ዘፍጥረት 22:16-18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 እንዲህም አለው፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በራሴ እምላለሁ፤+ ይህን ስላደረግክ እንዲሁም ልጅህን፣ አንድ ልጅህን ለመስጠት ስላልሳሳህ+ 17 በእርግጥ እባርክሃለሁ፤ ዘርህንም በሰማያት ላይ እንዳሉ ከዋክብትና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ በእርግጥ አበዛዋለሁ፤+ ዘርህም የጠላቶቹን በር* ይወርሳል።+ 18 ቃሌን ስለሰማህ የምድር ብሔራት ሁሉ በዘርህ+ አማካኝነት ለራሳቸው በረከት ያገኛሉ።’”+ መዝሙር 105:9-11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ከአብርሃም ጋር የገባውን ቃል ኪዳን፣+ለይስሐቅም በመሐላ የገባውን ቃል አይረሳም፤+10 ቃሉን ለያዕቆብ ድንጋጌ፣ለእስራኤልም ዘላቂ ቃል ኪዳን አድርጎ አቋቋመ፤11 “የከነአንን ምድርርስትህ አድርጌ እሰጥሃለሁ” አለ።+ ዕብራውያን 6:13, 14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 አምላክ ለአብርሃም ቃል በገባለት ጊዜ ሊምልበት የሚችል ከእሱ የሚበልጥ ሌላ ማንም ስለሌለ በራሱ ስም ማለ፤+ 14 እንዲህም አለ፦ “በእርግጥ እባርክሃለሁ፤ ዘርህንም በእርግጥ አበዛዋለሁ።”+
16 እንዲህም አለው፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በራሴ እምላለሁ፤+ ይህን ስላደረግክ እንዲሁም ልጅህን፣ አንድ ልጅህን ለመስጠት ስላልሳሳህ+ 17 በእርግጥ እባርክሃለሁ፤ ዘርህንም በሰማያት ላይ እንዳሉ ከዋክብትና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ በእርግጥ አበዛዋለሁ፤+ ዘርህም የጠላቶቹን በር* ይወርሳል።+ 18 ቃሌን ስለሰማህ የምድር ብሔራት ሁሉ በዘርህ+ አማካኝነት ለራሳቸው በረከት ያገኛሉ።’”+
9 ከአብርሃም ጋር የገባውን ቃል ኪዳን፣+ለይስሐቅም በመሐላ የገባውን ቃል አይረሳም፤+10 ቃሉን ለያዕቆብ ድንጋጌ፣ለእስራኤልም ዘላቂ ቃል ኪዳን አድርጎ አቋቋመ፤11 “የከነአንን ምድርርስትህ አድርጌ እሰጥሃለሁ” አለ።+
13 አምላክ ለአብርሃም ቃል በገባለት ጊዜ ሊምልበት የሚችል ከእሱ የሚበልጥ ሌላ ማንም ስለሌለ በራሱ ስም ማለ፤+ 14 እንዲህም አለ፦ “በእርግጥ እባርክሃለሁ፤ ዘርህንም በእርግጥ አበዛዋለሁ።”+