-
ዘፍጥረት 49:29-33አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
29 ከዚህ በኋላ የሚከተሉትን ትእዛዛት ሰጣቸው፦ “እንግዲህ እኔ ወደ ወገኖቼ ልሰበሰብ* ነው።+ በሂታዊው በኤፍሮን እርሻ ውስጥ በሚገኘው ዋሻ+ ከአባቶቼ ጋር ቅበሩኝ፤ 30 አብርሃም ለመቃብር ስፍራ ብሎ ከሂታዊው ከኤፍሮን በገዛው እርሻ ይኸውም በከነአን ምድር በማምሬ ፊት ለፊት በሚገኘው በማክፈላ እርሻ ውስጥ ባለው ዋሻ ቅበሩኝ። 31 አብርሃምንና ሚስቱን ሣራን የቀበሯቸው እዚያ ነው።+ ይስሐቅንና ሚስቱን ርብቃንም የቀበሯቸው እዚያ ነው፤+ እኔም ብሆን ሊያን የቀበርኳት እዚያው ነው። 32 እርሻውም ሆነ በውስጡ ያለው ዋሻ የተገዛው ከሄት ወንዶች ልጆች ነው።”+
33 በዚህ መንገድ ያዕቆብ ለወንዶች ልጆቹ እነዚህን መመሪያዎች ሰጥቶ ጨረሰ። ከዚያም እግሮቹን ወደ አልጋው አውጥቶ የመጨረሻ እስትንፋሱን ተነፈሰ፤ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ።*+
-
-
ዘፍጥረት 50:13, 14አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
13 ወንዶች ልጆቹም ወደ ከነአን ምድር ወስደው አብርሃም ለመቃብር ቦታ ብሎ ከሂታዊው ከኤፍሮን በገዛው ከማምሬ ፊት ለፊት በሚገኘው እርሻ ማለትም በማክፈላ እርሻ ውስጥ ባለው ዋሻ ቀበሩት።+ 14 ዮሴፍም አባቱን ከቀበረ በኋላ ከወንድሞቹና ለአባቱ ቀብር አብረውት ከሄዱት ሁሉ ጋር ወደ ግብፅ ተመለሰ።
-