የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘካርያስ 5
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘካርያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ራእይ 6፦ የሚበር ጥቅልል (1-4)

      • ራእይ 7፦ የኢፍ መስፈሪያ (5-11)

        • ክፋትን የምታመለክት ሴት (8)

        • መስፈሪያዋ ወደ ሰናኦር ምድር ተወሰደች (9-11)

ዘካርያስ 5:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    አንድ ክንድ 44.5 ሴንቲ ሜትር ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

ዘካርያስ 5:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 20:15
  • +ዘፀ 20:7፤ ዘሌ 19:12

ዘካርያስ 5:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ኢፍ።” ይህም አንድ ኢፍ ለመለካት የሚያገለግልን መስፈሪያ ወይም ቅርጫት ያመለክታል። አንድ ኢፍ 22 ሊትር ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

ዘካርያስ 5:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ባለ ረጃጅም እግር ትልቅ አሞራ።

ዘካርያስ 5:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ባቢሎንን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 10:8, 10፤ 11:1, 2፤ ዳን 1:2

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘካ. 5:3ዘፀ 20:15
ዘካ. 5:3ዘፀ 20:7፤ ዘሌ 19:12
ዘካ. 5:11ዘፍ 10:8, 10፤ 11:1, 2፤ ዳን 1:2
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘካርያስ 5:1-11

ዘካርያስ

5 ዳግመኛ ቀና ብዬ ስመለከት የሚበር ጥቅልል አየሁ። 2 እሱም “የምታየው ምንድን ነው?” አለኝ።

እኔም “ርዝመቱ 20 ክንድ፣* ወርዱ ደግሞ 10 ክንድ የሆነ የሚበር ጥቅልል አያለሁ” ስል መለስኩለት።

3 ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “ይህ በመላው ምድር ላይ የሚወጣው እርግማን ነው፤ ምክንያቱም የሚሰርቁ ሁሉ+ በአንደኛው በኩል በተጻፈው መሠረት አልተቀጡም፤ ደግሞም በሐሰት የሚምሉ ሁሉ+ በሌላኛው በኩል በተጻፈው መሠረት አልተቀጡም። 4 ‘እኔ ልኬዋለሁ’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ ‘ወደ ሌባውም ቤት ይገባል፤ በስሜ በሐሰት ወደሚምለውም ሰው ቤት ይገባል፤ በዚያም ቤት ውስጥ ይቀመጣል፤ እንጨቱንና ድንጋዩን ጨምሮ ቤቱን ይበላዋል።’”

5 ከዚያም ሲያነጋግረኝ የነበረው መልአክ ወደ እኔ ቀርቦ “እባክህ ቀና ብለህ የምትወጣውን ነገር ተመልከት” አለኝ።

6 እኔም “ምንድን ነች?” አልኩ።

እሱም መልሶ “ይህች የምትወጣው የኢፍ መስፈሪያ* ናት” አለ። አክሎም “በምድሪቱ ሁሉ የሰዎቹ መልክ ይህ ነው” አለ። 7 እኔም ከእርሳስ የተሠራው ክቡ መክደኛ ሲነሳ አየሁ፤ በመስፈሪያዋም ውስጥ አንዲት ሴት ተቀምጣ ነበር። 8 እሱም “ይህች ሴት ክፋትን ታመለክታለች” አለኝ። ከዚያም የኢፍ መስፈሪያዋ ውስጥ መልሶ ጣላት፤ ቀጥሎም ከእርሳስ የተሠራውን ከባዱን መክደኛ መስፈሪያዋ አፍ ላይ ገጠመው።

9 ከዚያም ቀና ብዬ ስመለከት ሁለት ሴቶች ወደ ፊት ሲመጡ አየሁ፤ በነፋስም መካከል ወደ ላይ ተወነጨፉ። ክንፎቻቸው የራዛ* ዓይነት ክንፎች ነበሩ። እነሱም መስፈሪያዋን በምድርና በሰማይ መካከል አነሷት። 10 እኔም ያነጋግረኝ የነበረውን መልአክ “የኢፍ መስፈሪያዋን ወዴት እየወሰዷት ነው?” ስል ጠየቅኩት።

11 እሱም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ቤት ሊሠሩላት ወደ ሰናኦር*+ ምድር እየወሰዷት ነው፤ ቤቱም በተዘጋጀ ጊዜ በዚያ በተገቢው ቦታዋ ላይ ያስቀምጧታል።”

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ