ከሐምሌ 28–ነሐሴ 3
ምሳሌ 24
መዝሙር 38 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
1. ለመከራ ወቅት ራሳችሁን አጠናክሩ
(10 ደቂቃ)
እውቀትና ጥበብ አከማቹ (ምሳሌ 24:5፤ w23.07 18 አን. 15)
ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ በሚያጋጥማችሁ ጊዜም ጭምር መንፈሳዊ ልማዳችሁን ይዛችሁ ቀጥሉ (ምሳሌ 24:10፤ w09 12/15 18 አን. 12-13)
2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች
(10 ደቂቃ)
ምሳሌ 24:27—የዚህ ጥቅስ መልእክት ምንድን ነው? (w09 10/15 12)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
(4 ደቂቃ) ምሳሌ 24:1-20 (th ጥናት 11)
4. ውይይት መጀመር
(2 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ምሥክርነት መስጠት ከመቻልህ በፊት ውይይታችሁ ይደመደማል። (lmd ምዕራፍ 2 ነጥብ 4)
5. ውይይት መጀመር
(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። (lmd ምዕራፍ 3 ነጥብ 4)
6. ውይይት መጀመር
(3 ደቂቃ) የአደባባይ ምሥክርነት። የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ስለምንሰጥበት ዝግጅት ለግለሰቡ ንገረው፤ እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የአድራሻ ካርድ ስጠው። (lmd ምዕራፍ 4 ነጥብ 3)
7. ንግግር
(3 ደቂቃ) lmd ተጨማሪ መረጃ ሀ ነጥብ 11—ጭብጥ፦ አምላክ ሐሳቡን ገልጾልናል። (th ጥናት 6)
መዝሙር 99
8. በመከራ ወቅት እርስ በርስ ተረዳዱ
(15 ደቂቃ) ውይይት።
ወረርሽኝ፣ የተፈጥሮ አደጋ፣ ሕዝባዊ ዓመፅ፣ ጦርነት ወይም ስደት ድንገት ሊከሰት ይችላል። እንዲህ ያለ ሁኔታ ሲከሰት በመከራው የተጎዱት ክርስቲያኖች እርስ በርስ ይረዳዳሉ እንዲሁም ይበረታታሉ። ይሁንና መከራው እኛን በቀጥታ ባይነካንም እንኳ በወንድሞቻችን ላይ በደረሰው ነገር በጣም እናዝናለን፤ እንዲሁም እነሱን ለመርዳት አቅማችን የፈቀደውን ሁሉ እናደርጋለን።—1ቆሮ 12:25, 26
አንደኛ ነገሥት 13:6ን እና ያዕቆብ 5:16ለን አንብብ። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦
የአምላክ አገልጋዮች ሌሎችን አስመልክቶ የሚያቀርቡት ጸሎት ትልቅ ኃይል አለው የምንለው ለምንድን ነው?
ማርቆስ 12:42-44ን እና 2 ቆሮንቶስ 8:1-4ን አንብብ። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦
የተቸገሩ ወንድሞቻችንን ለመርዳት ለዓለም አቀፉ ሥራ መዋጮ ማድረግ የምንችለው ብዙ ገንዘብ ባይኖረንም እንኳ እንዲህ ከማድረግ ወደኋላ ማለት የሌለብን ለምንድን ነው?
በእገዳ ሥር ያሉ ወንድሞችን ማበረታታት የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦
ወንድሞች በምሥራቅ አውሮፓ ሥራችን በታገደባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የእምነት አጋሮቻቸውን ለመርዳት ምን መሥዋዕት ከፍለዋል?
በእገዳ ሥር የነበሩት ወንድሞች አንድ ላይ እንድንሰበሰብና እርስ በርስ እንድንበረታታ የተሰጠንን መመሪያ የታዘዙት እንዴት ነው?—ዕብ 10:24, 25
9. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(30 ደቂቃ) lfb ትምህርት 4-5