 4:14ሐጌ 2:4፤ ራእይ 11:3, 4
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘካርያስ 4:1-14

ዘካርያስ

4 ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ ተመልሶ መጥቶ አንድን ሰው ከእንቅልፉ እንደሚቀሰቅስ ቀሰቀሰኝ። 2 ከዚያም “የምታየው ምንድን ነው?” አለኝ።

እኔም እንዲህ አልኩት፦ “እነሆ፣ ሙሉ በሙሉ በወርቅ የተሠራና ላዩ ላይ ሳህን ያለበት መቅረዝ+ ይታየኛል። በላዩ ላይ ሰባት መብራቶች፣ አዎ ሰባት መብራቶች አሉበት፤+ አናቱ ላይ ያሉት ሰባት መብራቶችም ሰባት ቱቦዎች አሏቸው። 3 ከጎኑም አንዱ ከሳህኑ በስተ ቀኝ፣ አንዱ ደግሞ በስተ ግራ የቆሙ ሁለት የወይራ ዛፎች አሉ።”+

4 ከዚያም ሲያነጋግረኝ የነበረውን መልአክ “ጌታዬ ሆይ፣ የእነዚህ ነገሮች ትርጉም ምንድን ነው?” በማለት ጠየቅኩት። 5 ከእኔ ጋር ሲነጋገር የነበረውም መልአክ “የእነዚህ ነገሮች ትርጉም ምን እንደሆነ አታውቅም?” ሲል ጠየቀኝ።

እኔም “ጌታዬ ሆይ፣ አላውቅም” ብዬ መለስኩለት።

6 በዚህ ጊዜ እንዲህ አለኝ፦ “ይሖዋ ለዘሩባቤል የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ ‘“በመንፈሴ እንጂ፣+ በወታደራዊ ኃይል ወይም በጉልበት አይደለም”+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።  7 ታላቅ ተራራ ሆይ፣ አንተ ማን ነህ? በዘሩባቤል+ ፊት ደልዳላ መሬት* ትሆናለህ።+ “እንዴት ያምራል! እንዴት ያምራል!” እያሉ በሚጮኹበት ጊዜ እሱ የመደምደሚያውን ድንጋይ* ያወጣል።’”

8 የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ዳግመኛ ወደ እኔ መጣ፦ 9 “የዘሩባቤል እጆች የዚህን ቤት መሠረት ጥለዋል፤+ የገዛ እጆቹም ያጠናቅቁታል።+ እኔንም ወደ እናንተ የላከኝ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንደሆነ ታውቃላችሁ። 10 ሥራው በትንሹ የተጀመረበትን ቀን* የናቀ ማን ነው?+ እነሱ ሐሴት ያደርጋሉና፤ በዘሩባቤልም እጅ ላይ ቱምቢውን* ያያሉ። እነዚህ ሰባቱ በመላው ምድር የሚዘዋወሩ የይሖዋ ዓይኖች ናቸው።”+

11 ከዚያም “ከመቅረዙ በስተ ቀኝና በስተ ግራ ያሉት የእነዚህ ሁለት የወይራ ዛፎች ትርጉም ምንድን ነው?” በማለት ጠየቅኩት።+ 12 ለሁለተኛም ጊዜ እንዲህ ስል ጠየቅኩት፦ “በሁለቱ የወርቅ ቱቦዎች አማካኝነት ወርቃማ ፈሳሽ የሚያፈሱት የሁለቱ የወይራ ዛፎች ቅርንጫፎች* ትርጉም ምንድን ነው?”

13 እሱም “የእነዚህ ነገሮች ትርጉም ምን እንደሆነ አታውቅም?” አለኝ።

እኔም “ጌታዬ ሆይ፣ አላውቅም” ብዬ መለስኩለት።

14 እሱም “እነዚህ በምድር ሁሉ ጌታ አጠገብ የቆሙት ሁለቱ ቅቡዓን ናቸው” አለ።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ