9 አቢሜሌክም ወዲያው ይስሐቅን ጠርቶ “መቼም እሷ ሚስትህ እንደሆነች ግልጽ ነው! ታዲያ ‘እህቴ ናት’ ያልከው ለምንድን ነው?” አለው። በዚህ ጊዜ ይስሐቅ “እንዲህ ያልኩት በእሷ የተነሳ ሕይወቴን እንዳላጣ ስለፈራሁ ነው” አለው።+ 10 አቢሜሌክ ግን “እንዴት እንዲህ ያለ ነገር ታደርግብናለህ?+ ከእኛ ሰዎች አንዱ ከሚስትህ ጋር ሊተኛ ይችል ነበር፤ እኛንም በደለኞች አድርገህ ታስቆጥረን ነበር!”+ አለው።