8 ከዚያም ይሁዳ አባቱን እስራኤልን እንዲህ በማለት ለመነው፦ “እኛም ሆን አንተ እንዲሁም ትናንሽ ልጆቻችን+ በረሃብ ከምናልቅ፣ በሕይወት እንድንተርፍ+ ልጁ ከእኔ ጋር እንዲሄድ ፍቀድና+ ተነስተን ወደዚያ እንሂድ። 9 የልጁን ደህንነት በተመለከተ ኃላፊነቱን እኔ እወስዳለሁ።+ አንድ ነገር ቢሆን እኔን ተጠያቂ ልታደርገኝ ትችላለህ። ልጁን ወደ አንተ መልሼ ባላመጣውና ባላስረክብህ በሕይወቴ ሙሉ በፊትህ በደለኛ ልሁን።