የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዕብራውያን 13
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዕብራውያን የመጽሐፉ ይዘት

      • መደምደሚያ ላይ የቀረበ ማሳሰቢያና ሰላምታ (1-25)

        • “እንግዳ መቀበልን አትርሱ” (2)

        • ‘ጋብቻ በሁሉ ዘንድ ክቡር ይሁን’ (4)

        • “አመራር ለሚሰጧችሁ ታዘዙ” (7, 17)

        • የምስጋና መሥዋዕት አቅርቡ (15, 16)

ዕብራውያን 13:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ተሰ 4:9፤ 1ጴጥ 1:22

ዕብራውያን 13:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ለእንግዶች ደግነት ማሳየትን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 12:13፤ 1ጢሞ 3:2
  • +ዘፍ 18:2, 3፤ 19:1-3

ዕብራውያን 13:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ከእነሱ ጋር መከራ የምትቀበሉ ያህል ሆናችሁ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 12:15
  • +ቆላ 4:18

ዕብራውያን 13:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻው ላይ “የፆታ ብልግና” የሚለውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 5:16, 20፤ ማቴ 5:28
  • +ምሳሌ 6:32፤ 1ቆሮ 6:9, 10, 18፤ ገላ 5:19, 21

ዕብራውያን 13:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ጢሞ 6:10
  • +ምሳሌ 30:8, 9፤ 1ጢሞ 6:8
  • +ዘዳ 31:6, 8

ዕብራውያን 13:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 118:6፤ ዳን 3:17፤ ሉቃስ 12:4

ዕብራውያን 13:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ጢሞ 5:17፤ ዕብ 13:17
  • +1ቆሮ 11:1፤ 2ተሰ 3:7

ዕብራውያን 13:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከምግብ ጋር የተያያዙ ደንቦችን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 14:17፤ 1ቆሮ 8:8፤ ቆላ 2:16

ዕብራውያን 13:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 9:13፤ 10:18

ዕብራውያን 13:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቅድስተ ቅዱሳኑን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 16:27

ዕብራውያን 13:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕብ 9:13, 14
  • +ዮሐ 19:17

ዕብራውያን 13:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 15:3፤ 2ቆሮ 12:10፤ 1ጴጥ 4:14

ዕብራውያን 13:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕብ 11:10፤ 12:22

ዕብራውያን 13:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 7:12፤ መዝ 50:14, 23
  • +ሮም 10:9
  • +መዝ 69:30, 31፤ ሆሴዕ 14:2

ዕብራውያን 13:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 12:13
  • +ፊልጵ 4:18

ዕብራውያን 13:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሳችሁን ተግተው ስለሚጠብቁና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 20:28
  • +1ተሰ 5:12
  • +ኤፌ 5:21፤ 1ጴጥ 5:5

ዕብራውያን 13:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ጥሩ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ቆሮ 1:12

ዕብራውያን 13:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ጴጥ 5:4

ዕብራውያን 13:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 27:1

ተዛማጅ ሐሳብ

ዕብ. 13:11ተሰ 4:9፤ 1ጴጥ 1:22
ዕብ. 13:2ሮም 12:13፤ 1ጢሞ 3:2
ዕብ. 13:2ዘፍ 18:2, 3፤ 19:1-3
ዕብ. 13:3ሮም 12:15
ዕብ. 13:3ቆላ 4:18
ዕብ. 13:4ምሳሌ 5:16, 20፤ ማቴ 5:28
ዕብ. 13:4ምሳሌ 6:32፤ 1ቆሮ 6:9, 10, 18፤ ገላ 5:19, 21
ዕብ. 13:51ጢሞ 6:10
ዕብ. 13:5ምሳሌ 30:8, 9፤ 1ጢሞ 6:8
ዕብ. 13:5ዘዳ 31:6, 8
ዕብ. 13:6መዝ 118:6፤ ዳን 3:17፤ ሉቃስ 12:4
ዕብ. 13:71ጢሞ 5:17፤ ዕብ 13:17
ዕብ. 13:71ቆሮ 11:1፤ 2ተሰ 3:7
ዕብ. 13:9ሮም 14:17፤ 1ቆሮ 8:8፤ ቆላ 2:16
ዕብ. 13:101ቆሮ 9:13፤ 10:18
ዕብ. 13:11ዘሌ 16:27
ዕብ. 13:12ዕብ 9:13, 14
ዕብ. 13:12ዮሐ 19:17
ዕብ. 13:13ሮም 15:3፤ 2ቆሮ 12:10፤ 1ጴጥ 4:14
ዕብ. 13:14ዕብ 11:10፤ 12:22
ዕብ. 13:15ዘሌ 7:12፤ መዝ 50:14, 23
ዕብ. 13:15ሮም 10:9
ዕብ. 13:15መዝ 69:30, 31፤ ሆሴዕ 14:2
ዕብ. 13:16ሮም 12:13
ዕብ. 13:16ፊልጵ 4:18
ዕብ. 13:17ሥራ 20:28
ዕብ. 13:171ተሰ 5:12
ዕብ. 13:17ኤፌ 5:21፤ 1ጴጥ 5:5
ዕብ. 13:182ቆሮ 1:12
ዕብ. 13:201ጴጥ 5:4
ዕብ. 13:24ሥራ 27:1
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዕብራውያን 13:1-25

ለዕብራውያን የተጻፈ ደብዳቤ

13 እርስ በርሳችሁ እንደ ወንድማማች መዋደዳችሁን ቀጥሉ።+ 2 እንግዳ መቀበልን* አትርሱ፤+ አንዳንዶች ይህን ሲያደርጉ ሳያውቁት መላእክትን አስተናግደዋልና።+ 3 በእስር ላይ ያሉትን ከእነሱ ጋር ታስራችሁ እንዳላችሁ አድርጋችሁ በማሰብ+ ሁልጊዜ አስታውሷቸው፤+ እናንተም ራሳችሁ ገና በሥጋ ያላችሁ በመሆናችሁ* እንግልት እየደረሰባቸው ያሉትን አስቡ። 4 ጋብቻ በሁሉ ዘንድ ክቡር፣ መኝታውም ከርኩሰት የጸዳ ይሁን፤+ አምላክ ሴሰኞችንና* አመንዝሮችን ይፈርድባቸዋልና።+ 5 አኗኗራችሁ ከገንዘብ ፍቅር ነፃ ይሁን፤+ ባሏችሁ ነገሮች ረክታችሁ ኑሩ።+ እሱ “ፈጽሞ አልተውህም፤ በምንም ዓይነት አልጥልህም” ብሏልና።+ 6 ስለዚህ በሙሉ ልብ “ይሖዋ* ረዳቴ ነው፤ አልፈራም። ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?” እንላለን።+

7 የአምላክን ቃል የነገሯችሁን በመካከላችሁ ሆነው አመራር የሚሰጡትን አስቡ፤+ ደግሞም ምግባራቸው ያስገኘውን ውጤት በሚገባ በማጤን በእምነታቸው ምሰሏቸው።+

8 ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትም፣ ዛሬም፣ ለዘላለምም ያው ነው።

9 በልዩ ልዩና እንግዳ በሆኑ ትምህርቶች አትወሰዱ፤ ልባችን በምግብ* ሳይሆን በአምላክ ጸጋ ቢጠናከር መልካም ነውና፤ በዚህ የተጠመዱ ምንም አልተጠቀሙም።+

10 እኛ መሠዊያ ያለን ሲሆን በድንኳኑ ውስጥ ቅዱስ አገልግሎት የሚያቀርቡት ከመሠዊያው ላይ ወስደው መብላት አይፈቀድላቸውም።+ 11 ምክንያቱም ሊቀ ካህናቱ የእንስሳቱን ደም የኃጢአት መባ አድርጎ ወደ ቅዱሱ ስፍራ* የሚወስደው ሲሆን ሥጋው ግን ከሰፈሩ ውጭ ይቃጠላል።+ 12 ስለዚህ ኢየሱስም ሕዝቡን በገዛ ራሱ ደም ለመቀደስ+ ከከተማው በር ውጭ መከራ ተቀበለ።+ 13 እንግዲህ እኛም እሱ የተሸከመውን ነቀፋ ተሸክመን ከሰፈር ውጭ እሱ ወዳለበት እንሂድ፤+ 14 በዚህ ቋሚ ከተማ የለንምና፤ ከዚህ ይልቅ ወደፊት የምትመጣዋን ከተማ በጉጉት እንጠባበቃለን።+ 15 ስለዚህ በኢየሱስ አማካኝነት የውዳሴ መሥዋዕት ዘወትር ለአምላክ እናቅርብ፤+ ይህም ስሙን በይፋ የምናውጅበት+ የከንፈራችን ፍሬ ነው።+ 16 በተጨማሪም መልካም ማድረግንና ያላችሁን ነገር ለሌሎች ማካፈልን አትርሱ፤+ አምላክ እንዲህ ባሉት መሥዋዕቶች እጅግ ይደሰታልና።+

17 ተግተው ስለሚጠብቋችሁና* ይህን በተመለከተ ስሌት ስለሚያቀርቡ+ በመካከላችሁ ሆነው አመራር ለሚሰጧችሁ ታዘዙ+ እንዲሁም ተገዙ፤+ ይህን የምታደርጉት ሥራቸውን በደስታ እንጂ በሐዘን እንዳያከናውኑ ነው፤ አለዚያ ሥራቸውን የሚያከናውኑት በሐዘን ይሆናል፤ ይህ ደግሞ እናንተን ይጎዳችኋል።

18 ለእኛ መጸለያችሁን ቀጥሉ፤ ምክንያቱም ሐቀኛ* ሕሊና እንዳለን እናምናለን፤ ደግሞም በሁሉም ነገር በሐቀኝነት ለመኖር እንፈልጋለን።+ 19 በተለይ ደግሞ ወደ እናንተ በፍጥነት ተመልሼ እንድመጣ ትጸልዩልኝ ዘንድ አሳስባችኋለሁ።

20 እንግዲያው ታላቅ የበጎች እረኛ+ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ የዘላለማዊውን ቃል ኪዳን ደም ይዞ ከሞት እንዲነሳ ያደረገው የሰላም አምላክ 21 ፈቃዱን እንድታደርጉ በመልካም ነገር ሁሉ ያስታጥቃችሁ፤ እሱ በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን ነገር እንድናደርግ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ያነሳሳናል። ለእሱ ለዘላለም ክብር ይሁን። አሜን።

22 እንግዲህ ወንድሞች፣ የጻፍኩላችሁ ደብዳቤ አጭር ስለሆነ ይህን የማበረታቻ ቃል በትዕግሥት እንድታዳምጡ አሳስባችኋለሁ። 23 ወንድማችን ጢሞቴዎስ መፈታቱን እንድታውቁ እፈልጋለሁ። ቶሎ ከመጣ አብረን መጥተን እናያችኋለን።

24 በመካከላችሁ ሆነው አመራር ለሚሰጧችሁ ሁሉና ለቀሩት ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ አቅርቡልኝ። በጣሊያን+ ያሉት ሰላምታ ልከውላችኋል።

25 የአምላክ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ