ዘፍጥረት 8:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ይሖዋም ደስ የሚያሰኘውን* መዓዛ አሸተተ። ስለዚህ ይሖዋ በልቡ እንዲህ አለ፦ “በሰው የተነሳ ከእንግዲህ ወዲህ ፈጽሞ ምድርን አልረግምም፤+ ምክንያቱም የሰው የልብ ዝንባሌ ከልጅነቱ ጀምሮ መጥፎ ነው፤+ ደግሞም አሁን እንዳደረግኩት ሕያው ፍጡርን ሁሉ ፈጽሞ ዳግመኛ አላጠፋም።+ ኤርምያስ 17:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ልብ ከምንም ነገር በላይ ከዳተኛ* ነው፤ ማንኛውንም ነገር ከማድረግ አይመለስም።*+ ማንስ ሊያውቀው ይችላል? ማቴዎስ 15:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ለምሳሌ ከልብ ክፉ ሐሳብ ይወጣል፦+ ግድያ፣ ምንዝር፣ የፆታ ብልግና፣* ሌብነት፣ በሐሰት መመሥከርና ስድብ።
21 ይሖዋም ደስ የሚያሰኘውን* መዓዛ አሸተተ። ስለዚህ ይሖዋ በልቡ እንዲህ አለ፦ “በሰው የተነሳ ከእንግዲህ ወዲህ ፈጽሞ ምድርን አልረግምም፤+ ምክንያቱም የሰው የልብ ዝንባሌ ከልጅነቱ ጀምሮ መጥፎ ነው፤+ ደግሞም አሁን እንዳደረግኩት ሕያው ፍጡርን ሁሉ ፈጽሞ ዳግመኛ አላጠፋም።+