29 እስራኤልም የሚሞትበት ቀን ሲቃረብ+ ልጁን ዮሴፍን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ እባክህ እጅህን ከጭኔ በታች አድርግ፤ ለእኔም ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት አሳየኝ። እባክህ በግብፅ አትቅበረኝ።+ 30 በምሞትበት ጊዜ ከግብፅ አውጥተህ በአባቶቼ መቃብር ቅበረኝ።”+ እሱም “እሺ፣ እንዳልከኝ አደርጋለሁ” አለው። 31 ያዕቆብም “በል ማልልኝ” አለው፤ እሱም ማለለት።+ በዚህ ጊዜ እስራኤል በአልጋው ራስጌ ላይ ሰገደ።+