ዘፍጥረት 2:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 በዚህ ጊዜ ሰውየው እንዲህ አለ፦ “እንግዲህ እሷ የአጥንቶቼ አጥንት፣የሥጋዬም ሥጋ ናት። እሷ ከወንድ ስለተገኘች+‘ሴት’ ትባላለች።” ኢሳይያስ 45:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 እኔ ምድርን ሠርቻለሁ፤+ በላይዋም ላይ ሰውን ፈጥሬአለሁ።+ በገዛ እጆቼ ሰማያትን ዘርግቻለሁ፤+ሠራዊታቸውንም ሁሉ አዛለሁ።”+ ማቴዎስ 19:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 እሱም መልሶ እንዲህ አለ፦ “ፈጣሪ ከመጀመሪያውም ወንድና ሴት አድርጎ እንደፈጠራቸው አላነበባችሁም?+