ዘፍጥረት 3:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ከመሬት ስለተገኘህ+ ወደ መሬት እስክትመለስ ድረስ ላብህን እያንጠፈጠፍክ ምግብ ትበላለህ። አፈር ስለሆንክ ወደ አፈር ትመለሳለህ።”+ መዝሙር 103:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 እሱ እንዴት እንደተሠራን በሚገባ ያውቃልና፤+አፈር መሆናችንን ያስታውሳል።+ መክብብ 3:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ሁሉም ወደ አንድ ቦታ ይሄዳሉ።+ ሁሉም የተገኙት ከአፈር ነው፤+ ሁሉም ወደ አፈር ይመለሳሉ።+