ዮናስ 3:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ዮናስም የይሖዋን ቃል በመታዘዝ ተነስቶ ወደ ነነዌ+ ሄደ።+ ነነዌ እጅግ ታላቅ ከተማ የነበረች ስትሆን* በእግር የሦስት ቀን ያህል መንገድ ታስኬድ ነበር። ማቴዎስ 12:41 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 41 የነነዌ ሰዎች የዮናስን ስብከት ሰምተው ንስሐ ስለገቡ+ በፍርድ ወቅት ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስተው ይኮንኑታል። ነገር ግን ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ።+